ከንፈር እና ደም መምጠጥ ምን እና ምን ናቸዉ! – ማላጂ

እንዳለመታደል ሆኖ እኛ ኢትዮጵያዉያን ካለፈዉ ታሪካችን በጎ ነገር በመዉሰድ መማር እና ማስቀጠል ተስኖን የመከራ እና በደል ፅዋ ደጋግመን እየተጋትን እንገኛለን ፡፡

ከ1960’ዎች መባቻ ጀምሮ በነፋስ አመጣሽ እና ሀሰተኛ ትርክት ገፀባህሪ የተላበሰ የብሄር ጭቆና ሽፋን ደም ማፍሰስ፣ የሠዉ ልጅ ክቡር ህይዎት በማጥፋት እና በማጣፋት የተጀመረዉ የአገር ክህደት ሠዎ ጠል ኃይል (ቡድን) ያጎነቆለዉ እና ያጎመራዉ ያን ጊዜ ነዉ ፡፡

1280px Ethiopia 1991 1995.svg

ዛሬ ላይ አዲስ የሚባል በህዝብ እና አገር ላይ የተከሰተ ክህደት የለም ፡፡ ይኸዉም ያኔም ህዝብ መሃል ከተማ ቁጭ ብለዉ ግራ እና ቀኝ ለማያዉቀዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ እሳት ጭድ እያቀበሉ አገር እና ህዝብ ለማጥፋት በትጋት ይሰሩ የነበሩት ዛሬም ዳግመኛ በነጻነት ትግል ስም እየደገሙት መገኘታቸዉ ልማድ ሲደጋገም አመል ሆነ እንጅ በምግባርም በተግባርም የተለየ ነገር አላየንም  ፡፡

አመል ያወጣል ከመሃል  እንዲሉ በድሀዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ደም እና ህይወት የስልጣን ጥም ለማርካት ጥፋት እና ሞት የሚመኙለት ልማዳቸዉ በሠራዊት ላይ ማሳየታቸዉ ለኢትዮጵያ እና ህዝቦች ብሎም ለሠዉ ልጅ ያላቸዉ ጥላቻ እና ንቀት ነፀብራቅ ነዉ ፡፡

ይህ የበታችነት  እና ጥላቻ  ትኩሳት ከብሄር ብሄረሰብ የማታገያ ስልት (manifesto) የሚነሳ ፈዉስ አልባ ደዌ ስር ሰዶ ወደ ነጻነት ትግል  ከዚያም ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ለክፉ ቀን ተብሎ በይደር የቆየ የጥፋት እና ሞት ጋሻ እንደገና ከመጋቢት 24፣2010 ዓ.ም ጀምሮ ከወደቀበት ተነስቶ ይኸዉ ዳግም የበታችነት እና የጥላቻ ባርነት ደዌ አገርሽቶ አገር እና ህዝብ እያዳረሰ ነዉ ፡፡ ሆኖም ደም ተቀብቶ ደም አይፈራም እና ያረጀ እና ያፈጀ ነገርን በመደጋገም ጊዜ አጥፍተን ለዳግም ጥፋት ጊዜ ሳንገዛ ከኋላ ታሪክ በመማር ክፉን ከነክፋት ሰንኮፍ በመንቀል ዳግም እንዳያንሰራራ ደርቆ አስኪቃጠል የሚደረገዉን ተጋድሎ ከእርስ በርስ ግጭት እና የአገር አንድነት ስጋት ጋር ማያያዝ ከንፈር እና ደም ከመምጠጥ ያለፈ ከንቱ ድካም ነዉ ፡፡

ዛሬ የአዞ እንባ የሚያነቡት ትናንት እና ለዓመታት የዘለቀ የዜጎች ሞት፣ ስደት እና ዉርደት ምንም ስሜት እና ትኩረት ያልሰጣቸዉ ለዘመናት በአገር እና ህዝብ ዉድቀት ላይ የስልጣን ፍላጎት ለመጫን ከህዝብ እና አገር በላይ በማን አለብኝነት ግፍ እና ሴራ ሲፈፅም የነበር ህዉሃት /ኢህአዴግ  የጀመረዉን ጦርነት እና ለዚህ ለሚደረግ አጸፋ የዓለም ፍጻሜ እንደሆነ ማስተጋብት ትዝብት እንጅ ሰባዊነትም ኢትዮጵያዊነት ሊሆን አይችልም ፡፡

