በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ ከኢትዮጵያዉያን ማኅበር በአዉሮፓ የተሰጠ መግለጫ

EU ethiopian ass. በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ ከኢትዮጵያዉያን ማኅበር በአዉሮፓ የተሰጠ መግለጫእኛ በአውሮፓ የሚንኖር ኢትዮጵያዊያን ባለፈው ሳምንት በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በተነሳው ግጭትና ጦርነት እንዲሁም የዜጎቻችን ላይ

በደረሰው የሞትና የሰላም መደፍረስ አደጋ እጅጉን አዝነናል። እስካሁን ባሉን መረጃዎች መሰረት

ለዚህ አስከፊ ግጭትና ጦርነት በሰሜኑ እዝ ስር በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ የደረሰ ጥቃትና የንብረት መዝረፍ ሙከራ ሲሆን ለዚህም ቅጥ ያጣ ወንጀልና ትንኮሳ ዋና ተጠያቂው ከማህከላዊው መንግስት አፈንግጠው የወጡትና መኖሪያቸውን በትግራይ ክልል ያደርጉት ጥቂት የህውሃት ባለስልጣኖች መኖቸውን አረጋግጠናል።

እንደሚታወቀው ሁሉ ህውሃት የየካቲት 66 ቱን ህዝባዊ አብዮት ክዶ ወደ ደደቢት በረሃ ከገባበት ከ1967 ዓም ጀምሮ የቅድሚያ ጠላቱ አድርጎ የተነሳው የአማራውን ህዝብና ኢትዮጵያዊነትን ሲሆን የካቲት 11 ቀን 1968 ዓም ባወጣም ማኒፌስቶ የአማራውንና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዩን በማጥፋትም የኢትዮጵያን ህዝብ ታሪክና አንድነት ለማጥፋት የመጨረሻ ግቡ አድርጎ መነሳቱን በማያሻማ መልኩ ገልጾታል። እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን ህውሃት የትግራይን ህዝብ በሙሉ እንደማይወክል ጠንቅቀን እናውቃለን ፤ አሁን ቢሆን ለትግራይ ህዝብ ታላቅ ፍቅርና አክብሮት አለን።

ህውሃት ወደ ስልጣን ከመጣበት ከ1983 ዓ/ ም ጀምሮ በስልጣን ላይ በቆየባቸው 27 ዓመታት በሙሉ የአማራውን ዘር ለማጥፋትና የዚህን አንጋፋና ታሪካዊ ህዝብ ባህላዊና መንፈሳዊ እሴቶቹን በሙሉ (የአማርኛ ቋንቋ፤ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት፤ የእምነት በዓላትንና ታሪካዊ ስራዎቹን) ለማኮሰስና ለማጥላላት የተለያዩ ጥረቶችን አድርጓል። በተለይም አማራውና ኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ በማንነቱ ተለይቶ እንዲጠፋ እንዲያፍር እንዲሸማቀቅ ከማድረግ በተጨማሪም አማራ ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ቋንቋ ሃይማኖትና ታሪክ ጋር እንዲቃረን የውሸት ትርክት ፈጥሮ፣ አሳሳች ፍኖተ ካርታ ቀርፆ አንድ ትውልድን በሙሉ ያጭበረበረ ሃላፊነት የጎደለውና ፀረ-ኢትዮጵያዊ ድርጅት ነው።

ለዚህም እኩይ ተልእኮው ዋና ማስፈጽሚያ የሆነውን ህገ-መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በመጫን የአማራው ማህበረሰብ ከሎሎች ማህበረሰብ ክፍሎች በተለየ መልኩ እንዲጠላ ፣ ታሪካዊና ነባራዊው አስተዋጾ በትውልድ ሁሉ እንዲናቅ እንዲረሳ ፣ በገዛ ሃገሩ የመኖር የመስራት የመማር የማምለክ ነጻነቱን ከመገደብም አልፎ ተርፎ በፖለቲካውና በምጣኔ ሃብት ተሳትፎውም ረገድ ከሌሎች ማህበረሰብ በተለየ መልኩ እንዲገለል ከፍተኛ ጥረት ያደረገ ጽንፈኛ ከፋፋይና አግላይ ድረጅት ስለመሆኑ የተባበሩት መንግስታት ደርጅት አምኒስቲ ኢንተርናሽናልንና ሂይማን ራይት ዎችን ጨምሮ በርካታ ሃገር በቀልና ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በተለያየ ጊዜያት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሚገባ ገልጽውታል።

ይሁን እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ሹመት ተከትሎ ከማእከላዊ መንግስት የስልጣን መዋቅር ውስጥ የተሰናበትው ህውሃት ላለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ብቻ በአማራው ህዝብና ኦሮቶዶክስ ክርስቲያን ማህበረሰብ ላይ ያነጣጠረ ግድያና መፈናቀል እንዲፈጸም የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታን ከማድረጉም በላይ አሁንም ለሃገራችን ሰላምና ለዜጎቻችን ድህንነት ከፍተኛ ስጋት ሆኖ ይገኛል።

በመሆኑ እኛ በአውሮፓ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ወቅት የመከላከያ ሰራዊታችን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመተባበር የሚወስዳቸውን ማናቸውም ዓይነት ወታደራዊ ሰብዓዊና ሞራላዊ እርምጃዎች ከመደገፍም አልፎ ተርፎ በማንነቱ ተለይቶ እየተገደለና እየተገፋ ያለውን የአማራ ህዝብ ለመታደግ ሃገራችን በምታደርግልን ጥሪ ሁሉ ከህዝባችን ጋር ተሰልፈን የሚከፈለውን መስእዋትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ መሆናችንን ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት መግለጽ እንፈልጋለን። ይህ ጦርነት እልባት እስኪያገኝም ድረስ የጠሚ አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በወለጋ ዞንና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተገደለና እየተፈናቀለ ላሉት የአማራና የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ወገኖቻችንን ትኩረት ሰጥተው አስቸኳይ የደህንነት ጥበቃና ዋስትና እንዲረግላቸው በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።

