‹‹እሣት ቢያንቀላፋ፣ ገለባ ጎበኘው!!! የወባ ትንኝ ለመግደል መድፍ አይተኳስም!›› ፀ/ትፂዮን ዘማርያም

et222‹‹የወባ ትንኝ ለመግደል መድፍ አይተኳስም!!!›› Do not use a cannon to killa mosquito.
የኢትዮጵያ ህዝብ አምኖ የላከውን የፌዴራል መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በተኙበት መጨፍጨፍ የማፍያው ህወሓት ሥራ እርኩስ ሥራ ነው፡፡ ሃገሪቱ በወያኔ ያወደመባትን  የጦር መሣሪያ ክምችት በሙሉ የሕወሓት የንግድ ካንፓኒዎች፣ ፋብሪካዎች፣ እርሻዎች፣ የአገልግሎት ዘርፎች፣ ባንኮች፣ ማይክሮ ፋይናንሶች እንዲሁም በየቦታው የሚገኙ ሠማይ ጠቀስ ፎቆች በሙሉ ተሸጠው የወደመው የሃገር ኃብት መከላከያ ሠራዊት ከባባድ መሳሪያዎች ተገዝተው ይተካሉ፡፡  ከትግራይ ክልል በመማርም ከክልል ፖሊስ በስተቀር ያሉ የክልል ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀትች ሙሉ በሙሉ ከክልሎች እጅ አውጥቶ በፌደራል መዋቅር ስር ማድረግ፡፡

ህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ህግሓት) The Eritrean People’s Liberation Front (EPLF) was an armed organization that fought for the independence of Eritrean from Ethiopia.  ሁለቱ የአፍሪካ ቀንድ ደሃ አገራት ፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ በድንበሮች ባድማ፣ ፆረና፣ ኢሮጵ  ወስን ግጭት የተነሳ የኢትዮጵያ ህወሓት መለስ ዜናዊና የህጋሓት ኢሳያስ አፈወርቂ  ከ1998 እስከ 2000 እኤአ ጦርነት ገጠሙ፣  ከ70 እስከ 100 ሽህ ወታደሮቻቸውን በጦርነቱ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡   በ2018 እኤአ በሁለቱ ሃገራት እርቀ ሰላም በዶክተር አብይ አህመድ አመራር ሠላም ሠፈነ፡፡ ጦርነት ‹‹ መቼም የትም አይደገም!!! ›› ማለት አልቻልንም፡፡ ዛሬ ደግሞ የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ የጦር አበጋዞች መንግሥት ጦርነት ገጥመው ብዙ ሽህ ወጣቶች ህይወት ተቀጥፎል፣ የሃገሪቱ ንብረት ወድሞል፣ የሃገሪቱ መከላከያ ሠራዊት የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ከባድ የጦር መሣሪያ ክምችት ታንኮች፣ ሚሳኤሎች፣ ላውንቸር፣ ሮኬቶች፣ ብሬል፣ አርፒጂ፣ ወዘተ የተገዙት  በብር ሳይሆን በውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ የገባ በመሆኑ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት ያስከትላል እንላለን፡፡ በፌዴራልና በትግራይ መንግስት ጦርነት የዘር ጥላቻ ቅስቀሳን ማጥፋት፡፡ የትግራይ ህዝብ ከህወሓትወያኔ የግፍ አገዛዝ ወጥቶ በስብዓዊ ጋሻነት ታግቶ ዛሬ ነጻነቱን መግኘቱን እንዲያጣጥም በተግባር ማድረግ፡፡