አስኪ እነኝህ እና ሌሎች በዚህ አገር ላይ ሲሆኑ ማን ምን አለ ፣ምን አደረገ የዛሬወች የአዞ ዕንባ አንቢዎች ትናንት እና አስቀድሞ የሆነዉ ሲሆን እና እየሆነ ላለዉ እኛም ነገ ምን እንደምንሆን አናዉቅም እና ተዉ ያለ አልነበረም ፡፡

እኮ እንዴት ነዉ ዛሬ ስለ አገር እና ህዝብ የዕርስ በርስ ግጭት ስጋት የሚነግሩን ፡፡ ለመሆኑ ከ1960ዎች አስከ አሁን ሲሰራ የነበረዉ አገር የማፍረስ፣ታሪክ የመደለዝ፣ ህዝብ ከህዝብ ከማናከስ ፣ድንበር ከመቁረስ እና ጠዜጎችን ደም ከማፍሰስ ዉጭ ምን ሰሰራ እንደነበር ከኢትዮጵያ እና የዓለም ህዝብ ዉጭ ማን ይንገረን ፡፡

አስኪ ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉትን እናንሳ ፡-

 • በ1966 á‹“.ም. የተቀጣጠለዉ የህዝብ የለዉጥ ጥያቄ መስመሩን እንዲስት ህብረ ብሄራዊ ኢትዮጵያዊነት ኢንዲከስም የከተማ ላይ ዕልቂት እሳት መለኮስ እና ኢትዮጵያን ማፈራረስ ዕቅድ ነድፎ በኢህፓ፣ መኢሶን እና ሌሎች ጥገኛ የወቅቱ የብሄር ብሄረሰብ ጥያቄ ጭንብል ለባሽ ጉያ ተወሽቆ የዕልቂት ነጋሪት ሲጎስም የነበር ማን ነበር፣
 • የአገርን እና ህዝብ አንድነት በማስጠበቅ እና በማስተባበር ስራ መሪነቱን ከያዘዉ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ጋር አዲስ አበባ ላይ በኃይል ስልጣን ለመያዝ አገሪቷን ለመበታተን የመጀመሪያዋን የሞት ጥሪ አብሳሪ ነጋሪ ጥይት ዕሳት ለኳሽ እና አስተባባሪ እነማን ነበሩ፣
 • እነ ተስፋየ ደባሳይ እና ብርሃነ መስቀል ረዳ እዉነት ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለብሄራዊ አንድነት ነበር የሚሰሩት ፣
 • ኢህፓ እና መኢሶን እና የወቅቱ ተለጣፊ የጥፋት ተባባሪዎች በተለያየ ድርጅት ስም ይጠሩ የነበሩት  እግሬ አዉጭኝ ብለዉ በደረሱበት ጥግ ሲይዙ በኢትዮጵያ እና በዕብሪተኛዉ ዚያድባሪ ወራሪ የሶማሊያ ጦር ወረራ ወቅት ከጠላት ጦር ጋር ኢትዮጵያን ክደዉ ከጠላት ኃይል ጋር የተባበሩ እና ያበሩ የእነዚህ ቅሪቶች አልነበሩም እኮ ብሄራዊ ክህደት የነበረ ባህሪ እንጅ ዛሬ የተከሰተ አይደለም ፣
 • የህዝባቸዉን እና አገራቸዉን ቃል ኪዳን ክደዉ በአብሄራዊ እና ጀግናዉ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ስም “የአገሪቷን የጦር ሠራዊት አባልነት” በህዝብ እና ሠራዊት መሀል ሆነዉ  ሲከፋፍሉ ፤ ከጀርባ ጦሩን  እና ህዝቡን በመዉጋት ከጠላት ጋር የማይፋቅ ታሪካዊ የአገር ክህደት ወንጀል የፈፀሙ እንማን እንደነበሩ ሀታወቀ የአገር ክህደት ነገር የዛሬ ሳይሆን የኋላ ታሪካችን ነባር አካል እንደነበር ይህ ያስገነዝበናል፣
