ከኢትዮጵያ የበለጠ መሳሪያ ታጥቀናል” ሲሉ በእብሪት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ደንፍተዋል

debre 3ሁለት ነገርም ሊሆን ይችላል። አንድ ነገር ግን በደንብ ጠርቷል። እሱም ሕወሓት የጦርነቱ ተንኳሽ መሆኗ ነው። በእርግጥ ይህንን የሕወሓት ትንኮሳ አስቀድመው የነገሩን ጠቅላይ ሚንስ ትር ዐብይ አሕመድ ናቸው።

“ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል” ነበር ያሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገሩን ቀለል አድርገው። አክለውም እንዲህ አሉ

“የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል። ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል”

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተነገሩት ቃል እውነት መሆኑን ሕወሓት አረጋግጣለች፦ በሊቀመንበሯ በኩል። የሕወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረ ሚካኤል “በሰሜን እዝ ስር የነበሩ ጠቅላላ መሣሪያዎች በትግራይ ልዩ ኃይል ቁጥጥር ስር ውሏል” ሲሉ ወረራው በሕወሐት ኃይሎች መካሄዱን በአንደበታቸው አምነዋል። ከዚህም በላይ ሄደው “ከኢትዮጵያ የበለጠ መሳሪያ ታጥቀናል” ሲሉ በእብሪት ደንፍተዋል። ይገርማል

ሁለት፤ ይህም ሆኖ ዶክተር ደብረጽዮን ከቀናት በፊት በሰጡት መግለጫ “የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራው ኢሳያስ ጋር በማበር ጦርነት ከፍቶብናል” ብለው ነበር። በዛሬው መግለ ጫቸው ደግሞ ኤርትራውያን ከጎናቸው እንደተሰለፉ አድርገው ነው የደሰኮሩት። ይህንን በተመለከተ የተናገሩትንና የትግራይ ቴሌቪዥን ተርጉሞ ያስተላለፈውን ቃል በቃል እነሆ

“ጎረቤት ክልሎች ከትግራይ ሕዝብ ጋር አታጣሉን እያሉ ነው ያሉት። እኛም ከጎረቤት ክልሎች ጋር ሆነን እንሰራለን፤ ይህንን ስርዓትም እንገጥመዋለን። ባለፈው ለኤርትራውያን ባደረግነው ጥሪ የኤርትራ ሕዝብ እና ሰራዊቱ ጥሪአችንን ተቀብለው የሰጡት ምላሽ የሚደነቅ ነው። ስለዚህ ማመስገን እፈልጋለሁ። ‘ሕዝቡም ከትግራይ ሕዝብጋ አታዋጉን በሰላማዊ መንገድ ችግሮቻችሁን ፍቱ’ እያለ ነው ያለው። ወጣቱ ከዚያም አልፎ ‘ከትግራይ ሕዝብ ጎን እንቆማለን፣ የትግራይ ሕዝብ አይመታም’ በሚል ያሳዩትን አቋም፤ ከውጭ ያሉ ኤርትራውያንም ከልብ ነው የማመሰግነው።”

ይህ የመግለጫ ክፍል ብቻውን የሚያስቅ ነው። የትኛው ጎረቤት ክልል ይሆን ከትግራይ ክልል አታጣሉን ያለው? ጎረቤት ክልል የሚባለው የታወቀና የምናውቀው ነው። ኤርትራ ደግሞ ጎረቤት ክልል አይደለችም፦ ጎረቤት ሃገር እንጂ። እንዲያም ሆኖ የኤርትራን እና የኤርትራውያንን ፖለቲካ እና የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያውቅ ሁሉ ይህንን የደብረጽዮንን ቃል ሲሰማ በሳቅ መንከትከቱ አይቀርም። ይታያችሁ፤ የኤርትራ ወጣት ከሕወሓት ጎን ሲሰለፍ

የሆነ ሆኖ የደብረጺዮን ዲስኩር የሕወሓት ሰዎች ቢሸነፉ “ማለፊያ ሊኖረን ወይም ልናገኝ የሚችለው በኤርትራ በኩል ተሹለክልከን ስለሆነ ሕዝቡን እንሸንግለው” ከሚል እሳቤ በመነጨ የማርያም መንገድ እያፈላለጉ እያመቻቹ ሊሆን ይችላል ያሰኛል። ብቻ የጦርነት ጊዜ ፕሮፓጋንዳ፤ መቀባዠር እና መቃዠት ጭምር እንደሆነ ይህ የደፂ ንግግር የሚያሳይ ይመስለኛል።

(ወሰን አየሁ)

2 Comments

  1. እሰይ ስለቴ ሠመረ!!!
    ህልሜ እውን ሊሆን ነው ተመስገን አምላኬ!!!
    በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም ማለት ይህ አይደለም እንዴ ሰዎችዬ!!!

  2. “አምባ ገነኖች ሲፎክሩ የፍርሃታቸውን ነው፤” ይሉ ነበር የኔታ መስፍን (ነፍሳቸውን ይማረውና)፤፤ ደጺ መጨረሻው ወይ [ጀግና ከሆነ] ራሱን ማጥፋት ወይም አብዲ ኢሌን መቀላቀል ነው፤ ካላስ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.