የድል ዜና ከራያ ዋጃ ጥሙጋ፣ አላማጣ‼️ – ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ!!

የመከላከያ ሰራዊትና እና የአማራ ልዩ ኃይል አየር ማረፊያ ሰፈር የተባለውን አካባቢ እና ዋጃ ጥሙጋን የተቆጣጠረ ሲሆን አሁን ላይ መሆኔ የተባለውን አካባቢ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ውጊያ ላይ ይገኛል።

125209027 4676421022430067 884567590879831797 nየኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ኃይል ራያ አላማጣን ከከሃዲው የትህነግ ቡድን ለማስለቀቅ በነበረው ውጊያ ከተያዙ ቦታዎች ባሻገር ቁጥራቸው በርከት ያለ የትህነግ ልዩ ኃይልና ሚሊሻዎች ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ በሌላ በኩል እድል የቀናው የትህነግ ሰራዊት እግሬ አውጭኝ ብሎ እየፈረጠጠ ነው። ቁጥሩ ቀላል የማይባል የትህነግ ሰራዊት ደግሞ ለመከላከያ እና ለአማራ ልዩ ኃይል እጃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

በስፍራው ያገኘናቸው የራያ ዋጃ ጥሙጋ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለፁት ከዚህ ቀደም ጨቋኙና ጨፍጫፊው የትህነግ ቡድን ከፍተኛ ጭቆና ሲደርስባቸው እንደነበር ገልፀው አሁን ላይ የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፖሊስ እና የሚሊሻ ኃይሉ ባንዳውን ቡድን አባሮ እኛን ነፃ አውጥተውናል ብለዋል።

125199573 4676421822429987 123896957786887549 n 125183440 4676421569096679 5254312256821418038 n 125351887 4676421402430029 8858459549088122882 n

አሁን ላይ የራያ የዋጃ ጥሙጋ ከተማ ነዋሪዎች ከከሃዲው እና ጨፍጫፊው የትህነግ ቡድን ነፃ በመውጣታቸው በራያ ባህላዊ ጭፈራ ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

ራያ አላማጣ መሆኒ ማይጨው እያለ ይቀጥላል‼️

ድል ለሰራዊቱ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.