በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የቀጠለዉ አሰቃቂ ግድያ 

ትናንት ጠዋት በመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ቂህዶ በተባለች ስፋራ ታጣቂዎች መኪና እያስቆሙ በፈፀሙት ጥቃት ከ 30 በላይ ሰዎች ተገደሉ። የሟቾች ቁጥር ከተጠቀሰዉ ቁጥር በላይ ነዉ የሚሉ ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፉት ሦስት ቀናት ብቻ በድባጢ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ታጣቂዎች ብዙ ሰዎችን ገድለዋል ከፍተኛ ጉዳትም አድርሰዋል።

3333ትናንት ጠዋት በመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ቂህዶ በተባለች ስፋራ ታጣቂዎች መኪና እያስቆሙ በፈፀሙት ጥቃት ከ 30 በላይ ሰዎች ተገደሉ። የሟቾች ቁጥር ከተጠቀሰዉ ቁጥር በላይ ነዉ የሚሉ ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፉት ሦስት ቀናት ብቻ በድባጢ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ታጣቂዎች ብዙ ሰዎችን ገድለዋል ከፍተኛ ጉዳትም አድርሰዋል።  የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት በወረዳዎ ታጣቂዎች የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪን አስቁመዉ መግደላቸዉን ገልፆአል። ግድያዉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣዉ መግለጫ “በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ፋታ የማይሰጥ ሆኖ በመቀጠሉ፤ በፌዴራልና በክልሉ መንግሥታት የፀጥታ ኃይሎች መካከል በፍጥነትና ንቁ ሆኖ መጠበቅ ላይ የተመሰረተ የተሻለ ቅንጅት የሚሻ ነው። የፌዴራልና የክልሉ የፀጥታና የፍትሕ አካላት ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመሆን እነዚህን ጥቃቶች  ሊያስቆም የሚችል አዲስ ክልላዊ የፀጥታ ስትራቴጂ  ሊነድፉ ይገባል።”  የአሶሳዉ ወኪላችን ዘገባ ልኮልናል።

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

DW

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.