ጥቃት ከመፈጸሙ አንድ ቀን ቀደም በሎ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ እና ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በስልክ ተነጋግረው ነበር ተባለ

በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ አንድ ቀን ቀደም በሎ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ እና የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በስልክ ተነጋግረው ነበር ተባለ።

ይህን ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ትናንት ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

በጥቃቱ ዋዜማ የትግራይ ክልል መሪ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ደውለው ያሉ ጉዳዮችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚችሉ ገልጸውላቸው ነበር ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ተናግረዋል።

115329732 redwangettyimages 473536632ሁለቱ መሪዎች በነበራቸው ንግግር፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ አዲሱን የብር ኖት ወደ ትግራይ አንደሚልኩና የክልሉ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል እንደሚያደርጉ ቃል አንደገቡላቸው አምባሳደር ሬድዋን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ መሪዎቹ ከተነጋገሩ በሰዓታት ልዩነት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መድረሱን ነው አምባሳደር ሬድዋን የተናገሩት። ጥቃቱ በተለያዩ ስፍራዎች በተመሳሳይ ሰዓት መፈጸሙንም ጨምረው ገልጸዋል።

“ጥቃቱ በመቀሌ ቀላል ነበር ምክንያቱም ብዙ ወታደሮች አልነበሩንም። በሌሎች ቦታዎች ደግሞ ራሳቸውን ለማዳንና ነጻ ለማውጣት ሞክረዋል። መጀመሪያ ጥቃቱን በመከላከል እና ራሳቸውን በመጠበቅ በኋላም አንዳንዶች በማምለጥ ወደ ኤርትራ ድንበር ለመሻገር ችለዋል” ብለዋል።

እንደ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጻ በአንዳንድ ስፍራዎች የአገር መከላከያ አባላት ድጋፍ ሰጪ ኃይል ደርሶ እንሲከታደጋቸው ድረስ እስከ ሦስት ቀናት ድረስ ጥቃት ሲደርስባቸው ነበር።

የትግራይ ክልሉ መሪዎችም ከመከላከያ የወሰዷቸውን መሣሪያዎች መታጠቃቸውን እና ማንኛውንም አካል ለማጥቃት እንደሚችሉ ማንም ከመጣባቸው እስከመጨረሻው ለመዋጋት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል ብለዋል።

“የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ 300 ኪ.ሜ ርቀት ያለን ቦታ ሊመታ የሚችል ሮኬቶችን እና ሚሳኤሎችን መያዛቸውን ሲያስታውቅ እነሱ ግን ከ300 ኪሜ በላይ በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ድረስ አውሮፕላኖቻችን ሲነሱ እና ሲበሩ ሊመቷቸው እንደሚችሉ ተናግረዋል” ብለዋል።

“መከላከያ ሠራዊቱን አጥቅተዋል። መሣሪያውን ወስደው ራሳቸውን አስታጥቀዋል። የፌደራል መንግስቱን እና ዋና ከተማውን እንደሚያጠቁ አምነው በልበ ሙሉነት ተናግረዋል። ይህ ግጭቱን እንደጀመረ ያሳያል። ይህን አልደበቁም” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል አምባሳደር ሬደዋን።

“ዘመቻው አጭር እና ግልጽ ዓላማ ያለው ነው” ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፤ “ጉዳቶች አነስተኛ አንዲሆኑ እና ሠላማዊ ዜጎችን እንዲጠበቁም መንግሥት ይሠራል። እነዚህ ኃይሎች በያዙት መሳሪያ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እንዳይጠቀሙ የተመረጡ ዒላማዎች በቁጥጥር ስር ይውላሉ ወይም ይወድማሉ” ብለዋል።

ባለፉት ወራት በህወሓት እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ተደጋጋሚ ጥረት ተደርጎ ሳይሳካ መቅረቱን አምባሳደር ሬድዋን ተናግረዋል።

አምባሳደር ህወሓት ባለፉት ሁለት ዓመታት ህገ-መንግስቱን የሚጻረሩ በርካታ ህገ-ወጥ ድርጊቶች ሲፈጽም ቆይተዋል ያሉ ሲሆን፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመፈጸም ለድርድር የማይቀርብ ቀይ መስመርን ጥሷል ብለዋል።

በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት ሲፈጸም ግንኙነት እንዲቋረጥ ተደርጓል ያሉ ሲሆን መብራት እና ስልክ እንዲቋረጡ እንዲሁም መንገዶችም በህወሓት እንዲዘጉ ተደረገዋል ብለዋል።

