የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ የተጠረጠሩ 7 የጄኔራል መኮንኖች ፍርድ ቤት ቀረቡ

tplf 300x287 1የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ገብረመድህን ፍቃዱን ጨምሮ ሃገርን በመክዳት ወንጀልና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመናድ በማሰብ ወንጀል የተጠረጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ገብረመድህን ፍቃዱ፣ የመከላከያ ሰራዊት ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይርዳው ገብረመድህን፣ የደቡብ ዕዝ ሰው ኃብት ልማት አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ገብረዮኃንስ ሳርሲኒዮስ፣ የሰሜን ዕዝ መረጃ ዘርፍ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ኢንሱ ኢጳጆ ረሾን ጨምሮ ሰባት ሀገርን በመክዳት ወንጀልና ህገመንግስትና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ ማሰብ ወንጀል በቁጥጥር ስር ውለው በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡
የፌደራል ፖሊስም ተጠርጣሪዎቹ መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት ወደጎን በመተው መቀመጫውን ትግራይ ክልል ካደረገ የፀረ ሰላም ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል በመከላከያ ጦር ውስጥ ሴሎችን በማደራጀት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የሀገር መከላከያ የሰሜን ዕዝ ሬዲዮ ግንኙነት ማቋረጣቸውን ገልጿል፡፡
በዚህም ሰራዊቱ እርስ በርስ እንዳይገናኝና እንዳይቀላቀል፤ በጦሩ ላይም የሞት፣ የአካል ጉዳትና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ እንዲፈፀም አድርገዋልም ነው ያለው፡፡
እንዲሁም በሀገር ውስጥና ከውጭ የሚቃጣበትን ጥቃት እንዳይከላከልና የሰሜን ዕዝ ጦር እንዲፈርስ በማድረግ በተቀናጀ መልኩ ኦነግ ሸኔ ከተባለና ከሌሎች የፀረ ሰላም ሃይሎች ጋር በመተባበር በተለያዩ ክልሎችም ሐይማኖትን ሽፋን አድርገው የብሄር ግጭት በማስነሳትም ሀገርን ለመበተን ሲሰሩ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ ገልጿል፡፡
ፍርድ ቤቱም የወንጀሉን ክብደትና በሀገር ደህንነት ላይ ከባድ ጉዳት የሚያደርስ ወንጀል መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ለፖሊስ 14 የምርመራ ቀን ፈቅዷል፡፡
በታሪክ አዱኛ
ኤፍ ቢ ሲ

4 Comments

  1. በክህደት የተያዙ መከላከያ ስሰራዊት አባላት መቅረብ ያለባቸው በወታደራዊ /ጦር ፍርድ ቤት እንጁ በመደበኛ ፍርድ ቀርቦ ሲጉዋተት ማየት የኢትዬጵያ ህዝብ ሊታገሰው አይገባም። ወያኔ ደርጎችን የዳንኘው በልዩ ፍርድ ቤት መሆኑ ይታወሳል።

  2. አይ አብይ አህመድ አረ አሁን እንኳን ቀልዱን ተወዉ ኦነግና ህወአት በሀገር መከላከያ ላይና በአማራዉ ላይ ባደረሱት በደል መደበኛ ፍርድ ቤት ነዉ መቅረብ የሚገባቸዉ።? መሸሸግ የማይቻልህ ሁኖ ነዉ ወደ ሲቪል ፍርድ ቤት ያቀረብካቸዉ? አባዱላን ለማዳን እንዳደረግኸዉ ወንጀለኛ ጓዶችህ ላይ መጨከን አቅቶህ ነዉ ማለት ነዉ?
    እነዚህ ሰዎች የጦር ሰዎች ሁነዉ በሀገር መከላከያና በገዛ ጓዳቸዉ ላይ ለፈጸሙት ስራ ባስቸኳይ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀርበዉ የመጨረሻዉ ቅጣት ሊሰጣቸዉ ይገባል እስከዛሬ የተደረገዉን የአማራ ጭፍጨፋ በዚያ ስትገፋዉ በዚህ ስትገፋዉ ግፍ ግፍን እየወለደ ቀድሞ ጠብቆ ይዞኸል። ለወንጀለኛ ያለህ ክብርና ጥበቃ ይህ ነዉ ተብሎ ሊገለጽ አይቻልም። ህወአት ያለ ደብረጽዮን አባይጸሀይ ስብሀት ነጋ….. እንዴት ነዉ ህወአት የሚሆነዉ ጁንታ የምትለዉን ቀልድህንና ድብቅ ሂሳብህን ትተህ ህወአትና ኦነግን በዘር ማጥፋት በሀገር ክህደት ፈርጀህ የሚገባዉን ቅጣት አሰጥልን ይህን ባታደርግ አምነዋለሁ ብለህ የምትቀለድበት አምላክ የስራህን ይሰጥሀል። ዛሬ ታብየህ ወንጀለኛን ከፍርድ ልታስመልጥ ትችላለህ ነገ ግን እነሱም ከዚህ ማምለጥ እንዳልቻሉ ሁሉ አንተም የጥፋትህ ስበት ከዚህ በባሰ ያመጣብሀል እመነን።

  3. የሚገርመዉ ከማንም በላይ በዚህ ወንጀል ሊጠየቅ የሚገባዉ አብይ አህመድና አስተዳደሩ ነዉ ከጥቃቱ ቀደም ብሎ ከደብረ ጽዮን ጋር በመነጋገር ለወንጀላቸዉ ማስፈጸሚያ 1.3 ቢሊዮን ብር ልኮላቸዋል። አዲስ አበባ የሰበካ ወሬዉን ሲነዛ በትግራይ ስላለዉ ሁኔታ ምንም ኢንፎርሜሺን አልነበረዉም ባጠቃላይ ለመምራት ብቃት ያለዉ ሰዉ ሁኖ ባለመገኘቱና የአካባቢዉን ፖለቲካ ኢሳይያስ እግር ስር ቁጭ ብሎ የሞተ ፖለቲካ ተሸካሚ በመሆኑ ሰሞኑን በደረሰዉ ጥፋት ከትግሬ ወንጀለኞች ጋር አብሮ የጦር ፍርድ ቤት ሊቀርብ ይገባል። ከዚህም በላይ በትግሬዎች የተወሰደዉን የአማራን መሬት ወኔ አጥቶ ዉሳኔ መስጠት ቸግሮች አሁንም ትግሬዎችን ለማለዘብ የአማራዉን መሬት አሳልፎ የመስጠት አዝማሚያ በማሳየቱ ይህ ግለሰብ አንድ ሊባል ይገባል።
    አማካሪዎቹ አርከበ እቁባይ ሌንጮ ለታ/ባቲ አረጋዊ በርሄ ብርሀኑ ነጋ አንዳርጋቸዉ ጽጌ የመሳሰሉ ሙታኖች በመሆናቸዉ ወደፊትም ከዚህ ሰዉዬ ብዙ ነገር መጠበቅ ስለማይቻል ወገን አገሩን ነቅቶ መጠበቅ ይገባዋል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.