 • በጥቅምት 24 ቀን 2020እኤአ በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዶክተር አብይ አህመድና የትግራይ ክልል የጦር አበጋዞች መንግስት ዶክተር ደብረፂዮን ገብረማርያም ኢትዮጵያን ለሃያ ሰባት አመታት በግፍ ከገዛ በኃላ ከሥልጣኑ ወርዶል በዚህም ብሶቱ በትግራይ ውስጥ የሚገኘውን የሃገሪቱን የፌዴራል መንግሥት የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ የመሣሪያ ጥቃት በመፈፀም፣ የሃገሪቱን የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በመማረክ የተራ ወንበዴ ሥራ ሰርቶል፡፡  የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት አባሎችን በመግደልና መሳሪያውን በመዝረፍ ዳግም ወደ ሥልጣን መንበራችን እንመለሳለን በሚል የንፁሃን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል፡፡  አበው ሲተርቱ ‹‹እሣት ቢያንቀላፋ፣ ገለባ ገበኘው!!!›› ብለው እንደተረቱት፡፡ወያኔ ያወጣውን  ህገ-መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ቀብሮታል፡፡ ወያኔ ሁሉን ነገር በኃይል ለመፍታት በመሞከራቸው የተነሳ ድህነትን ሊጠፉ አልቻሉም፡፡ የሠለጠነው ዓለም ችግሮቹን የሚፈታው በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ውይይት ብቻ ነው፡፡ ወያኔን ‹‹የወባ ትንኝ ለመግደል መድፍ አይተኳስም!!!›› ልንለው ይገባል፡፡ በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ የጦር አበጋዞች መንግሥት ጋር የተደረገው ጦርነት ነገ ደግሞ ከኦሮሞ፣ አማራ፣ ሱማሌ፣ከደቡብ ክልል የጦር አበጋዞች መንግሥት ጋር ጦርነት መግጠሙ እንደማይገጥም ምንም ዋስትና የለም፡፡ ስለዚህ በዘር ላይ የተመሠረተው ህገ መንግሥትና በዘር ላይ የተዋቀረው ወሰንና ድንበር ጅኦ ፖለቲካል ካርታ  መቀየር አለበት እንላለን፡፡ የፌዴራል መንግሥቱ ይህን መስተካከል ካላደረገ  ዘለቄታዊና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ለውጥ ማምጣት አይቻልም፡፡

ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል

 • የትግራይ ክልል መሪ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፤ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አደረጃጀት ላይ ለውጥ መደረጉን ተከትሎ የትግራይ ክልል መንግሥት እርምጃውን ተቃውሞ መግለጫ ማውጣቱም የሚታወስ ነው። “የፌደራሉ መንግስት ስልጣኑ መስከረም 25/ 2013 á‹“.ም ላይ ያበቃ በመሆኑና ሕጋዊ ተቀባይነት ስለሌለው በመከላከያ ሰራዊት አደረጃጀት ላይ ለውጥ ሊያደርግ አይችልም” ብሏል በመግለጫው፡፡የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በበኩሉ ይህን የትግራይ ክልል መግለጫ “ኢ-ህገመንግስታዊ” በማለት ተቃውሞ መግለጫ አውጥቷል። ዶክተር  ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፤ የትግራይ ክልል መንግሥት የመጀመርያው ፍላጎት ሰላም መሆኑን በመግለጽ “ቢሆንም፤ እኛም ሰራዊት አዘጋጅተናል፤ ሚሊሻችንን አዘጋጅተናል፤ ልዩ ኃይላችንን አዘጋጅተናል። ጦርነት ለማስቀረት ነው የተዘጋጀነው። መዋጋት ካለብን ግን፤ ድል ለማድረግ ተዘጋጅተናል” ሲሉ ተናግረው ነበር። ዶክተር ደብረጽዮን በሰኞ መግለጫቸው ላይ “የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መንግሥትና የኤርትራው መንግስት በትግራይ ላይ አብረው እያሴሩ ነው” ሲሉ ከስሰው ነበር።
 • በኢትዮኤርትራ ጦርነት ጊዜ ወደ ትግራይ ተጎጉዞ በትግራይ ውስጥ የተከማቸውን የሃገሪቱ የጦር መሣሪያ ሰባ በመቶ ያህል እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ የሀገሪቱ ታንኮች ከአራት መቶ እስከ አምስት መቶ ታንክ፣ አጭርና መካከለኛ ርቀት የሚወነጨፉ ሚሳኤሎችና ሮኬቶች፣ ላውንቸሮች፣ አርፒጂ፣ ስታሊን ኦረጋን፣ መድፎች፣ ብሬል፣ ልዩ ልዩ ፈንጅዎች፣ የነፋስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎች፣ ወዘተ ወደ ትግራይ የጦር ግምጃ ቤቶች በማከማቸት ጦርነቱን አሸንፎል፡፡
 • መቐለ የመሸገው ህወሓት መሪዎች የኢትዮጵያን ሠራዊት ለማጋጨት፣ ደም ለማፋሰስ፣ የትግራይን ህዝብ አማራ ሊወርህ ነው ተነስ፣ አፋር በዚህ በኩል መጣል፣ ኤርትራ ጦር ሠበቀብህ እያሉ የሥልጣን እድሜቸውን ለማራዘም የአዞ እንባቸውን ሲያፈሱ አመታት ተቆጠረ፡፡ ህወሓት ለክልሉ ሠራዊት ደሞዝ የሚከፍለው ቤሳቤስቲን ገንዘብ የለውም፣ የትግራይን ህዝብ ኃብት እየዘረፈ ውጭ ሃገር በልጆቹ ስም ቪላቤት ሲገዛ ከርመዋል፡፡ ወያኔ  በንዋይ ፍቅር ሃገር ሲበዘብዙና ዴሞክራሲ ለ27 አመታት ሲያፍን ሠንብቶ ዛሬ ምርጫ ካላደረግሁ ብሎ ይፎክራል፡፡ ወያኔ የትግራይ ህዝብ ንፁህ ውኃ፣ መብራት፣ ህክምና መኖሪያ ቤት ለመስራት  ወዘተ ነፍገውት በፍርሃት ሲገዙት ዘመናት ተቆጥሮል፡፡
 • የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፣የትግራይ ክልል አራት አዋሳኝ ወይም ድንበርተኞች አሉት እነዚህም በሰሜን ከኤርትራ፣ በምሥራቅ ከአፋር ክልል፣ በደቡብ ከአማራ ክልል  እንዲሁም በምዕራብ ‹‹ከሱዳን ሪፐብሊክ›› ጋር ይዋሰናል፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ድንበር  የማስፋፋት ፖሊሰ  ከጎንደር፣ ከወሎ፣ ከአፋር ህዝብ ለም መሬት በመንጠቅ ወደ ትግራይ ክልል በማካተት የትግራይን ህዝብ ከሌሎች ደሃ ወንድሞቹና እህቶቹ የማለያየት ፖሊሲ ውጤት ነው፡፡ ከጎንደር መሬት ሁመራ፣ ወልቃይት ወዘተ የሠሊጥ ለም መሬት ላይ የትግራይ የጦር ጉዳተኛችን በማስፈር፣ የአገሬውን መሬት በግፍ በመንጠቅ የተቃወመውን ህዝብ በመግደል፣ በማሰር እንዲሰደድ በማድረግ ኃብቱን ተቆጣጥረዋል፡፡ በተመሳሳይ ከአፋር የጨው ማዕድናት ፋብሪካዎች በመትከል አብዛኛዎቹን የሚቆጣጠሩት የትግራይ ጦር አበጋዞች ነበሩ፡፡ እንዲሁም በአፋር የተገኘውን የፖታሽ ማዕድን አምርቶ ለመሸጥ በአፋር በኩል በትግራይ አርጎ ጅቡቲ የሚገባ የባቡር መስመር ዝርጋታ የህወሓት ጦር አበጋዞቹ የኃብት ቅርምትና የመስፋፋት ፖሊሲ ስትራቴጂ ውጤት ነበር፡፡

