ስለ አማራ ልዩ ሀይል ጀብዱ የተሰጠ ምስክርነት: = ሲሳይ አልታሰብ

125428040 2766635163551841 251458235549591768 n ስለ አማራ ልዩ ሀይል ጀብዱ የተሰጠ ምስክርነት: = ሲሳይ አልታሰብ-ሀያ ሶስት ዓመታት በውጊያ ውስጥ ቆይቻለሁ። እነዚህን የመሰሉ ተዋጊዎች ግን አጋጥሞኝ አያውቅም። ክላሽንኮቭ ቁመው እንደስናይፐር ይተኩሳሉ ። ከኢላማቸው ውጭ የመቱ ወታደሮች አላየሁም ። የውጊያ ቀጠናቸው ከፊት ለፊቱ ግንባር በግራና በቀኝ ክንፍ ቢሆንም በፍጥነት ስለሚያጠቁ የመሃል ግባሩን ጭምር እነሱ ይሸፍኑት ነበር።

-ሌላው አስገራሚ ባህሪያቸው እጅግ ፈጣን ተዋጊዎች መሆናቸው ነው። ሶስት ቀናት ይፈጃሉ ተብለው የተገመቱትን ከሁመራ በስተ ምዕራብ እና በስተደቡብ ምዕራብ የሚገኙትን አራት ጠቃሚ ወታደራዊ ቦታዎችን በሰባት ስዓታት ብቻ የወገን ጦር ሊቆጣጠር የቻለው በእነሱ ታምራዊ የውጊያ ስልት ነበር።

– ከኤርትራውያን ጋር በዛላንበሳ እና በቡሬ ግንባር ተዋግቻለሁ። ከትግሬዎቹ ጋር አሁን የግንባር ጦርነት ውስጥ ገብተናል። ሁለቱም በፊት ለፊት ጦርነት ብዙም ባይሆኑ በደፈጣና በቆረጣ ውጊያ ድንቆች ናቸው ።
ዐማሮቹ ግን በሁሉም የውጊያ ዓይነቶች ፍጹም ተወዳዳሪ የላቸውም።

-አስቸጋሪ ይሆናሉ ተብለው በተገመቱ ግንባሮች ለመሰለፍ አያመንቱም። እንደውም ጀብዱ ለመፈፀም ካላቸው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ የጠላት ጦር ይበረታባቸዋል የተባሉትን ምሽጎች ለመደርመስ ይሽቀዳደማሉ። ጦርነቱ ጋብ ሲል ወደ ማታ የሰው ኃይል ስምሪትና ድልድል ቆጠራ ስናደርግ ከእነሱ ወገን ጥቂትም ቢሆን የጎደለ የለም። ወታደራዊ ስልጠና ብቻውን እንዲህ አያደርግም ከትውልድ የሚተላለፍ አንዳች ድፍረትና ብልሃት ቢኖር እንጅ ብየ አስባለሁ።

-ስለ ዐማራ ልዩ ኃይል እና ስለ ዐማሮቹ ጀግንነት የምገልፅበት ቃላት ባይኖረኘም በቻልኩት አቅምና ባገኘውት አጋጣሚ ለሁሉም ከምንመሰክረው የጦር ሜዳ ውሎየና ከወታደር ታሪኬ አንዱ ይሄው ነው። ኢትዮጵያ ከሁለት ሽህ ዓመታት በላይ ታፍራና ተከብራ የኖረችበት አንዱ ሚስጥር ይሄው ነው።
*
በወልቃይት ሁመራ ግንባር ከዐማራ ልዩ ኃይል ና ሚሊሻ ጋር የተሰለፈ የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጅ የመከላከያ መኮንን ስለ ዐማራ ልዩ ኃይል ጀግንነት ከሰጠው የዓይን ምስክርነት
===