 • በኢትዮጵያ ህዝብ መሪነት እና የዘመናት ተጋድሎ ግንቦት 20፣1983 á‹“.ም. ስልጣን ከያዙበት ዕለት ጀምሮ አገሪቷ የሞት እና የስደት ምድር እንድትሆን በማድረግ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ብሄራዊ የአገር ዳንበር እና ልዑላዊነትን ከ ህዝብ አንድነት ጋር በማስጠበቅ ከሩቅ እና የዉስጥ ጠላት ሲታደግ የነበረን ኃይል የበተነ ማን እንደነበረ ለምን ይረሳል ፤
 • ይህን ከአገር አልፎ ለአፍሪካ እና ለቀሪዉ ዓለም የደህንነት ዋስትና የሚሆን ኢትዮጵያዊ ጦር ኃይል በታትኖ ከብሄራዊ ጦር  ወደ “ቋንቋየ” -ብሄረሰብ- የቡድን እና የግል ጦር ያቋቋመ ማን እና መቸ እንደነበር ካወቅን ዛሬ በመላዉ የአገሪቷ ክፍል በኢትዮጵያዉያን እና በሰሜን ዕዝ ላይ የሆነዉ ነገር የሚጠበቅ እንጅ አዲስ እና ድንቅ ነገር አይደለም ፣
 • ከ 30 እና ከዚያ በላይ የእናት አገር ኢትዮጵያን በደም እና አጥንት እንዲሁም በህይዎት መስዋዕትነት አስከብሮ ያስረከበን ህዝብ እና ጦር ሠራዊት ጡረታ እና ዳረጎት ከመከልከል አልፎ መኖሪያ እና መቀበሪያ ያሳጠ ማን እንደሆነ ስናዉቅ እንደ ድንገተኛ ነገር በመዉሰድ ለምን ጊዜ እናጠፋለን  ፣
 • ከሽምቅ ዉጊያ አስካሁን አገርን እና ወገንን ለጥቃት እና ዉርደት አሳልፎ የሠጠ እና እየሰጠ ላለዉ ገና በ 1983 .á‹“.ም. ከተሰደደበት እና ከወደቀበት እየተጠራ ወደ ኋላ ላልሰራበት ጊዜ ብቻ አይደለም ላልኖረበት ዘመን በቀጭን ትዕዛዝ እና መመሪያ ከ15አስከ 20 ዓመት ወደ ኋላ በመቁጠር በልዩ ዜግነት ደምዎዝ፣ ጥቅማጥቅም ፣ ጡረታ….. እንደከፈለዉ ያደረገ እና የተደረገለት ማን ነበር ፣
 • ኢህዴግ የሽግግር መንግስት ሲመሰረት እና ህገ መንግስት ሲረቀቅ ህዝብን የማያሳትፍ መሠረታዊ እና ታሪካዊ ስህተት የፈፀመዉ ማን እና ከማን ጋር እንደነበር ስናዉቅ ይህ ዛሬ የሆነዉ ያኔ እንደነበር እንደህዝብ ለምን እንስታለን ፣
 • በታሪክ የራሱን አገር እና ህዝብ ለመለያየት ዕንቅልፍ አጥቶ የሰራ እና ይህንም በገቢር ያስመሰከረ ማን እንደነበር ዓለም የሚያዉቀዉን ትናንት ጣራ የነቀለ ዛሬ የአገሪቷን እና ህዝቧን መሰረት እንዳልነበር ለማድረግ አፈር ቢምስ ፤ድንበር ቢያፈርስ አይድነቀን ፣
 • የአንድ አገር ህዝብ የሁለት አገር ኗሪ እንዲሆኑ ( የመሃል አገር እና ኤርትራን) በማስጨነቅ እና ማራራቅ ለመለያየት ከጥዋት አስከ ዛሬ የማይታክተዉ ማን እንደነበር ለማወቅ እንዴት እኛ ኢትዮጵያዉያን ይሳነናል ፣
 • ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ጥንታዊት እና የስልጣኔ አገር መሆኗ ከድሮ አስከ ዘንድሮ የሚያመዉ እና ለዚህም የተሳካለት እንደ ኢህአዴግ /ህወሀትመንግስት ማን ነዉ ፤ማን ነበር ፣
 • ለመሆኑ አገርን እና ህዝብ አምርሮ በሚጠላ እና በሚንቅ መንግስት የሚመራ /የተመራ ህዝብ በጠላት እና ወዳጅነት እየፈረጁ ዳግም የባርነት ቀንበር ለመጫን የጥፋት እና ሞት መላ መሞከሪያ እንዲሆን የክፉ ምኞት መተግበሪያ ቤተ ሙከራ ማድረግ ዛሬ ነዉ ወይ የተጀመረዉ ፣

