ጠ/ሚ ዐቢይ የምዕራቡ የትግራይ ክልል ቀጠና ነጻ መውጣቱን አስታወቁ

125250907 3520021838088530 5101898156027565519 n
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሃገር መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ የምዕራቡ የትግራይ ክልል ቀጠና ነጻ መውጣቱን አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በዚያ ቀጠና ሠራዊቱ ሰብአዊ እርዳታና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰው ነጻ ባወጣቸው አካባቢዎች ሕዝቡን እየመገበ፣ እያከመና እየተንከባከበ ነው ብለዋል፡፡
ለስግብግቡ ጁንታ ግፍ እስትንፋሱ፣ ጭካኔ ነፍሱ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ሽራሮን ሲቆጣጠር፣ እጅና እግራቸውን የፊጥኝ ታሥረው የተረሸኑ የመከላከያ አባላትን ማግኘቱን ገልጸዋል፡፡
ጭካኔው ልብ ሰባሪ እንደነበር በማውሳትም ዓላማው ኢትዮጵያን መስበር እንደሆነም አንስተዋል፡፡
በፅሁፋቸው ኢትዮጵያ ከአልማዝ የጠነከረች መሆኗን አላወቁም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ የጁንታው ዓላማ ሠራዊቱንና ሕዝቡን አስቆጥቶ ለበቀል እርምጃ ማነሣሣት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያም ልበ ሰፊ ሕዝብና ሠራዊት አላትም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
በየቦታው ከዚህ የከፋ ጭካኔና ግፍ ሊያጋጥም እንደሚችል በመጥቀስም የአሁኑ ግን ለዚህ ጁንታ የመጨረሻው መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
ጥንቃቄው ሙት ይዞ እንዳይሞት በመሆኑ፥ በመፍጠን የተረፉትን መታደግና ግፍ የተፈጸመባቸውንም ለዓለም ለማጋለጥ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል ግጭት ‘አንገታችንን አስደፍቶናል’ አሉ

1 Comment

  1. የአሜሪካ ዜግነት አላቸው እየተባለ ያለው የትህነግ ወንበዴዎች አሜሪካ ጣልቃ ገብታ ሳይጠየቁ እንዲወጡ ከተደረገ ይህ ስራ በአለም አቀፍ ወንጀለኞችን የመተባበር መሰሪ ተግባር እና እራሷ አሜሪካንን ወንጀለኛ ሊያደርግ ስለሚችል መንግስት እዚህ ላይ ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡አሜሪካ የወንጀለኞች መሸሸጊያ መሆን የለባትም፡፡ እውነት ከሆነ በአይሮፕላኑ ላይ እርምጃ እስከመውስድ እንደሚደረስ ማስጠንቀቅ ይገባል፡፡ እንደውም ለአለም ቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ሊጠየቁ እንደሚችሉ ዲፕሎማቶችና የህግ ሰዎች ክሱን በተፋጠነ ሁኔታ ማስተላለፍ አለባቸው፡፡

    If America withdraw those TPLF junta groups (with dual citizenship), USA will be liable for those criminals who committed genocide, mass murderer and so many crimes. Ethiopia shall stand by objecting this and it has to be immediately sued their charge on International Criminal Court. This is a sabotage Ethiopia Government shall reject at any expense.
    Long live to Ethiopia!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.