የሲኦል ደናሿ ህውአትና የነገው ዶክተር አብይ – ከተማ  ዋቅጅራ

woyane 1

ህውአት ሲኦል ደጃፍ ላይ ቆማ የምትደንስ ድንቅ ኮሜዲ ናት:: ጣር ላይ ሆና ስለመደምሰስ የምታወራ ድ አስቂኝ ፍጡር ናት:: እፍኝ ሆና ሳለ እራሷን እንደ ማይገፋ ተራራ ነኝ የምትል የውሸት ትርክት ናት:: ጠንካራነኝ ለማለት ኢትዮጵያዊያን ለሷ አንሰው ከኤርትራ ጋር ወጉኝ ለማለት ትዳዳለች:: ውጊያ ከጀመርን በሳምት ውስጥ የአብይን ጆሮ ይዘን ከቤተመንግስት እናወጣዋለን ብለው እንዳልፎከሩ በሳምንታቸው ልንጠፋ ነውና አስታርቁኝ የሚል መልእክታቸው ለአለሙ ማህበረሰብ ማዝጎድጎድ ጀመሩ:: ለትግራይ ጦርነት በህላዊ ጨዋታ ነው ብሎ ሲያቅራራ ተው ነውር ነው በትግራይ ህዝብ አትቀልድ ያለው ማንም  የለም ነበረ የኢትዮጵያ  ህዝብ ግን እንዲ በማለት ቀልደውበታል << ጥይትስ ባህላዊ ምግባችሁ ነው>> በማለት:: ጦርነት በአፍ የሚወራ በወሬ የምታሸንፈው ሳይሆን በሜዳና በጫካ፣ በተራራና በገደ፣ በቀንና በማታ  ተፈትነህ በብቃት የምትወጣው የጀግናዎች ሜዳ ነው:: ይሄንን ጀግንነት በብቃትና በአይበገሬነት የተወጣው ደግሞ የአፍ ጦረኛዋ ህውአት ሳትሆን ፋኖ፣ የአማራ ገበሬ፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ የአማራ ሚንሻና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ናቸው:: የቁርጡ ቀን ሲመጣ ወንድ የሚውልበት ቦታ ተገኝቶ የጀግንነ  ገድል የፈጸመው ፋኖና ገበሬው ታሪካቸው መንግስት አሰልጥኖ ካስታጠቃቸው ባልተናነሰ ከድል ማግስት ታሪካቸው ለአለም ሊነገር ይገባል፡፡

Woyane

እንደጥቆማ መንግስት ካለምንም ወጪ አገርን መጠበቅና ማስጠበቅ ከፈለገ ተኩሰው የማይስቱትን እና በሃገር የማይደራደሩትን ፋኖን እና ገበሬውን ዘመናዊ መሳሪያ  ቢያስታጥቅ በሰላሙ ግዜ የራሳቸውን ስራ እየሰሩ ጠላት ሲመጣ ደግሞ እንደ ንብ የሚናደፉ ጀግና የኢትዮጵያ መሰረት ናቸው:: ይሄንን ጀብዱ ያለመመስከር እራሱ ባንዳነት ነው::