ዶክተር አብይ አህመድ

 • ጠቅላይ ሚንስትሩ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው “ይህንን ጡት ነካሽ ኃይል ለማሳፈር እና ለመደምሰስ አስፈላጊውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን እገልጻለሁ” በማለት ጦርነት መከፈቱን አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ መከላከያ ሠራዊት አገር የማዳን ግዳጅ እንደተሰጠውም አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ “ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል” ብለዋል።
 • ጠቅላይ ሚንስትሩ ሠራዊቱ ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ መሆኑን ገልፀው በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው።”ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታትና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል” ብለዋል። አክለውም “የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል። ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል” በማለት ገልፀዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ሲናገሩ ከትግራይ ክልል ጋር የተከሰተው አለመግባባት “በሕግ እና ሕግ ብቻ የሚመለስ ይሆናል” በማለት መናገራቸው ይታወሳል።
 • ህገ-መንግስት፤- ከህወሓት ኢህአዴግ የፖለቲካ ሴራን ለመበጣጠስ የወያኔን ህገ-መንግስት በአዲስ ተክቶ ይሄን የአባላሽኝ ዘመን አልፈን አዲሲቶን ኢትዮጵያ በእውነትና በሃቅ መምራት ይጠበቅብናል፡፡ የህወሓት ኢህአዴግ ጅኦ ፖለቲካል ካርታ ሃገሪቱን ክልል ግዛትና ድንበር በዘር የሸነሸነ በመሆኑ የሃገሪቱ ዜጎች በድንበር ግጭት ወደማያባራ ጦርነት መግባታቸው የሻብያ ፣ወያኔና ኦነግ የተቀበረ ቦንብ ነው፡፡ ዛሬ በትግራይ ክልል ህዝብ ላይ የአማራ ክልል ህዝብ ጦርነት እንዲገጥሙ ማድረግ የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ብልፅግና ፓርቲ የመቶ ዓመቱን ፖለቲካ ፓርቲ ቀጣይ ተግባር ነው፡፡
 • በኢትዮጵያ የክልል መንግሥት ድንበሮች/ ወሰኞች፣ (Regional state borders) የኦሮሚያ ክልል 9 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የአማራ ከልል 5 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የትግራይ ክልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የአፋር ከልል 6 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የሱማሌ ከልል 5 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የደቡብ ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የጋምቤላ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የሃረሪ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉዋቸው፡፡  በኢትጵያ የክልል ብሄራዊ መንግሥታት  የመስፋፋት ፖሊሰ፣ ሃገሪቱን ወደ ማያባራ የድንበርና የወሰን ግጭት እንደሚዳርጋት ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡ ፌዴራሊዝም በጂኦግራፊያዊ ወይስ በቌንቌ!!!
 • ጅኦ ፖለቲካል ካርታ ይወገድ፡- በኢትዮጵያ ዜጎች በመላ ሃገሪቱ ተዘዋውረው እንዲሰሩ ከተፈለገና በፈለጉበት ቦታ መኖር እንዲችሉ ከተፈለገ ይህ በዘር ላይ የተሸነሸነ ሰው ሰራሽ ጅኦ ፖለቲካል ካርታ መወገድ አለበት፡፡

ከትግራይ የጦር አበጋዞች መንግስት የሌሎች ክልሎች የጦር አበጋዞች መንግስት ምን ይማራሉ?

የአማራ፣ የኦሮሞ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ሃረሪ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ፣ ሲዳማ፣ የጦር አበጋዞች መንግስት ከትግራይ ክልል የጦር አበጋዞች መንግስት ምን ይማራሉ የፌዴራል መንግሥት ምን ሊማር ይገባዋል?

1ኛ/ ከክልል ፖሊስ በስተቀር ያሉ የክልል ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀትች ሙሉ በሙሉ ከክልሎች እጅ አውጥቶ በፌደራል መዋቅር ስር ማድረግ፣

በኢትዮኤርትራ ጦርነት ጊዜ በትግራይ ውስጥ የተከማቸውን  የሃገሪቱ የጦር መሣሪያ ሰባ በመቶ የሚሆነውን የጦር ክምችቶን ማውደሞን ዶክተር አብይ አህመድ  አብስሮናል፡፡ በመላ ሃገሪቱ በተደጋጋሚ በሚከሰቱት ግጭቶችና የዘር ፍጅት ከክልሌ ውጣ፣ ህዝብ በነፃነት ተንቀሳቅሶ መስራት አልቻለም፡፡ ሃገሪቱ በጦር አበጋዞች የክልል መንግሥቶች  የድንበር ግጭት የተነሳ ወደማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነት ለመሸጋገር ክልሎች ካራ እየሳሉ ይገኛሉ፡፡ የትግራይ ክልል 250000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ) ልዩ ሓይል፣ የአማራ ክልል 300000 (ሦስት መቶ ሽህ) ልዩ ኃይል፣ የኦሮሚያ ክልል 400000 (አራት መቶ ሽህ) ልዩ ኃይል፣ የሱማሌ ክልል 40000 (አርባ ሽህ በአብዲ ኢሌ ሄጎ ኃይል)፣ የጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሃረሪ፣ አፋር፣ ደቡብ (ሲዳማ ክልል አንድ ሽህ ልዩ ኃይል)፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት 250000(ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ) ይገመታል፡፡ ሁሉም ክልሎች የራሳቸው ሚሊሽያና ፖሊስ ኃይል በተጨማሪ አላቸው፡፡  ይህ የዕለት ተዕለት ሥራችን ሆኖ ምርት የማያመርት እልፍ ልዩ ኃይል ጥገኛ ተዋሲያንና ሰባት ሚሊዮን የኢህአዴግና ብልፅግና ፓርቲ ጥገኛ ተዋሲያን መጅገር ካድሬዎች ባሉበት አገር የኢኮኖሚ እድገት አይታሰብም፡፡ የህክምና ዶክተሮች መቅጠር ያልቻለ መንግሥት ብልፅግና አያመጣም፡፡ የህግ የበላይነት የማያስከብር መንግስት ብልጽግና አያመጣም፡፡ በሃገሪቱ የኮሮና ቨይረስ ወረርሽኝ፣ ጎርፍ፣ አንበጣ ወረርሽኝ፣ የዘርና ኃይማኖት ፍጅት እንዲሁም የድንበር ግጭት እያለ የኢኮኖሚ እድገት ውሸት ነው፡፡

የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት የክልል ሥልጣንና ተግባር ‹‹የክልሉን የፖሊስ ኃይል ያደራጃል ፣ይመራል፣የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃል፡››  ይላል አንቀጽ 52፡፡ በህገ-መንግሥቱ  መሠረት ክልሎች የፖሊስ ሠራዊት ኃይል ብቻ ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ( ትህነግ) ህገመንግሥቱ በመጣስ ክልሎች  ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀቶች  እንዲኖራቸው አደረገ፣ ቀስ በቀስ እየተጠናከሩ በመሄድ በክልሎች መኃል ተጨማሪ ኃይል የማሰባሰብ ክልሎች እርስበእርሳቸው የጎሪጥ እንዲተያዩ አደረጋቸው፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በዘርና በብሔር አደረጃጀት ከፋፈለው፣ ሸነሸነው፡፡ ወያኔ የሠራዊቱን  ሃገራዊ ፍቅሩንና ብሄራዊ ክብሩን በማዋረድ ሠራዊቱን በዘርና ኃይማኖት ፍጅት ውስት ተሳታፊ እንዲሆን በመቀስቀስና የዘር ጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት  ሃገሪቱን እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊቢያ ሊያፈርሳት እየጣረ ይገኛል፡፡ የወያኔ የፖለቲካ ሴራ ለስልጣኑ ሲል ሃገር በማፍረስ  ሠራዊቱን  ተባባሪ ማድረግ አልተቻለውም፡፡ ትግራይ ክልል የሚኖር የኢትዮጵያ ሠራዊት የወያኔ ተባባሪ አይሆንም የወያኔ መሪዎችን አስሮ ለፌዴራል መንግስት እንደሚያስረክባቸው ምንም ጥርጥር የለንም፡፡

‹‹የጎሳ ፖለቲካ ጡዘት ሰማይ በነካበት እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገር ውስጥ በብሔር የተዋቀረ የክልል ታጣቂ ልዩ ኃይል ወይም ሚሊሻ ማደራጀት ማለት የተጠመደ ፈንጅ በጀርባ አዝሎ እንደመዞር ነው። ክልሎች በአገር ውስጥ ያሉ አገሮች ሆነው ተዋቅረዋል። በዛ ላይ አወቃቀራቸው ቋንቋና ብሔርን መሰረት ያደረገ ነው። የብሔር ፖለቲካው እያመሳት ላለች አገር በብሔር የተደራጁ ታጣቂ ኃይሎች እያሰለጠኑ እና እያስታጠቁ በየክልሉ ማስቀመጥ ካየነው በላይ ብዙ ግፍ እንድናይ እና ኢትዮጵያንም በቀላሉ ወደ ዘር ተኮር ግጭት ከመውሰድም በላይ የአክራሪ ቦድኖች መፍለቂያነት እና ወደ ሽብር ቀጠና ሊለውጣት ይችላል። ከወዲሁም አንዳንድ ምልክቶች በግላጭ እየታዩ ነው፤

በክልሎች መካከል ያለው ውጥረት እና ትከሻ መለካካት በየጊዜው ግጭቶችን አስከትሏል። አሁንም ተፋጠው፣ ጉድጓድ ምሰው እና ቃታ ስበው ለፍልሚያ ቀን የሚጠብቁ አሉ። ለዚህም የትግራይና የአማራ ክልል ፍጥጫ ጥሩ ማሳያ ነው።››

