የመከላከያ ሠራዊት ሕዝብ እንዳይጎዳ የህወሓት ጽንፈኛ ኃይልን ለይቶ ለመምታት በጥንቃቄ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጀነራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ

123767864 1171437993253837 8100868720057005706 o
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹም እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ሓላፊ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ በሰጡት መግለጫ፣ ማክሰኞ ከምሽቱ 4:00 ላይ ትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ የራሳችን መንግሥት አካል በሆነው በጽንፈኛ የሕወሓት ኃይል ጥቃት ደርሶበታል ብለዋል።
መከላከያ ይህን መሰል ጥቃት ይፈጸማል የሚል ግምት አልነበረውም ያሉት ጀነራሉ የሠራዊቱ ተልዕኮ ሕገ መንግሥቱ ከሚፈቅደው ውጭ የሚንቀሳቀስ ኃይል ላይ እርምጃ መውሰድ እንደነበር አስታውቀዋል።
ከኤርትራ ጋር ያልተቋጨ የድንበር ጭቅጭቅ ስላለበት ይህ ይመጣል ብሎ ያላሰበው ሠራዊቱ በፅንፈኛው ሕወሓት ቡድን ጥቃት ደርሶበታል ብለዋል።
የትግራይ ሕዝብ ይህንን ጥቃትአልቀበልም ብሎ ከመከላከያ ሠራዊቱ እና ከመንግሥት ጎን መሆኑን ማሳየቱንም ጀነራል ብርሃኑ ተናግረዋል።
ጥቃት ለደረሰበት ለመከላከያ ሠራዊታችን ድጋፍ የሚሰጥ ኃይ ወደ ቦታው መንቀሳቀሱን የጠቃት ጀነራል ብርሃኑ ጁላ፣ እንዲዋጋ ተልእኮ የተሰጠው ኃይል ተገድዶ ወደ ጦርነት እንዲገባ ተገዷል ብለዋል።
ሠራዊቱ አርሶአደሩን ሰብል በመሰብሰብ እና አንበጣን በመከላከል ድጋፍ እያደረገ ባለበት ወቅት የህወሓት ጽንፈኛ ኃይል ጦርነት መክፈቱ ለሕዝብ ደንታ የሌለው መሆኑን ጀነራሉ ገልጸዋል።
“በአሁኑ ወቅት የተገጎዱት ከሁሉም ወገን ህክምና እያገኙ ነው፤ አንዳንዶቹም እያመለጡ ወደ ሠራዊታችን እየገቡ ነው” ሲሉ በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።
“አገራችን ያላሰበችው ዓላማ የሌለው ጦርነት ውስጥ ገብታለች፤የትግራይ ወጣት በዚህ ዓላማ ቢስ ጦርነት ውስጥ መግባት የለበትም፤ ኢትዮጵያ ስትኖር የትኛውም አካባቢ ተንቀሳቅሶ መሥራት፣ ማደግ ይችላል”ሲሉ ተደምጠዋል።
የመከላከያ ኃይሉ ሕዝብ እንዳይጎዳ ለማድረግ ሕዝብ እና ጽንፈኛ ኃይሉን ለይቶ ለመምታት በጥንቃቄ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል።
የመከላከያ ሠራዊቱ የትም አይሄድም፣ ጦርነቱ እዚያው ያልቃል ሲሉ ጀነራሉ ገልፀዋል
#EBC

1 Comment

  1. “የትግራይ አለመግባባት ጉዳይ በህግ ነው የሚፈታው” ከሚለው ዜቤ የተሻለ ሌላ means የለም!
    ሰራዊቱ አንበጣን በመከላከልና የመሳሰሉት ተግባራት ዘንዳ እውነትም ተሰማርቶ ከሆነ፣ በርግጥም የጀግንነት ተግባር ነው::
    ባድመን በሚመለከት፣ ያ የሃይለስላሴ መንግስት በሱዳን በኩል አዟዙሮ ባርካ ውስጥ ወደ ጀብሃ ያሰረገው ዘላለሙን ቂመኛም ቢሆን፣ የባድመ ችግር ኢትዮጵያን የመዝረፍ ኤኮኖምያዊ ችግር እንጂ፣ የመሬት ችግር አለመሆኑን ቀደም ሲል በቁሙ እያለ ተናዟልና፣ you don’t need to mention this trash point anymore! ከዚህም በላይ ደግሞ የባድመ theoretician እና ተሸክሞ አልጀርስ/ዘሄግ አድራሹው ኣይተ መለስ ዜናዊም የለም፣ ተላላኪው ‘ኤርትራዊው’ ስዩም መስፍንም ለአዲስ አበባ መግቢያ ትኬት ስላሌለው የት ሆኖ ውስጠ ሚስጢራዊ አባባሉ “አሸንፈናልና ጨፍሩ” ብሎ ሊወሰልት ነው?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.