ህውአትን  ሳስብ ብዙ ጉዶች ቢመጡብኝም ከብዙዎቹ አንዷን መዘን የፌስ ቡክ አርበኞቿን እንይ:: ስማቸው ዲጅታል ወያኔ ነው፡፡ ካለስማቸው ስም ተላብሰው ካለግብራቸው ግብር ተዋርሰው ፌስብክ መንደርን የኢትዮጵያ  ክብርን  የት ድረስ እንዳወረዱት መመልከት ያስፈልጋል። ኦሮሞ ሳይሆኑ የኦሮሞ ስም አማራ  ሳይሆኑ የአማራ  ስም በመያዝ እነዚህ ሁለት ብሄሮችን ለማጋጨት ያልተሳደቡት ስድብ ያልተራገሙት እርግማን ምን አለ? ኢትዮጵያዊነት እንዲ ናቸው እንዴ እስከሚባል የብልግናቸውንና የክፋታቸው ጥግ አሳይተዋል:: እኔ የምጽፈው ለነዚ ባለጌዎች ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ ነው የቀራችሁ ግዜ ነጠብጣብ ግዜ  ቢቀራችሁም ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለመታረቅ በውጪም በአገር ውስጥም ያላችሁ ድምጻችሁን ማሰሚያው ግዜ ዛሬ ነው። ለዚህም ፊያታዊ ዘየማንን ማሰብ በቂ ነው በመጨረሻው ሰአት ምህረትን እንዳገኘ  ሁሉ እናተም ከልብ በመመለስ ህውአት ይዞአችሁ ሲኦል እንዳይገባ የኪነቱ አባል ሳትሆኑ አውጋዦች ሆናችሁ ውጡ:: ስለትግራይ ህዝብ የመጨረቻ መልእክቴ  ነው።

woyane1

አሉላ ሰለሞን ቢጮህና ቢያጓራ  የህውአት የሲኦል ኪነት አባል ስለሆነና  ልደቱን በአሜሪካ  ኤንባሲ የሚያከብር ሰርጉንም በዛው ማድረግ የፈለገ  ኤንባሲውን እንደግል ንብረቱ የሚጠቀብ ብቻ ሳይሆን ወጪዎቹ ሁሉ በኤንባሲው የሚሸፈንለት የኢትዮጵያን  ህዝብ ንብረት የሚቦጦቡጥ ስለነበረ  ያቺ ጥቅም ስለቀረበትና ቀጣሪዋ ህውአት እንዳትሞትበት ስለሚፈልግ ነው።tpf 1

ዳንኤል ብርሃኔ  ወርቃማው ባንክ ቢሮ  ተሰጥቶት በሚሊዮን ብሮች ያለስራው እየተከፈለውና አዲስ አበባ ላይ ፈላጭ ቆራጭነት ስለቀረበት ለዚህም ስልጣን ያበቃችው ህውአት ስለሆነች እሷ ታድጎ ጥቅሙን ለማስጠበቅ የሚላላጥ የትግራይ  ህዝብ ጠንቅ የኢትዮጵያ  ህዝብ ደግሞ ጠላት ነው::

 

ሰናይት መብራቱ ይቺ ደግሞ ነውሯ  ክብሯ የሆነች ሴት ናት:: ማእከላዊ የታሰሩትን የህግ ታራሚ ላይ ፊቷን  ሸፍራ ሃፍረተ ስጋዋን እያሳየች የምትጸዳዳ ወራዳ ክብር የሌላት ሴት ናት:: በምታሳየው የነውር ጥግ ከህውአት ሰዎች በሚሊዮን ብር የምትቀበለዋ ሰናይትመብራቱ  ለትግራ  ህዝብ ተቆርቋሪ ነኝ ስትል ህዝቡ ዝም ካላት በሷ ምክንያት ባላደረገውና ባልሰራው  ዝም በማለቱ ብቻ ዋጋ እንደሚከፍል ላሰምርምርበት እፈልጋለው:: ሰናይት መብራቱ ማለት የሲኦል ሙሽራ ናት:: ይቺን የሲኦል ሙሽራን የሚያጅብና  የሚደግፍ በሙሉ እራቱ የሚበላው ሲኦል ነው::

 

ታዲያ የትግራይ  ህዝብ እነዚህን የሲኦል ኪነተኞችን በሰሩት ግፍና  በሰሩት ጭካኔ ለአጃቢነት የሚጋበዘው በምን ሞራላቸው ነው:: እራሳቸው በሰሩት ግፍና  ጭካኔ  ወደዘላለማዊ ሞታቸው ይሂዱ እንጂ የትግራይ ህዝብ አጅቦን አብረን ወደ  መቃብር እንውረድ ሲሉ ህዝቡ መፍቀድ የለበትም  የትግራይ  ህዝብ ሆይ በነጠብጣብ ግዜአችሁ አስቡበት:: ነገ ሳይሆን ዛሬ  ነው ከዛሬም አሁን:: ግዜው አልቋል::

