በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የነበሩ ሁለት የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

123795649 4643794072359429 1847302002754453158 n

1. ህንፃ ተክለብርሃን ይባላል። የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 (መርካቶ) ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበረ በኃላ በእድገት የክፍለ ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበረ ነው።
2. ገ/ትንሳኤ ዓርአያ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበረ በእድገት የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበረ በቅርብ ጊዜ ከአመራር የተቀነሰ ነው።
ህብረተሰቡም ካሁን ቀደም ህዝብን እናገለግላለን በማለት ከተማችንን የእኩይ ተግባራቸው ማስፈጸሚያ ስፍራ ለማድረግ ከሚጥሩ ጸረሰላም አካላት
በመራቅ የተለዩ እንቅስቃሴዎችን በተለይ በአገልግሎት መስጫ ተቋማት ፣ በሆቴሎች ፣በመዝናኛ ስፍራዎች እና በትራንስፖርት ስፍራዎች አጠራጥሪ ነገር ካጋጠመ በአካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ እና የጸጥታ አካል ማሳወቅ ይገባል፡፡
በተጨማሪ በተለያዩ አደረጃጀት የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት አባላት፣የታክሲ ተራ አስከባሪ እና የጫኚ እና አውራጅ ማህበራት ፣የፓርኪንግ ሰራተኞች የጸጥታ አካል ጋር አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የከተማችችን ሰላም በመጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል፡፡
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሰክሪተሪ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዘ-ሐበሻ ዕለተ አርብ ዜናዎች

1 Comment

  1. የቀድሞ ከንቲባ ታከለ ኡማን ሊገድሉ ሲያሴሩ የተያዙት አሸባሪዎች አሁንም ከንቲባ አዳነች አበቤን አስገድለው በከተማችን ሽብር ለማስነሳት ወደ ኋላ ስለማይሉ ህዝቡ በንቃት ሊከታተላቸው እና የነዳጅ ሚንስቴር ታከለ ኡማንም ሆነ የከንቲባ አዳነች አበቤን እስትንፋስ ለማቆየት በቁርጠኝነት ነቅተን መታገል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሙሉ ግዴታችን ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.