ለሙሉ-ዓለማችን ስንል ተመልሰናል !!

unnamed 5ባለፉት ሦስት ቀናት እንቅልፍ አልባ ለሊቶችን ሳሳልፍ ዳንሻ ላይ በከሃዲው ቡድን ከበባ ተፈጽሞበት ሀገራዊ ተልዕኮውን በመስዋዕትነት ለማሳመር ሲፋለም የሰነበተው መድፈኛው ብ/ጀኔራል ሙሉዓለም ጉዳይ እጅግ ያሳስበኝ ነበር።

ሦስት ቀናት ሙሉ ከበባ ውስጥ ሆኖ በቆራጥ አመራር ሲያዋጋ የሰነበተው ጀኔራል ሙሉዓለም ከኋላ የደረሰለት የመከላከያ እና የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ (Popular Force) ከበባውን ሰብሮ ደርሶለታል።

እነሆ ትላንት ምሽት ከወድሞቹ ከነ ኮሎኔል አለበል አማረ፣ ኮሎኔል ባምላኩ አለበል ጋር  የድል ፎቶ ተነስቶ ስመለከት ልቤ አረፈ!

የሰውዬው ቆራጥ ታጋይነት፣ የብሔር ማንነቱ እና የተወለደበት አካባቢ በከሃዲው ትሕነግ እጅግ እንዲፈራና እንዲጠላ አድርጎታል። የኔም የሦስት ሌሊቶች ሃሳብ ይህ ነበር። በርግጥ ጀኔራል ሙሉዓለም የከሃዲው ቡድን የከበባ ጥቃት ተሳክቶ የከፋው ቢመጣ  እጅ እንደማይሰጥ የምናውቅ እናውቃለን! ፈጽሞ እጅ መስጠት ያደገበት ባህል አይደለምና!!

ለዚህም ነው ጄኔራሉ <<ደሜን ትጠጣለህ እንጅ፣ እጄን አትጨብጣትም>> ሲል የመጀመሪያው ቀን  ከበባ ውስጥ ሆኖ በውድቅት ለሊት በማይክራፎን መልዕክት ያስተላለፈው

የሦስቱም ቀናት የሬዲዬ መገናኛ መልዕክቶቹ ለታሪክ የሚቀመጡ ናቸው። ወደፊት ጀኔራሉ ከፈቀደ ታሪኩን እኔ ነኝ የምጽፍለት።
~~
የመድፈኞች መሃንዲስ፣ የሜካናይዜሽኑ ጠበብት የመይሳው ልብ ወራሽ ጄኔራል ሙሉዓለም እናከብርሃለን! ኢትዮጵያ ባንተ ትኮራለች!

ሞት ለከሃዲው እና የእናት ጡት ነካሹ ትህነግ!
ድል ለመከላከያ ሠራዊታችን!!

(ከሁለተኛው ጠቅላይ ሰፈር የተከተበ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.