ነገ ጠቅላይ ሚንስት አብይ አህመድ የሚጠብቃቸው ትልቁ ፈተና

ጠቅላይ  ሚንስትሩ ሲወቀሱበትና  ከኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ከፍተኛ  ተቃውሞ ሲቀርብባቸው የነበረው ህውአትንና ወንጀል የሰሩትን ምህረት በሚል የህግ የበላይነትን እና  የሃገር ህልውናን የሚፈታተኑ ነገሮች ላይ እርምጃ  ባለመውሰዳቸው  ነበረ::  አሁንም ህውአት ባትጀምረው ኖሮ  በህውአት ላይ እርምጃ  ይወስድ ነበረ  ወይ ወይንስ አይወስድም የሚለውን ለመመለ  ከድሉ በኋላ ከትግራይ ክልል ውጪ ያሉትን ወንጀለኞች እርምጃ  ይወሰድባቸዋል ወይንስ እደቀደመው የብልጽግናን ስብከት ይሰብኩን ይሆን የሚለውን በማየት አቋማቸው የሚታይ ይሆናል::

woyane

የጠቅላ  ሚንስትሩ ፈተና  ይቀጥላል ክልል የሚባል አጥር ካልፈረሰ ህገ መንግስ የሚባለው ካልተለወጠ መለወጥ ብቻ  ሳይሆን በፍጥነት ወደ  ስራ  ካልተገባ  ህውአት ላይ እንደተዘመተው ጠቅላይ ሚንስትሩላይም ይዘመታል::

ጠቅላይ ሚንስትሩ በፖለቲካ  ፓርቲዎች በአማራው በኦሮሞው በትግሬውና  በሌሎችም ተቀባይነታቸ ጥያቄውስጥ የገባበት ነበረ ህውአት በለኮሰችው ኢትዮጵያን የማፍረስ አላማ እንዳይሳካ ሁሉም የጠቅላ ሚንስትሩን ጥሪ በሙሉ ተቀብለው ካለ ምንም ልዩነት ተሰልፈዋል ከሁሉም በፊት ሃገር ይቀድማልና  ነው:: ከድል መልስ ግን ፍልሚያው ይጀምራል::

ወልቃይት፣ ራያ፣ ጠገዴ፣ ሁመራ፣ ዳንሻ የአማራው ቀደምት ርእስቱ እንደሆነ  ይታወቃል በአሁኑ የዘር የክልል ፖሊሲ ከህዝቡ ፍቃድ ውጪ ወደ ትግራይ ተካለዋል:: የዘር ማጥፋትም ተከናውኖባቸዋል:: አሁን ደግሞ  በፋኖ፣ በገበሬው፣ በአማራ ልዩ ሃይላና ሚንሻ  እንዲሁም በኢትዮጵያ  መከላከያ  ሰራዊት መሰዋትነት ህውአትን ተደምስሳ  ግዛቱን አስመልሷል::  ይሄ ቦታ የትግሎች ሁሉ ምንጭ ነው:: የጠቅላይ ሚንስትሩም የመንግስትነታቸው ወንበር የሚጠብቅበት አልያም የሚነቃነቅበት ክስተቶች ይጠበቃል::