ስለዚህ ትናንት ለኢትዮጵያ ህዝብ ሞት ለአገሪቷ ድቀት እና ዉድቀት ሲምሉ እና ሲገዘቱ ከነሱ ክፉ ፍላጎት እና ምኞት ዉጭ ብርሃን ጨለማ ነዉ ለሚሉት የአዞ ዕንባ የሚያነቡ የልማዳቸዉን ከንፈር መምጠጥ ከደም መምጠጥ (መዥገር) የጥገኝነት ባህሪ ዉጭ ሠባዊነት እና ሠላማዊነት የሚያሳስባቸዉ የሚመስሉት ትናንት እና ከትላንት በስቲያ የት እና ምን ሲሉ እና ሲያደርጉ እንደነበር ይጠየቁ ፤ይናገሩ ፡፡

ከልሆነ ታላቁ እና የህንዶች የነጻነት አባት ማሕተመ ጋንዲ እንዳሉት “እዉነት የማትናገር ከሆነ ዝም በል” ለናንተ ሲሆን ብርን ጨለማ ፤ ጨለማ ብርሃን የክህደት መዝገበ ቃላት ትርጉም ለናንተ እንጅ ለብዙሃን ኢትዮጵያዉያን እና ለአገር አንድነት የቆየ እና ነባር ብሄራዊ እና ህዝባዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት ትስስር ስላለን እንደለኮሳችሁ ባታጠፉት የሚያቃጥላችሁ እናንተን እንጅ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሆና እንደምትቀጥል የአዞ ዕንባ ለሚያነቡት ሁሉ አትስጉ በሉልን ፡፡

እንደናንተ እና እንደ እነሱ(የሩቅ ታሪካዊ ጠላቶች) ሃሳብ እና ምኞት  ቢሆን ኢትዮጵያ የፈረሰችዉ እኮ ከ1960 አስካሁን በተደረገባት ተደጋጋሚ ሴራ ነበር ፡፡

ይህንም ዳግም ስናስረዳ ኢትዮጵያን በቀይ ባህር እና በዓባይ ወንዝ ምክነያት ለማጠፋት እና ለማክሰም ለዘመናት ሲያሰሩ የነበሩት እነ ኢራቅ፣ ፓኪስታን፣ ሶሪያ፣ ግብጽ፣ ሱዳን ፣ሶማሊያ ፣የመን ……ወዘተ እኮ የእጃቸዉን አላጡም ፡፡ የእኛ ኢትዮጵያዉያን በስም መለቴ ነዉ በምግባር እና ተግባር ለእንሩ እና ለህዝብ ትቸ  ከጠላት ጋር በየዘመናቱ እየተለጠፉ የራስን ማዕድ በአፈር መሙላት አስከ መቸ እንደሚቀጥሉ ለማወቅ አለመቻል ግን ሌላ ነዉ  ፡፡

በመጨረሻም ሁሉም የእጅ ዋጋዉን አያጣም ፡፡ እናም በህዝብ እና አገር ላይ ገና ለገና አትንኩኝ የሹም ዶሮ ነኝ ይል የነበር እና ለኢትዮጵያ ዉድቀት ፤ለህዝቧ ድህነት፣ ስደት፣ ሞት እና ዉርደት ሲያዝላት የነበር ዛሬ ምሱን የሚያገኘዉ በሰጠዉ ልክ እንጅ የኢትዮጵያ ህዝብም ፤መንግስትም አይደለም ፡፡

ልክ እንደ ጀግና ሰዉ ዋ እኔን የነካ በቁም ይቀበራል ሲል የፎከረዉ ፣

ለካስ እንደዚህ ነዉ ጨካኝ እና ፈሪ ሞቶ ያዳነዉን ላሞራ የሚሻዉ ፡፡

እኛ በአገራችን እንኳንስ የሞተ ገዳይ ክብር ክብር አለዉ ፣

ግን ዛሬ ተዋረድን ከሠዉ ተራ ወረድን ለአገር የሞተን ሠዉ አፈሩን ነፈግነዉ ፡፡

ትናንት በጦርነትብቻዉን ሲመካ በከንቱ ሲኩራራ ፣

ምን ተገኘ ኑ ! እንቁም የሚለዉ ለጥፋት በጋራ ፡፡

እናም ፡

“አንተም ጨካኝ ነበርክ ጨካኙን ላከብህ ፣

        እንደ ገና ዳቦ እሳት ለቀቀብህ ፡፡”

 ማላጂ

እናት አገር ምንጊዜም ትኑር !!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.