ፈጣን እርምጃ ሳይወሰድ ቀርቶ የንፁሃን ወገኖቻችን መታረድ፣ የንብረት መዉደምና መፈናቀል ከቀጠለ ግን የኢትዮጵያን መንግስት በሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉድለትና በሰው ዘር መጥፋት ወንጀል ለዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለማቅረብ የምንገደድ መሆኑን በአፅንዖት እናሳስባለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ! ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ

የኢትዮጵያዉያን ማኅበር በአዉሮፓ (ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓም). 09-11-2020 (GC)

Ethiopian EU በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ ከኢትዮጵያዉያን ማኅበር በአዉሮፓ የተሰጠ መግለጫ

 

2 Comments

  1. ጄ/ባጫ ደበሌ የሰጡትን መግለጫ ላዳመጠ ወያኔ እንስሳ አረመኔ እና ሃገር ሺያጭ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። በሰራዊቱ ላይ የተፈጸመው በደል ለዘላለም አይረሳም። ልዪ ሃይሉ መደምሰስ አለበት። ኮማንዶው መደምሰስ አለበት። ሳያውቅ ነው እያሉ ማላገጥ ለማንም አይጠቅምም። በሰው ሬሳ ላይ የሚጨፍሩ። ልብስ አውልቀው የሰራዊትን ሬሳ ለአራዊት ከሰጠ ወገን ነኝ ባይ ጋር እንዴት ነው አብሮ የሚኖረው? በምን ሂሳብ? ኦነግ፤ ወያኔ አብረው ነው ጦሩን ያጠቁት። ይህ ያደረሱት ግፍ ለምን በቪዲዮ ተቀርጾ ለዓለም ህዝብ እንደማይታይ ግን አይገባኝም። እነርሱ ተወጋን እያሉ ሲያላዝኑ መንግስት አይ እውነታው ይህ ነው ብሎ ለምን መረጃውን ይፋ አያደርገውም? በእርግጥም እልፎች ተጨፍጭፈዋል። የድሃ ልጅ በአለበት ታርዷል። ተራፊው ልብሱ ተገፎ ወደ ኤርትራ ተሸኝቷል። ከእነዚህ ጉዶች ጋር ነው አብረን የምንኖረው? እንባ እየተናነቃቸው በአይናቸው ያዪትን እና በስፍራው ተገኝተው ያናገሯቸውን ተራፊ የጦር ክፍሎች ጉዳይ ሲነገሩ ጄ/ባጫ እንባ እየተናነቃቸው ነው። እጅግ የሚያሳዝን ነው። አማራ ተለይቶ በተጠና መልኩ መረሸኑ ምን ያህል ይህ ሃይል አበረን እንኑር እያለ በፍቅር የሚለምነውን ህዝብም መርዝ እንደሚያበላው ያሳያል። የተሰራው ግፍ ታሪክ የማይረሳው ነው። እኔ ዶ/ር አብይን ብሆን ለትግራይ ህዝብ መመሪያ በመሰጠት ወያኔ የሚተማመንባቸው የማሰልጠኛና የትጥቅ፤ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረት ሁሉ በምድርም በሰማይም በማጥቃት ማውደም ነው። ይህ ጦርነት በተጓተተ ቁጥር ሌሎች ሃይሎች ይገቡበትና ሶርያ መሆናችን አይቀሬ ነው። እጅግ በፈጠነና በተቀናጀ መልኩ ሊመቱ ይገባል። ያለበለዚያ አዲስ አበባ ላይ በሰው ሬሳ ሲጨፍሩ እናያለን። ወያኔ ድርቡሽ ነው። ማንንም ማመን ጭራሽ አይቻል። ሶስቱ የቀድሞ የወያኔ ጄኔራሎች አስቀድመው ጥቃት እንደሚደርስ ያውቁ ነበር። ግን ከሃገር ይልቅ የፓርቲ ምስጢር በመያዝ ጦርነቱ ከመከሰቱ በፊት ሃገር ጥለው ነው የወጡት። ጭራሽ አይታመኑም። የዘር ልክፍቶች ናቸው። እንደ አራዊት በዘሩ አስቦ የሚሰለፍ የእብድ ጥርቅም። ከእነዚህ ጋር ነው እርቅ የሚደረገው? ዶ/ር አብይ አብዶ ካልሆነ ከእነዚህ ጋር እርቅ ቢያደርግ ጦሩ ይነሳበታል። የግፍ ግፍ ነው የተሰራው። ለወያኔ ማዘን ራስን ለማጥፋት ካለሆነ ጥቅም የለውም። አይለወጡም። ሞት ለወያኔ። እጅግ እጅግ ያሳዝናል። በዘር በተጠና ሁኔታ ስንት የድሃ ልጆች ረገፉ! በቃኝ!

  2. እንደው በማርያም “በጦርነት” ላይ ላለ መንግስትና መሪ እንዲህ ዓይነት “ድጋፍ” እና “ማስፈራሪያ” የተቀላቀለበት መግለጫ ይወጣል ? በአጭርና ብግልጽ ቋንቋ “ወያኔን በቀኝ ቡጢ፤ አቢይን በግራ ቡጢ”፤፤ ወይ ዲያስፖራ ! ያለው ማን ነበር?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.