Woyane

ጠቅላይ ሚንስትሩ  በመግለጫቸው ምዕራብ ትግራይ በማለታቸው ከአማራው ማህበረስ የተላለፈው መልእክት በደማችን ላይ መቀለዶትን ያቁሙ የሚል ጠንካራ ቃላቶች ተላልፈዋል:: ጠቅላይ  ሚንስትር አብይ እነዚህ ግዛቶች ለትግራ  ብልጽግና  ከሰጡ ከድል ማግስት ጦርነቱን ከአማራው ማህበረስብ ጋር ነው የሚል ቀይ መስመር የተሰመረበት ቃል ከአማራው ህዝብ ተላልፏል:: የዚህን ውሳኔ  ከድል በኋላ  ወደፊት የምናየው ቢሆንም ቅሉ እኔም እንዲ እላለው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ  ከአማራው ማህበረስ ጋር የሚጋመዱበት አልያም ለመጨረሻ  ግዜ ገመዱን የሚበጥሱበትታሪካዊ ትእይንት ከድል ማግስት እንዳይፈጽሙ እመክራለው::

Woyane satenaw news 4

ሌላው ደግሞ  መሃል አዲስ አበባ  ላይ እየተካሄደ  ያለው  ነገር በጣም አደገኛና  ከባድ ነው:: በፍጹም በፍጹም ለኦሮሞ ማህበረሰብ የሚጠቅም አይደለም:: ጥቂት ስልጣኑላይ ያሉት ሰዎች ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ የሚሰሩትን ስህተት መላው የኦሮሞ  ህዝብ እንደ ትግራይ ህዝብ ዋጋ  እንዳያስከፍለን ከፍተኛ ፍራቻ  አለኝ:: ምክንያቱም አሁን እንዳየነው በሚያስደነግጥና  በሚያስፈራ  ሁኔታ በሙሉ ጀግንነትና ወኔ የአማራው ገበሬና  ፋኖ እንዲሁም የአማራ ልዩ ሃይላና ሚንሻ ወደ ወልቃይትና  ራያ   እንደዘመተው ሁሉ አዲስ አበባ የኔ ነው ያንተ አይደለም የምትለው ፖለቲካ የኢትዮጵያ  ማህበረስ ዘንድ ከደረሰ ሁሉም የኔነው በሚለው እሳቤ ኦሮሞ ለይ ጦርነት እንዳታስነሱ ጨዋታውን ቶሎ አቁሙት:: ሁሉም የኔ የሚል ስግብግብ አካሄድ ከህውአት ካልተማርን የይገባኛል ጦርነት ህዝቡ ካነሳ መቀልበሻው እንዳይጠፋን  ከድል ማግስት ከብሄር ቋት ወጥተን ኢትዮጵያን ሁሉ የሚጠቅም ስራ  እንድሰራ ለማሳሰብ እወዳለው::

 

ከተማ  ዋቅጅራ

16.11.2020

waqjirak@yahoo.com

6 Comments

 1. የራስን ጥቅም በሌላው ኪሳራ በስግብግብነት ለማሳደግ የሚደረግ ጥረት መጨረሻው የወያኔ አይነት ነው። ይልቅስ የትህነግን አግላይ፣ ዜጎችን ነዋሪ እና መጤ፣ ባለእርስት እና ጭሰኛ ብሎ የሚከፋፍለውን ህገ መንግስት ውድቅ አድርጎ ሁሉን ኢትዬጵያዊ ዜጋ በፍጹም እኩልነት የሚያስተግናድ ህገ መንትግስት መቀየር ጊዜው አሁን ከጦርነት መልስ ነው።
  በአባቶች አጥንት እና ደም የቆመችን ሀገር በባንዳ እና ዘረኛ ስትናጥ ዝም ብለን ማየት የለንብም።
  በኢትዬጵያ አንድነት እና ሉአላዊነት የማያምን ሀገሪቱን ለቆ መሄድ መብቱ ነው። ከዛ ውጭ መሀላችሁ ሆኜ ላተራምስ የሚለውን የማያዳግም ምት ሊሰጠው ይገባል።
  ትናንት የኦሮሞ መብት አስጠባቂዎች ነን እያሉ ፣ወጣቱን ሲያስጨፈጭፉ የነበሩ ዛሬ ተገልብጠው በጨፍጫፊ ው ማዱያ ብቅ ብለው ስለ ዲማክራሲ ለመናገር ሲቃታቸው ማየት ምን ያህል ሞራል አልባ፣ ህሊና ቢሶች መሆናውቸን ያሳያል።
  የነሱ እና መሰሎቻቸው መድረክ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መዘጋት ይኖርበታል።
  Enough is enough !

