በትግራይ ክልል ሕግን ለማስከበር እየተወሰደ ስላለው እርምጃ ፣

zegaNovember 12, 2020

በማንኛውም ሀገር መንግሥት የሕዝቡን ሰላም መጠበቅና የሕግ ማስከበር ተግባሮቹ ተቀዳሚ ኃላፊነቱ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ሆኖም ላለፉት ሁለት ዓመታት የብሔርና ሃይማኖት ተኮር ወንጀሎች በተለያዩ ክልሎች በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ መንግሥት ኃላፍነቱን በሚገባ አልተወጣም የሚሉ ወቀሳዎች ከሕዝብ ሲቀርቡ ቆይተዋል፡፡

አንዳንድ የትግራይ ክልል መሪዎች በሠሩት ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ለፍርድ እንዲቀርቡ መጥሪያ ቢሰጣቸውም እስከ አሁን በእምቢተኝነት ቆይተዋል። አልፎ ተርፎም በሀገራችን የብሄር ግጭቶች እንዲፈጠሩና አለመረጋጋት እንዲፈጠር በቀጠሯቸው የጥፋት ኅይሎች አማካኝነት ሲያስፈጽሙ በማስረጃ እየተያዙ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በእነዚሁ መሪወች አማካኝነት በሀገር መክላክያ ሠራዊት ላይ አሰቃቂ ግድያዎች ፈጽመዋል፡፡ ይህ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ሃገራዊ ክህደት ነው። መንግሥት በአሁኑ ጊዜ ወንጀለኞቹን ከሕግ ፊት ለማቅረብ እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደግፋለን፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብም ድጋፉን እየሰጠ ይገኛል፡፡

ካሁን ቀደም እንደገለፅነው፣ አሁን በትግራይ ክልል አመራሮች ላይ የሚካሄደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ በጥሞናና በጥንቃቄ እንዲከናወን፣

  • መንግሥት ጥፋተኞችን ለሕግ ለማቅረብ በሚያደርገው ዘመቻ ሰላማዊ ሕዝቡ እንዳይጎዳ እስካሁን እያደረገ ያለውን ጥንቃቄ እያደነቅን ለወደፊቱም በዚሁ እንዲቀጥል እናበረታታለን፡፡
  • አንደኛው የችግሩ ምንጭ በየክልሉ የተዋቀረው አላስፈላጊ ‘ልዩ ኅይል’ መሆኑ ታውቆ የየክልሉ “ልዩ ኃይሎች” ከመክላከያ ሠራዊትና ከፌደራል ፖሊስ ውስጥ እንዲጠቃለሉ የሚያስችል እርምጃ ባስቸኳይ እንዲወሰድ እናሳስባለን፡፡
  • የሃይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግሌወች፣ አባገዳዎች፣ የሲቪል ማኅበራትና የሜድያ ኃላፊዎች ሁሉም ለሰላምና ለሕግ መክበር ተከታዮቻቸውን እንዲያስተምሩ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡
  • በኅብረተስባችን መሀከል እስከአሁን የመከፋፈል፤ የእርስ በርስ ጦርነትና ጥላቻን በከፍተኛ ደረጃ እንዲስፋፋ የሚያደርገው በሌሎች ሀገሮች ታይቶ የማይታወቀው በኅዋሀት፤ በዚሁ ወንጀለኛ ቡድን፤ የተቀነባበረው ዘርና ቋንቋን መሠረት ያደረገ የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት መሆኑ ታውቆ በአስቸኳይ እንዲታረም ወይም በአዲስ መልክ እንዲዘጋጅ እንዲደረግ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡

 

ኢትዮጵያ በነፃነቷና ባንድነቷ ተከብራ ለዘላለም ትኑር!

ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ

An international and independent rights-based civic movement

 

1 Comment

  1. ግን ታድያ “በ’HUTUSIM” ዜቤ ነው እንዴ? ኢትዮጵያ ውስጥም እንደዚህ አይነት BARBARISM ሊካሄድ ይችላል ብዬ አልገመትኩም ነበር፣ በክፉኛ በሃፍሬት ለሃፍሬት ተሸፍኘ ተደብቄ እገኛለሁኝ…………………………..!!!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.