2ኛ/ በብሔር የተዋቀረውን የጸጥታ አስከባሪ ኃይል ሙሉ በሙሉ በመበታትን ወደ ሁሉም የአገሪቷ ክፍል ማሰባጠር እና በእያንዳንዱ ክልል ውስጥ ያለው ታጣቂ ኃይል ከሁሉም ብሔር የተወጣጣ እንዲሆን ማድረግ፣

3ኛ/ በየክልሉ ያለውን ስብጥር ኃይልን በበላይነት የሚመሩትንም አዛዦች እንዲሁ በተሰባጠረ መልኩ ማዋቀር፣

4ኛ/ ይህን ኃይል በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት አይምሯቸው ውስጥ ያለውን የብሔረተኝነት ስሜት በሂደት እንዲቀይሩና ያለመድሎ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ደህንነት ዘብ እንዲቆሙ ማድረግ።

ክልሎችም ያንጃበበውን አደጋ ከወዲሁ አጢነው ለዚህ ለውጥ መሳካት ካልተባበሩ በዘር ያደራጁት የታጠቀ ኃይል ተንሸራቶ አክራሪዎች እጅ የወደቀ ዕለት የመጀመሪያዎቹ የጥቃት ኢላማዎች እነሱ መሆናቸውን ሊያጤኑት ይገባል። በዘር ተደራጅቶ በዘር የታጠቀ የዘር ፍጅትን ያፋጥናል። ይህን ለማድረግ ግን ወሳኙ ነገር የአገዛዝ ሥርዓቱ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና ያንጃበበውንም አደጋ በበቂ ሁኔታ መረዳትን ይጠይቃል። ይሄን የተጠመደ ፈንጂ ሳያመክኑ በጀርባ አዝለው እየዞሩ ኢትዮጵያ አትፈርስም ማለት ብቻውን አደጋውን አያስቀረውም።›› የብልፅግና ፓርቲ መሪ ዶክተር አብይ አህመድ ይሄን ምክር ተጠቅመው የኢትዮጵያን እናቶች፣ ህጻናትና፣ ሁሉን ዜጎች ከዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጀኖሳይድ) ሊታደጉት ይገባል እንላለን፡፡ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ፣ ፈጣሪ ይርዳዎት፡፡

‹‹በሀገራችን ውስጥ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ግምባር ቀደም ተጠቂ ይሁኑ እንጂ፣ “መጤ”ና “ኗሪ” በሚል የጥላቻ ትርክት የተቀመረው ሕገ-መንግሥት ሌሎች ብሄረሰቦችንም ለጥቃት አጋልጧቸዋል። ጉራጌዎች፣ ስልጤዎች ጋሞዎች…ወዘተ ተጠቂዎች ሆነዋል። በሃይማኖትም ክርስቲያን ኦሮሞዎች የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ይገኛሉ። የፌዴሬሽኑን ሕገ-መንግሥትና የክልል ሕገ-መንግሥቶችም፣ ተቀርፀው የተዋቀሩት አንዱን ‹ኖሪ/ባለቤት› የአንደኛ ደረጃ ዜጋ ሌላውን ‹መጤ/ ሠፋሪ›  በሚል የሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ማዕከልነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው።  በቡራዩ፣ በአርሲ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሻሸመኜ፣ በዝዋይና በባሌ እስከ ሦስት ጊዜ ድረስ የተካሄደው ጥቃት፣ ባመዛኙ የአማራና ሌሎችንም “መጤ” ተብለው የተሰየሙ ብሄረሰብ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞችንና የዕምነት ቤቶችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ነው። በኢትዮጵያ  የሃይማኖትና፣የእምነትና የአመለካከት ነፃነት በትግላችን ይከበራል!!!

 

ምንጭ፡-

(1)  የክልል ልዩ ታጣቂ ኃይል ይፍረስ፤ በዘር ተደራጅቶ፣ በዘር የታጠቀ፣ የዘር ፍጅትን ያፋጥናል…!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

1 Comment

 1. TPLF robbed new printed cash from banks in Tigray by using military attacks as diversion tactics.. This attack on Ethiopian Military forces was a diversion tactic so TPLF robs new bank notes cash from banks in Tigray.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.