ከአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር የተላለፈ መልዕክት !

123552607 1170356130028690 2475554894099065441 nላለፉት ሶስት አስርት አመታት የአማራ ህዝብ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ እንዲጠላ የተሳሳተ የታሪክ ትርክት በማዘጋጀትና ህገ -መንግስታዊ ስርዓትን በማዘጋጀት ለመከራና ለፍጅት የዳረገው ፣ ለም እና የአባቶቻችን እርስት የሆኑትን ወልቃይት ፣ጠለምትና የራያ መሬቶችን በሀይልና በአምባገነን ስርአት የነጠቀው እንዲሁም ኢትዮጵያን የትርምስና የክፍፍል ሀገር ያደረጋት እብሪተኛው ቡድን ህውሃት ወያኔ በትናንትናው ምሽት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት አድርሷል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በአማራ ህዘብ የትግል መሪነት ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በአደገኛ ትርክታቸው በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ዘር ተኮር የሆነ አማራን የማጥቃትና ሀገር የማፍረስ ትልማቸውን ሊያሳኩ ረጅም ጉዞ ሄደው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ድንበሮችና በመከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ የተፈጠረውን ጥቃት ተከትሎ መንግስት በሚያደርገው ወታደራዊ እርምጃ የህውሃት ወያኔን ግብዓተ መሬት እንዲፈፀም ድጋፍ የምናደርግ ሲሆን መላው የአማራ ህዝብና ወጣት ትህነግን ለማባረር የነበረን ፍፁም የሆነ አንድነት በዚህ ሰዓት ከየትኛው ጊዜ በላይ የሚስፈልገን መሆኑን እያሳወቅን፦
1) ትህነግ የግጭት አቅጣጫ ለማስቀየርና የሀይል ሚዛን ለመበታተን ፣ የብሔር ግጭት ለመፍጠር እንዲሁም የእምነት ተቋማት ላይ ጥቃት የማድረስ እንቅሰቃሴ ለማድረግ የምትችልበት ሁኔታ ስለሚኖር ሁላችንም የአማራ ህዝብና ወጣቶች በመደራጀት አካባቢያችንን በንቃትና በትኩረት እንድንጠብቅ ፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ሌሎች የፀጥታ አካላት ከማህበረሰባችን ጋር አንድ በመሆንና ትክክለኛ መረጃን በመለዋወጥ አካባቢያችንን ክልላችንና ሀገራችንን እንድንጠብቅ ስንል ጥሪ እናቀርባለን።
2) የአማራ ህዝብ አንድነትን በተመለከተ ከፋፋይ አጀንዳዎችን ይዛችሁ የምትፅፉ ምንደኛ አክቲቪስቶች ህዝባችን ትኩረቱን የምንግዜም ጠላቱ ከሆነው ትህነግ ወያኔ እንዳያደርግ እየሰራችሁ በመሆናችሁ እናንተን ከባንዳው ህውሃት ለይተን የማናያችሁ መሆኑን እንድትገነዘቡና ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ ስንል እናሳስባለን።
3) በመጨረሻም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ለሀያ ሰባት አመት ሀገራችንን በዘር ሲከፋፍል፣ ሲዘርፍና ሲገድል የነበረው ወንበዴው የህወሃት ወያኔ ቡድን በቀጥታ የጦርነት አዋጅ አውጆ አገራችን ላይ ግልፅ ጦርነት የከፈተ ስለሆነ ሀገራዊ አንድነታችንን ጠብቀን ይሄንን ባንዳ ሀይል ላይመለስ እስከመጨረሻው ለመደምሰስ በአንድነት እንቁም ስንል ጥሪ እናቀርባለን ።
የአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር
ጥቅምት 25 /2013
ጎንደር , አማራ ,ኢትዮጵያ !

1 Comment

  1. የአማራ ወጣት እንዳትዘናጋ ትግሬና ኦሮሞ በቅንጅት ተንኮል ደቅነዉብሃል። ፕሮፌሺናል ሰራዊት ለዉጊያ የሰለጠነ እያለ እራስህን ለጦርነቱ አትማግድ ለአማራ ያለኸዉ አንተ ነህ። ለጊዜዉ የኦሮሞ ሹሞች እና የትግሬ ሹሞች በግል ባላቸዉ ቁርሾ አማራዉን ሊማግዱት ይፍልጋሉና የግምባር ስጋ አትሁንላቸዉ ለወገንህም ይህንኑ አስረዳ አንተ አካለ ጎደሎ ከሆንክ በሗላ ይስቁብሀል አያዝኑልህም። ከአማራዉ የተነጠቀዉን መሬት ያለመታከት ከወገንህ መክረህ በተጠንቀቅ ጠብቅ የተቀማኸዉን ሳትዘነጋ። የጊዜዉ ጉዳይ ነዉ እንጂ ትግሬ በርሮ ይጠፋል። እሰከዛዉ በጽናት ቁሙ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.