 2. በድሉ ዋቅጅራ ከመእልክትህ የወንጀለኞች ይፈለጋሉ ፎቶ እንዴት ቅብጭ ያለች የፖሊሲ ሰነድ ነች? እንደ ወስላታ አድር ባይ የትግራይን ህዝብ ከአህወአት እንለይ እያለ የሌለ ነገር ከሚፈተፍተዉ አክቲቪስትና አድር ባይ ፖለቲከኛ የተለየ ይዘት ያላት እዉነት ላይ የቆመች መልእክት ነዉ ለትግሬዎች ያስተላለፍከዉ። የትግሬ ህዝብ እጅና ጓንት ሁኖ ከህወአት ጋር መቆሙን መሸሸግ እኛንም እነሱንም ማሞኘት ነዉ ይልቀ በድርጊታቸዉ ተጸጽተዉ ኢትዮጵያዊ እንዲሆኑ ያልሆነ ዉሸከታችንን እናቁም። እንዲህ አይነቱ ሃሳብ አሁንም ሳይወዱ ኢትዮጵያዊ ልናደርጋቸዉ ስለሆነ ለነሱ እንተወዉ።

  ዶ/ር አብይን በተመለከተ ልክ እንደ መለስ ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ላይ ሊያደርግ ያሰበዉን ሊያደርግ ይፈልጋል። የማንነት ኮሚቴ ዉስጥ የሰገሰጋቸዉ ዋናወና መርዞችን ነዉ አረጋዊ በርሄም ሌንጮም አሉበት ብርሀኑና ሐይለ ማርያምም አይጠፉበትም። የሰዉየዉ ሀሳብ ባድሜን ለኤርትራ ሰጥቶ የአማራን ግዛት ለትግሬ ማባባያነት ሊያስመልስ ሳያስብ አልቀረም። አብይ የአማራ ጥላቻዉ ልክ የለዉም ያሁን አካሄዱ አሜሪካኖች የኢጣሊያ የኮሚኒስት ፓርቲ እንዳይጠናከር በሁለተኛዉ የአለም ጦርተን ማለቂያ ላይ ስልጣንና መንግስቱን ለማፊያ የሰጡት አይነት ዘዴ ነዉ።
  እንግዲህ ወንድማችን በድሉ ዋቅጅራ ነግሮሀል የአማራ ፋኖ ርስትህን በደምህ መልሰሀል ድሮም መንግስት ተብዬዉ ባይጫንህ ይህን ነገር ታዉቅበት ነበር አሁንም ተከዜ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ ገጥግጠህ ሰቅለህ የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙር መዘመር ነዉ ያለብህ። ለወደፊት ትግሬ አዘናግቶ እንዳያርድህ በንቃት መጠበቅ ነዉ።ባንድራቸዉንም ስርአታቸዉንም ለነሱ ተዉላቸዉ አንተ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊ ነህ የከፋፈሉህ እንሱ ናቸዉ ወደህ ሳይሆን።
  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