5 Comments

 1. የአማራ ጀብዱ ሳይታለም የተፈታ ነወ። ታሪክም ይመሰክራል። እነ በላይ ዘለቀን ያፈራ። ድሮም በጨካ ጦርነት ስለሚያውቁ የህወአት መሪያቸው መለስ አማራ ቀና ያለ ቀን ወየውላችሁ ይል ነበር ጊዜው ደረሰ አሁን። እውነት ለመናገር ለትዕግስት፣ ለማመዛዘን፣ ለፍቅርና ላለመቸኮል ማን እንደአማራ አለ። ማንስ እንደሱ የተጨቆነ አለ? በችግርስ የሚኖር ማንስ እንደሱ አለ። በተበተበ የህዋአት አገዛዝ ይበልጡኑ የተጎዳ አማራ ነው። ኢትዬጵያን በይበልጥ ከአገር ወዳድ ጋር የሚያስቀጥልም እሱ ነው።
  ድል የኢትዬጵያ።

 2. “ሲሳይ አልታሰብ” የት ሆኖ ነው የምስክርነት ቃሉን እየሰጠ ያለው?
  DC ሆኖ ወይንስ ዓዲ ኣርቃይ(ዓደርቃይ)፣ ዓደርቃይ ሆኖ ከሆነ፣ ግንባር ፊት ላይ በመሆን እንደ ናፖልዮን ፊውዳሊዝምን ለመገርሰስ ሰራዊቱን እየመራ ነው ማለት ነው፣ DC ውስጥ ሆኖ ከሆነ ግን ልክ ሂትለር የበርሊን ቡንከሩ ውስጥ ተደብቆ የ15 ዓመት እድሜ ያላቸውን ህፃናትን ወደ ጦር ግንባሩ ይልክ እንደነበረው አይነት Feige ተግባር ነው! DC ውስጥ ሆናችሁ ቀረርቶ ሽለላን ባበዛችሁ ቁጥር ኢትዮጵያ ወደ ሁቱዝም እየወረደች ነውና ለ1000ኛው ጊዜ መልእክታችን ይድረሳችሁና ልብ ትገዙ ዘንዳ አስቡበት……..!!!

