ከአፋኙ የህወሓት ቡድን ነጻ የወጡ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለጹ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ ጥቃት ለመፈፀም እና ሰላም ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የሚያደርገውን ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ከቂርቆስ ወደ ቄራ አቅጣጫ በምሽት ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2A-41649 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ በክፍለ ከተማው ወረዳ 4 በተለምዶ 31 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲደርስ ነበር ለፍተሻ እንዲቆም በፖሊስ አባላት የተጠየቀው፡፡
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ እንደገለፁት፣ በተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገ ፍተሻ 4 የተለያዩ ሽጉጦች፣30 የክላሽ ጥይቶች ከነካርታው እና 39 የሽጉጥ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በዚህ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ 3 ተጠርጣሪዎች ከነተሽከርካሪው ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ አስረድተዋል፡፡
ከህወሃት በተሰጣቸው የጥፋት ተልዕኮ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት ለመፈፀም እና ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ አካላት ዕቅዳቸው እንዳይሳካ ለማድረግ ከህብረተሰቡ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ተባብሮ እየሰራ መሆኑን ያመለከተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

ከተማ ንጉስ፡- በምዕራብ ትግራይ የጸገዴ ወረዳ ነዋሪዎች የአገር መከላከያ ሰራዊት ከአፋኙ የህወሓት ቡድን ነጻ ስላወጣቸው ደስተቸውን ገለጹ።
በትግራይ ክልል ከተማ ንጉስ የተገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የአገር መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ከከሀዲው ቡድን ነጻ በመውጣታቸው ደስታቸውን መግለጻቸውንና የመከላከያ ሰራዊቱን በደስታ መቀበላቸውን ገልጸዋል።
ከሀዲው የህወሓት ቡድን የፌዴራል መንግስት ሊወረን ነው፣ የትግራይን ህዝብ በሀይል ሊያበረክክ ነው ሲል ቆይቶ ራሱ ቀድሞ በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት መፈጸሙ የሚወገዝ ተግባር ነው የጸገዴ ወረዳ ነዋሪዎች፤ ይህ የሚሳየው ከላይ ያለው የህወኃት ቡድን ለራሱ ጥቅም እንጂ ለህዝብ ደንታ እንደሌለው ነው ብለዋል፡፡
124331877 1814334152051258 6859882388362425768 n
የጸገዴ ወረዳ የከተማ ንጉስ ከተማ ነዋሪ አቶ ስምረት አቦይ እንደገለጹት፤ ከሀዲው የህወሓት ቡድን አፋኝና ለህዝብ ደንታ የሌለው ነው፡፡ ቡድኑ ለትግራይ ህዝብ እኛ ጦርነት አንገጥምም ራሳችን ብቻ የምንከላካለው እያለ ሲያታልል ቆይቶ ቀድሞ ራሱ በአገር መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተው ጥቃት የምናወግዘው ተግባር ነው ብለዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ ከጦርነት የሚያተርፈው ነገር የለም ያሉት አቶ ስምረት ከሀዲው የህወሓት ቡድን ለህዝቡ የሚነግረውና የሚፈጸመው ተግባር ለየቅል ነው ያሉት አቶ ስምረት፤ ህዝብ የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያነሳ የሚያሰር፣ የሚያገላታ፣ ጫናና አፈና የሚፈጸም በመሆኑ ከዚህ አፈና በአገር መከላከያና በአማራ ልዩ ሀይል ነጻ መውጣታቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡
124192624 1814334148717925 4135136183621782529 n
የአገር መከላከያ ሰራዊት ከህወሓት ቡድን ነጻ ስላወጣን ደስተኞች ነን ያለችው በጸገዴ ወረዳ የከተማ ንጉስ ከተማ ነዋሪ ወጣት ከተማ ከፍያለው፤ ይህን ደስታችንንም ሰልፍ በመውጣት ጭምር አረጋግጠናል፤ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በነሱ ተላላኪ ሰዎች አማካኝነትም ህዝቡ እርስ በእርሱ በጥርጣሬና በአይነ ቁራኛ እንዲተያይ፣ የፈለገውን ሀሳብ እንዳይገልጸ ሲያደርጉ እንደነበር ገልጻለች፡፡
“ህወሓት የፈለግነውን ሙዚቃ እንኳን እንዳንሰማ ያደርግ ነበር፤ የመብት ጥያቄዎችን ስናነሳ ሲያስረንና ሲያንገላታን ነበር ያለቸው ወጣቷ፤ የመከለከያ ሰራዊት ጸገዴ ወረዳን መቆጣጠሩ ነዋሪው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ተናግራለች፡፡
አሁን ከተማ ንጉስ ከተማ ሰላምና መረጋጋት መስፈኑንና ህዝቡ መደበኛ እንቅስቃሴውን መጀመሩን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ ታዝቧል።
በጌትነት ምህረቴ
(ኢ.ፕ.ድ)

2 Comments

  1. ብራቮ መከላከያ ሰራዊት፡፡ የታፈነ ህዝብ ጊዜው ሲደርስ የልቡን መናገሩ አይቀሬ ነው፡፡ በህዝብ መቀለድ እስከመቼ፡፡

  2. ጌትነት ምህረቴ ቸኩለህ የጻፍከዉን ጸሁፍ እርምት አድርግበት አዉቀህ ካልሆነ የተለቀቀዉ ክልል የትግራይ ሳይሆን የአማራ ነዉ ይህን አርእስት የምትሰጠዉ መቀሌና አክሱም ደስታቸዉን ሲገልጹ ነዉ ተሳስተህ ሰዉ አታሳስት

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.