 3. @ከተማ
  በጣም በጣም ተሳስተሃል፤፤ ማንም የፈለገውን ሃሳብ ማራመድ መብቱ ነው፡፡ ነገር ግን ከህዝብ ዉሳኔ ዉጭ ማንም ይሁን ማን አቢይ አህመድን ጨምሮ በጉልበት የሚቀይረው አንድም ነገር አይኖርም፤፤ እትዮጵያ ከዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ በኋላ ሽግግር አድርጋ የምትድን ከሆነ ከነችግሮቹም ቢሆን ባላንስ ጠብቆ ሊሄድ የሚችለው መሪ ዶ/ር አቢይ አህመድ ይባላል፤፤ ቁርጡን ንገረኝ ካልክ ደግሞ፤ አቢይ ካልሆነ ኢትዮጵያ ልትቀጥል የምትችለው በመፈንቅለ መንግስት ወደ ሥልጣን በሚመጣ ሃይል ብቻ ነው፤፤ ለዛውም ጦሩ ራሱ በዘር ተከፋፍሎ ካልተጫረሰ፤፤ የህውህትን መሪዎች ማጥፋት እና የህወሃትን አስተሳሰብ ማጥፋት ይለያያሉ፤፤ “መተንተን” ከሆነ የያዝከው “የምትመኘውን” ሳይሆን “ሊሆን የሚችለውን (scenario) ” ነው ማሰብ ያለብህ፡፡ ትግስት ግበር!

 4. አይ ከድር ሰተቴ አብይ ከመጣ የተወለድክ ልጅ መሆን አለብህ ያለ ህዝብ ፍላጎት እያልክ ስትደክም አያለሁ። ህዝብ ይህ ድርጅት ይወክለኛል ብሎ ውክልናውን የሰጠው ድርጅት አንድ ትጠቅስልኛለህ? ኦነግ፣ህወአት፣ኢህአፓ፣….. ወይ ትምህርት የከበዳቸው እይታን የፈለጉ ወጣቶች ወይም ጫት አብዝተው በሚቅሙ ወጣቶች ስብስብ ወይም ደግሞ ፈረንጅ ኢትዮጵያን በትኑ ብሎ በላካቸው ወይም ደግሞ እዚህ አገር እንዲህ ተደርጓል እኛስ ለምን ይቅርብን በሚል እሳቤ ነው እንጅ ህዝብ ተሰብስቦ ውክልና የሰጠው አንድም ድርጅት አላየሁም። ዋቆ ጉምቱ እዳ ስለበዛበት ለዚያድ ባሬ አድሮ እንጅ የባሌ ገበሬዎች በደል አሳስቦት እንዳልሆነ ማስረጃ የመቆፈር አቅሙ ካለህ መረዳት ትችላለህ።
  በተረፈ ሁሉም ቀልድ ነው ጫት እየቃምክ ትወያያለህ ትርክቱን በሀሳብ ለተጎዳ ዜጋ ትሸጣለህ ቀጥሎ እንዳንተ ህዝቡ ህዝቡ የሚሉ ምስኪን ዜጎችን ትፈጥራለህ። አትጥፋ ወዳጄ የኢትያጵያን ትንሳኤ ያሳየን።

  • @ስመረ
   የአማራን ህዝብ አቢይ ላይ ተነሱ እያልክ ስትቀሰቅስ ከረምክ፤፤ እስቲ የአማራ ህዝብ ምን ያድረግ በግልጽ አስረዳን ብልህ በዛው ጠፋህ፤፤ በአንተ አነጋገር በግልጹ ቋንቋ “አማራ ሌላውን ውረርና አቢይን አባር” ማለትህ ነው፡፡ ከአባይ ወዲያ ማዶ ከሆንክ አሁንም እኔ የምለው በፍጹም ሊገባህ አይችልም፤፤ አልፈርድብህም! ጃዋርም እኮ የሳተው ይህንኑ አልኩህ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ መስተጋብር ያለመረዳት፤፡
   “የህዝብ ፍላጎት” ማለት በቅላል ቋንቋ “በዲሞክራሲአዊ መንገድ” ማለት ነው፤፡ ህዝብ ማንንም ወክለኝ አይልም፤፡ የሚመቸውን የፖለቲካ ሰብስብ እንዲመርጥ፡ ህገ መንግስትን በመሳሰሉ መሰረታዊ ጉዳዮች በሪፈረንደም መልክ እንዲሳተፍና ነጻ ሆኖ እንዲወስን ማድረግ ነው፡፤ አለቀ፤፤
   እኔ የምናገረው እንዲሆን የምፈልገውን የግል ምኞቴን አይደለም፤፤ በጉልበት ምነም ነገር እቀይራለሁ በልና ሞክር፤፤ አቢይን ንካና ሞክር፤፤ ለትጥለው የምትችለው በምርጫ ብቻ ነው፡፡ በፓርትይ ተደራጅ፡፡ “ኢትዮጵያ አትፈርስም ከፈረሰችም ከሌላው የበለጠ እንዎዳታለን፤ ከእኛ ወዲያ ኢትዮጵያዊነት ላሳር” በሚሉ ሰዎች ነው፡፤ ያንተ ዓይነት ማለት ነው፡፤ አቢይ ምንም ቢያደርግ ያንተን ዓይነት ሰዎች ማስደስት አይችልም፤፤ ከውስጥ የሚተናነቅህ ችግር አለብህ፡፡ መጀምሪያ እሱን አራግፍ፤፤