 3. አሁን ማን ይሙት ይህ ወሬ ሆኖ ይወራል? ወንድም ወንድሙን ገድሎ የሚፎልልበት የእብዶች ምድር። አማራ ትግራይ ወያኔ ሻቢያ ኦሮሞ ገለ መሌ እየተባባሉ መሞሻለቅ ጀግንነት አይደለም። የግድ ሆንም እንኳን ውጊያ ቢቀና የሚፎከርበት ጉዳይ አይደለም። መቸም የጦርነት የመጀመሪያ ሟች እውነት ናትና እንሆ በየቀኑ እየሞተች ትገኛለች። ከሶፋቸው ተቀምጠው ሁልጊዜም ሃበሳ የሚያየውን ህዝብ በሉ አይዞአችሁ የሚሉ ከማህጸንዋ የወጡት ልጆቿ ብቻ ሳይሆኑ ቅጥር ነጭና የአረብ ዜጎችም ናቸው። ሄርማን ኮሆን እና ሚስተር ፕላት የውሸት ወሬ ሲያናፍሱ ማየት ልብ ይጎዳል። የፈረንሳይ የዜና አገልግሎት ሌሎችም የቆየ ቪዲዪ እያሳዪ ለአለም ይህ ሆነ ያ ሆነ ሲሉ ያስተዛዝባል። ሄርማን ኮኽን የት ነበር ሁለት ሚሊዪን አማሮች የት እንደገቡ የወያኔ መንግሥት አላውቅም ሲል? ግን ከድሃው ህዝብ እየተነጠቀ በላቢ ስም የሚከፈለው የደም ገንዘብ የሚያስለፈልፈው እንጂ እውነትን ያውቃትም።
  አሁን ጎንደርን ባህርዳርንና አስመራ መታሁ እያለ በራሱ አፍ የሚለፈልፈው ወያኔ ሞት ላይ ስለሆነ ውጊያው እነርሱ እንዳልጀመሩት ሁሉ የአለም ህዝብን ድረሱልን ለማለት የሚለኩስት እሳት እንጂ አብቅቶላቸዋል። ያኔ ነበር ተው ሲባሉ ሲመከሩ መስማት። አሁን ወደ ሱዳን የሚጎርፈው ህዝብ አሜሪካ እሻገራለሁ ሌላው የአለም ሃገር ይቀበለኛል ብሎ ከሆነ አፍንጫችሁን ላሱ እንደሚባሉ ሊያውቁት ይገባል። የጥቁር ህዝብ ፍልሰት በነጩ አለም ተጠልቷል። ትላንት ዛሬ አይደለምና! ወያኔ ግን ወደ ሱዳን እንዲወጡ የሚያደርጋቸው ለራሱ አላማ ነው። በዚያው ተደራጅቶ ሲገድልና ሲያጋድል ለመኖር። ያኔ በደርግ ግዜም ያደረጉት ይህ ነው። ደርግ ሰፈራ እያለ ሲያፍስ እነርሱ ደግሞ ቀሪውን ህዝብ አጣድፈው ሱዳን በማሻገር እልፍ ሰዎች በበሽታ እረግፈዋል። አሁን የምናየውም ያንኑ ነው። ሁሉ ነገር በሃገር ላይ ሲሆን ያምራል። ሌላው ሁሉ ከንቱ ነው። ወያኔ ደጀን የሚሆኑትን ነው ሃገር ለቀው እንዲወጡ ከባድ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ያሉት። ዞሮ ተመልሶ በአረብና በሌሎች እየታገዘ ደም ለማፍሰስ፤ የመገናኛና የሃይል አውታሮችን ለማውደም ሊጠቀምባቸው ነው። ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ገዶት አያውቅም።
  አሁን የአረብ ኤሜሬት ድሮኖች ደበደቡኝ፤ አስመራን መታን የሚሉት ከኢራን ወይም ከቱርክ ወይም ከሌላ ድጋፍ ለማግኘትና እሳት ለማንደድ እንጂ እውነትነት የለውም። ኤርትራዊያን በአንድ ቀን መቀሌ መግባት ይችላሉ። ያኔም በባድመ (በሃብት ክፍፍል) ላይ ሲጣሉ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባይዋጋላቸው ኑሮ ወያኔ ዛሬ አፈር ውስጥ ነበረች። ትላንት የገደለው ሲገደል፤ ተረፈ ከሞት ተብሎ ጡረታ የወጣው ና ተብሎ ሲሞት ምን አይነት የእብድ ሃገር ነው ያለ ጠበንጃ ሌላ ነገር የማያስብ? አይበቃም የእስከዛሬው መገዳደል? ግን በወንድሙና በእህቱ ሬሳ ላይ የሚዘፈን በድን በሞላበት ምድር አሞራና አውሬ እንጂ ሰው ጠግቦ ማደር አይችልም። ሁልጊዜ ኡኡታ፤ ሁልጊዜ ስደት፤ ድረሱልኝ አድኑኝ መቼ ነው በራሳችን አሰብን በራሳችን ቆመን በሰውኛ ቋንቋ ተግባብተን መኖር የምንጀምረው? እናማ ከላይ ያለውም የጀብድ ታሪክና ቀረርቶና ሽለላ ለዘመኑ የማይመጥን፤ ኋላ ቀር፤ የጊዜውን የወታደራዊ ልቀትና የውጊያ ስልት ያላገናዘበ በመሆኑ እንደ ገድል ሊወራ አይችልም። ከውጭ ጠላት ጋር እኮ አይደለም ውጊያው። ከወገን ጋር እንጂ! እናስተውል! በቃኝ!

