የትግራይ ተወላጆች የሆኑ የብሄራዊ ጸጥታና ደኅንነት ተቋማት ሠራተኞች በግዳጅ ዕረፍት እንዲወስዱ መደረጉ ተሰምቷል

addis ababaየትግራይ ተወላጆች የሆኑ የብሄራዊ ጸጥታና ደኅንነት ተቋማት ሠራተኞች በግዳጅ ዕረፍት እንዲወስዱ እንደተደረጉ ዋዜማ ሰምታለች፡፡ በተያያዘ፣ በአውሮፕላን ወደ ውጪ ሀገራት ጉዞ የነበራቸው የትግራይ ተወላጅ መንገደኞች መታወቂያቸው እየታየ እና ብሄራቸውን እየተጠየቁ ከጉዟቸው እንዲቀሩ እና ወደቤታቸው እንዲመለሱ መደረጋቸውን ዋዜማ ድርጊቱ ተፈጽሞብናል ካሉ ምንጮች ሰምታለች፡፡ ዋዜማ በጉዳዩ ላይ የመንግሥትን አስተያየት ለማግኘት እየሞከረች ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በሱማሊያ ከአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ውጭ በተናጥል የሠፈሩ ወታደሮቹን ማስወጣት እንደጀመረ ዋዜማ ከአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል ምንጮቿ ሰምታለች፡፡ ወታደሮቹ የተጠሩት የሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል ጸጥታ ሃይል ጋር የገባበትን ግጭት እንዲያግዙ ነው፡፡ ከባድ ጦር መሳሪያ የታጠቁ ወታደሮች የኢትዮጵያ አዋሳኝ ወደሆነችው የሱማሊያዋ ጌዶ ግዛት ተመልሰዋል፡፡ በተያያዘ፣ የሱማሌ ክልል ልዩ ሃይል ወደ ኢትዮጵያ-ሱማሊያ ድንበር ተጠግቶ ድንበር እየጠበቀ እንደሆነ ታውቋል፡፡

በመከላከያ ሠራዊት እና በትግራይ ክልል ታጣቂዎች ሃይሎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ለማስቆም አፍሪካ ኅብረት ከመጋረጃ ጀርባ የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እንዳልተቀበሉ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በተያያዘ፣ ከዛሬ ጧት ጀምሮ በትግራይ-አማራ ድንበር የመድፍ እና ጥይት ተኩስ ይሰማ እንደነበር እና በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ በአብደራፊ ከተማ 24 ያህል ቁስለኛ ወታደሮች ሕክምና ሲሰጣቸው ምንጮች መመልከታቸውን ሮይተርስ ጨምሮ ጠቅሷል፡፡ ቁስለኞቹ ከየትኛው ወገን እንደሆኑ ግን ምንጮች ማረጋገጥ አልቻሉም ብሏል፡፡

ዋዜማ

1 Comment

  1. ‘Collective thinking is like digging a mass grave” ያለው ማን ነበር?
    ለሰራትኞቹም ቢሆን ጥሩ መሰለኝ፤፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን መሆኑን ቢያምኑበት እንኳ የቀድሞ ‘የደም” አለቆቻቸው ላይ ይጨክናሉ ብሎ ማመኑ ይከብዳል፤፤ ባይሆን “እዚህ ደረጃ በመድረሳችን እናዝናለን፤ ትረዱናላችሁ ብለን እናስባለን”፤ ብሎ በጽሞና ለማስረዳት መሞከር ነው፤፤ ጫካ በነበሩ ጊዜ የነበረውን የወያኔ አሰራር ለሚያስታውስ ሰው ምንም ሊገርም አይገባም፤፤ ወያኔዎች እኮ “የሚያስረግዝሽን ወንድ ምረጭ” ብለው ተጋዳልይት አስረግዘው፤ ለስለላ አዲሳባ ድረስ አሰማርተው ነበር፤፤ ጭራሽ ጀብድ አርገውት “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” በሚለው መጽሃፍ ዉስጥ ምንም ሳያፍሩ የጻፉ ሰዎች መሆናቸውን አንርሳ፤፤
    There is NO room for error this time around. አገር ሲረጋጋ ይቅርታ ትጠይቀው ይመለሳሉ፡፤

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.