በቅራቅር አካባቢ አንፃራዊ ሰላም ቢኖርም የመንግስት መሥሪያ ቤቶች አልተከፈቱም

Tigray 1በአማራ ክልል ጠገዴ ወረዳና በትግራይ ክልል ፀገዴ ወረዳ አዋሳኝ ቦታዎች የነበረው ግጭትን የመከላከያ ሰራዊት ቢቆጣጠሩትም የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ሥራ እንዳልጀመሩ ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡
አንድ ጠገዴ ወረዳ ቅራቅር ከተማ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ (DW) በስልክ እንደተናገሩት አሁን በአካባቢው የተኩስ ድምፅ እንደማይሰማ ገልፀው በከተማዋ ሰዎች በሰላም እየተዘዋወሩ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
ይሁን እንጂ በጠገዴ ወረዳ ቅራቅር ከተማ አሁንም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ግጭቱ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ዝግ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
የወረዳውን አመራር አስተያየት ለማካተት ብንሞክርም መረጃ የሚሰጠው ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች በጋራ ነው በማለታቸው አልተሳካም፡፡
ይህ በአንዲህ እንዳለ፦ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማና በትግራይ ክልል አላማጣ ከተማ መካከል መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን አንድ የቆቦ ተማዋ ነዋሪ ገልጸዋል፡፡ ነዋሪው እንዳሉት መደበኛ የትራንስፖርት ባይኖርም ከሁለቱም ከተማዎች ሰዎች በእግራቸው ከአንዱ አቅጣጫ ወደ ሌላው አቅጣጫ እንደሚንቀሳቀሱ አብራርተዋል፡፡
ከማክሰኞ አነጋግ ጀምሮ መብራት እስከ ረቡዕ ምሽት ተቋርጦ እንደነበርና ከመጣ በኋላም እንደገና ወዲያውኑ ጠፍቶ ዛሬ ጠዋት ቢመጣም ኅብረተሰቡ በዚህ ምክንያት ትክክለኛ መረጃ ማግኘት አልቻለም በተንቀሳቃሽ ስልክም ግንኙነት ተቋርጦ ቆይቷል ብለዋል፡፡
አስተያየት ሰጪው አያይዘውም ባለፉት ሁለት ቀናት የባንክና ሌሎች አንዳንድ ተቋማት መደበኛ ሥራቸውን መሥራት ተስኗቸው መቆየታቸውን አመልክተዋል፡፡
በቆቦ ከተማ ባንኮች ዛሬ መከፈት ቢችሉም ሙሉ አገልግሎት አይሰጡም ያሉት እኝሁ የዐይን እማኝ ሰዎች በገንዘብ ማውጫ ካርድ ገንዘብ ሲያወጡ መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
ዛሬ የቆቦ የገበያ ቀን እንደሆነ ያመለከቱት ነዋሪዎቹ እንደበፊቱ የደመቀ ባይሆንም ገበያተኞች እየተገበያዩ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
የፀጥታ ኃይሉ ከቀድሞው ባልተለየ ሁኔታ በከተማዋ እየተዘዋወረ ጥበቃ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡ ኅብረተሰቡ ከመብራት መቋረጥ ጋር በተያያዘ በቴሌቪዥንም ሆነ በኢንተርኔት የተሟላ መረጃ ባለማግኘቱ ተጨባጭነት በሌላቸውና ሥጋት በሚፈጥሩ ወሬዎች ውጥረት የሚገቡ ሰዎች አሉ ብለዋል፤ ሆኖም እንደሚዲያ ባለሞያ ወሬዎቹ መሰረት የሌላቸው እንደሆኑም አስተያየት ሰጪው ገልፀዋል፡፡ አሁን ቆቦና አካባቢው አንፃራዊ ሰላም ያለበት አካባቢ እንደሆንም አረጋግጠዋል
ዘገባ፦ ዓለምነው መኮንን ዶይቸ ቬለ (DW) ባሕርዳር
DW
ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: ጄኔራሎች በምደባ ስም እየተበወዙ ነው

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.