 4. “ኤርትራዊያን በአንድ ቀን መቀሌ መግባት ይችላሉ። ያኔም በባድመ (በሃብት ክፍፍል) ላይ ሲጣሉ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባይዋጋላቸው ኑሮ ወያኔ ዛሬ አፈር ውስጥ ነበረች። ”
  እንዲህም አድርጎ የለ ሽንፍላው ያልጠራ መሃከላቸውም ገባሁበት ባይ አላ-ቻልኩበት…………………!
  “ወዳጄ” ተስፉኒ፣ የዓፋቤት፣ የባፅዕ ወይንስ የታላቁ ሽረ-ህንድ ውቅያኖስ ኪይናት (ጦር ድምሰሳ) ትርፍራፊ የደርግ ወታደር ነህን….! ወይንስ ባሁኑ ጊዜ ዓደርቃይ የጦር ግንባር ዘንዳ እየተገኘህ ነውን…………….! ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው………….! እነ በርሀ “ሻዕቢያ” ካሉበት ሆነው እንዳሰሙህ ብቻ………….!

  ነናይ ዓቕምኽን ሕለማ………….!

  • ወዳጄ ዘ-ያዕቆብ – እንደ ወያኔ የፈጠራ ታሪክ ያለ ወያኔ ጀግና የለም። ሂድና ከበሮህንና ክራርህን እየመታህ በወገንህ ሬሳ ላይ ዝፈን። እኔ ወንድምና እህቱን ገድሎ የሚፎክር አክ እንትፍ ካልኩት ቆየሁ። ሻብያ የወያኔ ጌታ ነው። ያሰለጠነው፤ ያስታጠቀው፤ የዘር መርዝ የጋተው የወያኔ የነፍስ አባት ሻቢያ ነው። ደርግ የፈራረሰው ራሱን አቁስሎ፤ የሃገሪቱን ምርጥ ልጆች ረሽኖ በባዶ ሜዳ ጡርንባ ሲነፋ ነፋስ ገብቶበት ነው። ከወያኔና ከሻቢያ ውጊያ ጋር ምንም አያያይዘውም። በዚህ ላይ የአለም የፓለቲካ ንፋስ አቅጣጫ ሲለውጥ ጭራሹኑ ደርግ ተፍረከረከ። ቁም ነገሩ የጀንነት ጉዳይ አይደለም። ሻቢያም ወያኔም ደርግም አረመኔዎች ናቸው። ለውጡን አንተ ንገረን። እርግጥ ነው የባድመው ውጊያ የሃብት ክፍፍል ጦርነት እንጂ ባድመ ድባ የማያበቅል የድንጋይ ክምር ምድር ነው። እስቲ ንገረን አንተ ጉራህን የምትነዛው? የወገን ስቃይ፤ እንባ፤ የማይገዳቸው ሙቶች ሃገር ይዘው ይሞታሉ። ያኔ ሻቢያ በትግራይ ጥቃት ሲከፍት የመከቱትን ልጆች ነው የፍጥኝ አስረው በጥይት የደበደቧቸው። አለም ሁሉ ወያኔና ወያኔ አፍቃሪዎች ምን ያህል ጨካኞች እንደሆኑ ይህ ግጭት አሳይቷል። ትርፍራፊ የደርግ ወታደር ያልከው ነው በሻቢያ ከመገረፍ ያዳነህ። አሁን ደግሞ አንተው በለኮስከው እሳት ትለበለባለሁ። ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው። በጭራሽ የሚታመን ነገር የላቸውም። ለትርፋቸው እናታቸውን ገቢያ አውጥተው ይሸጣሉ። ታሪካቸው የሚነግረን ይህ ነው። ሌላው ሁሉ ጉራና ቀረርቶ ፉርሽ ነው። አንተም ዝም በል። እኔም ዝም እላለሁ። ምድሪቱ የደም አፍሳሾችና የዘራፊዎች መሆኗ የሚያበቃው ግን መቼ ነው?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.