 5. ይህንን፡ወቅቱን የሚመጥንና ለዚህና ለዚያ ፈፅሞ ያላጋደለ ሚዛናዊ መልእክት ያደረሱትን ከተማ ዋቅጅራን አለማመስገን ንፉግነት ነው። ልብ ብሎ ለሚያስተውል ያለንባትን የገደል ጫፍ ለሚገነዘብና በቀጣይ አጭር ጊዜያት(ከህወአት ቀብር መልስ)ሳልስት ድረስ እንኳን በእነዚሀ ካንሰሮች ጦስ ያጣናቸዉን ዉድ ህይወቶች(ሲቪልና የታጠቁ)ቁጭ ብለን እርም ማውጫና መዘከሪያ ጊዜ ሳይኖረን ከጠ/ሚንስትሩ የማያሻማ ከሰበካ የፀዳና መጪ እጣፈንታችንን ቁርጣችንን የሚያሳውቁበት ፈታኝ የቤትስራቸውን ድንቅ አድርገው ነዉ ያስቀመጡላቸው። ጠ/ሚዉ በእርግጥ ልባዊ መካሪ ካላቸው ይህን ከዘመኑ የሀገራችን ክፉ ቫይረስ ከሆነው ሚዛኑን የሳተ ወገንተኝነት የፀዳ ምክር እንዲያነቡት ቢመክሯቸው ምኞቴ ነዉ።ችግሩ ሚዛናዊ፡በሳልና በክህሎት/በንባብና/በስራልምድና ተሞክሮ የበለፀጉ ሀገር ወዳድ ሰወችን ምክርና ውትወታ ጠ/ሚአብይ ዋጋ ሲሰጡና ሲቀበሉ አለማየቴ ነዉ። እንዲህ ያሉትን አገርወዳድ ኢትዮጵያዉያን በነፃ ያለምንም ክፍያና አመስግኑኝ እንኳን ሳይሉ ላገራቸዉ ይጠቅማል ያሉትን ሲሰነዝሩ አስተዉሎ ገንዘብ አለማድረጉ ዋጋ ቢያስከፍለንም እንዳገር ከዚህ የሚከፋው ደግሞ እሳቸው አማካሪ አድርገው በሀዝብ ገንዘብና ሌላው ሁሉ ጥቅማጥቅም ማዕረግ የሚሰጧቸው ሰዎች ማንነት:የኋላ ታሪክ:እውቀትና ከህሎት እንዲሁም በኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ አንድነት ላይ ያላቸው የተንሻፈፈ አመለካከት ጠ/ሚውን ከእንዲህ ያለው ወሳኝየሆነ ምክር የሚያገናኛቸዉ አይመስለኝም። ፈጣሪ ይሁናቸው/ይሁነነ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.