“ዜናን ጨምሮ የተለያዩ መረጃ ሲልኩም ሆነ ሲፈልጉ የግንኙነት መስመሩን ይከፍታሉ” ያሉት አምባሳደር ሬድዋን በዚህ መንገድ መዝለቅ ስለማይችሉ በቅርቡ ይከፍቱታል ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል።

የአየር ጥቃት

በተከናወኑ የአየር ጥቃቶች የነዳጅ እና ጦር መሣሪያ ማከማቻዎች እየተመቱ መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን ገልጸዋል።

በደረሰባቸው ጥቃት ወደ ኤርትራ ሸሽተው የነበሩ ራሳቸውን በማደረጃት የማጥቃት ዘመቻውን ተቀላቅለው ወደ ኢትዮጵያ በመሻገር ሽራሮ አካባቢን ተቆጣጥረዋል፣ ያጡትን ቦታም ለመቆጣጠር ወደፊት እየገሰገሱ ነው ብለዋል አምባሳደር ሬድዋን።

“አዲስ አበባን እና ቢሾፍቱን የሚመታ 700 ኪሜ የሚሄድ ሚሳየል መንግሥትም የለውም። ካላቸው ያስታጠቃቸው አለ ማለት ነው። ይህ ብቻ በሃገር ከህደት የሚያስጠይቅ ነው። እንደቃላቸው ከሆነ ቢሾፍቱን እና አዲስ አበባን ማጥቃት ይችላሉ። ይህ ከሆነ የሚያስታጥቃቸው አለ ማለት ነው። ይህን ደግሞ ማስወገድ አለብን። ይህን ራሳቸው ናቸው የሚናገሩት። ይህ በራሱ መንግስት የሚወስደው እርምጃ ትክክለኛ ስለመሆኑ ማሳያ ነው” ብለዋል።

በሰው የደረሰ ጉዳት

በእስካሁኑ ጦርነት የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን አምባሰደር ሬድዋን ተናግረው “የመጀመሪያዎቹ የእኛ መከላከያ አባላት ናቸው” ብለዋል።

“እነሱ የመጀመሪያዎቹ ተጎጂዎች ናቸው። በተኩስ ምልልሱም የተሰዉ አሉ። በጦርነቱ ወቅትም በህወሓት በኩል የሞቱ አሉ። ለመናገርም ደስተኛ አይደለንም ብዙዎቹ ታዳጊዎች ናቸው። ሃላፊነት የሚሰማው ቤተሰብ አይደለም ሊያስታጥቃቸው የጦርነት ፊልም እንዲያዩ የማይፈቅድላቸው ታዳጊዎች ናቸው። ግንባራቸውን ለጥይት እንዲሰጡ ማድረጉ በራሱ ወንጀል ነው። እነሱን መግደል አያስደስትም ልጆቻችን ናቸው” ብለዋል።

መረጃዎች በሁሉም ቦታ ባለመገኘቱ ቁጥሩን መናገር እንደማይችሉ አስታውቀው በቀጣይ ጥቂት ቀናት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በኩል ያለውን እውነታ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል።

የድርድር ቅድመ ሁኔዎች

ለድርድር በሮች ዝግ አለመሆናቸውን የጠቆሙት አምበሳደር ሬድዋን ይህ ግን የሚሆነው የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ መሆኑን ጠቁመዋል።

በህወሓት እጅ የሚገኙ መሣሪያዎች ሲወድሙ ወይንም በቁጥጥር ስር ሲውሉ የፌደራል መንግሥቱ ያስቀመጠው የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ተናግረዋል።

አምባሳደር ሬድዋን በቁጥጥር ስር ያሉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለመንግሥት ተላልፈው ሲሰጡ፣ ህግ ሲከበር እና በህግ የሚፈለጉ ሰዎች ለህግ ሲቀርቡ መሆኑን ጠቁመዋል።

BBC

1 Comment

  1. Redwan Hussein should tell us the truth about the whereabouts if the 1.3 Billion Birrs which the National Bank of Ethiopia claimed to have misplaced it.

    If the whereabouts of the misplaced money is not known by the private security companies’ investigators , then the National Bank of Ethiopia should be used as detectives by the public having access to the serial numbers of the misplaced 1.3 Billion Birrs.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.