ታሪክ ራሱን ይደግማል ፤ዛሬ ተደጋግሟል! –  ማላጂ

ከ 1983 ዓ.ም በፊት በቀድሞዋ ታላቋ ኢትዮጵያ  የሩቅ እና የቅርብ ጠላት በከፈቱት የዉክልና ጦርነት የአገሪቷን ልዑላዊነት ለማስከበር እና ዳር ድንበሯን ለመከላከል በተደረገ የረጅም ዓመታት ጦርነት ከፍተኛ የሠዉ ህይወት እልፏል፣ ሀብት፣ ንብረት ወድሟል፡፡

ይህ ከዚህ በላይ የተከናወነዉ አገርን የመታደግ ጥረት አገሪቷን እና ህዝቦቿን ከ1983.ዓ.ም ጀምሮ አስካሁን ያስተናገዱትን ወደር አልባ አሳር እና ፍዳ  ማለትም  በሠባዊ መብት ጥሰት ፣ ማህበራዊ አስተዳደር አድሎ ፣ ምጣኔ ሀብታዊ ፣ ፖለቲካዊ ችግር ይህም በድምር ኢፍትሃዊ የመንግስት አስተዳደር ከጅምሩ ስለተገመተ ከምንጩ ለማድረቅ እንደነበር ከትናንት ታሪክ እና ከዛሬ ሁነት መረዳት ይቻላል ፡፡

Ethiopiaሆኖም ይህ ለአንዲት ሉዓላዊት አገር ህዝቦች አንድነት እና የጋራ ጥቅም ሲባል ከተካሄደዉ  የ17 ዓመት ጦርነት በላይ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ከፍተኛ የሠዉ ህይወት እና ብሄራዊ ሀብት  ጥፋት እና ዉድመት የተመዘገበበት ግልፅ መነሻ እና መድረሻ ያልነበረዉ በድንገት ተጀምሮ ለዓመታት ያልተቋጨ ነበር ፡፡

ይህም ሰዶ ማሳደድ  “ ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለዉጥ ”  ከፍተኛ ሠባዊ እና ቁስ አካላዊ ቀዉስ ያስከተለ የኢትዮ ፤ኤርትራ ጦርነት በባዶ ከባዶ ተጀምሮ በባዶ የሚገኝ የህዝብ እና አገር ጥቅም እና መብት ሳይሆን የግል እና ቡድን የምኞት  ጦርነት ሆኖ በታሪክ የሚታወስ ነዉ  ፡፡

ይህ ጦርነት የስንቱን ቤት እንደዘጋ ፤ስንቱን ያሞራ ቀለብ እንዳረገ ሲታይ በአገራችን ጦርነቱ ለአገር ሉዓላዊነት እና ህዝብ ደህንነት ሳይሆን ከዚህ በተቃራኒ ለሆነ የስልጣን ማጠናከሪያ እና መከለያ ለመሆኑ የሚስተዋል የቅርብ ጊዜ እዉነት ነዉ ፡፡

በዚያን ዘመን የነጻነት ትግል አራማጆች እና ዛሬም በዳግም ነጻነት ትግል ስም በህዝብ እና አገር ኪሳራ የሚኖሩት ምኞታቸዉ ራሳቸዉን ባቋራጭ በፈጠሩት እና በተጣባቸዉ የበታችነት እና የምቀኝነት ስሜት እና ባርነት ስለነበር ለህዝብ እና አገር ምንም ዓይነት ክብር እንዳልነበራቸዉ ከዚያን ጊዜ አስካሁን የሚያሳዩት ጥላቻ፣ ንቀት እና ድርጊት ዋቢ እማኞች ናቸዉ ፡፡

ያኔም ዜጎችን ዘግናኝ እና አረመኔነት ባህሪ በሚገለጥበት አኳኋን በሽተኞችን ከተኙበት የህክምና ክፍል ፣ እናቶችን ከጓዳ ፤ ህጻናትን ከጨዋታ፣ አባዉራዉን ከተገኘበት እንደ እንደ ማገዶ እንጨት እየሰበሰቡ መማገድ ፣መግደል የትናንት እና ዛሬ  አልቦ-ነጻ ኢሰባዊነት ነዉ  ፡፡

በነጻት ትግል ስም ለግል ስልጣን እና ድሎት ሲባል ባልተለወጠ ሰባዊነት ኢ-ሠባዊ ድርጊት ሲፈጽሙ ከ1983 .ዓ.ም. አስከ ጥቅምት 25/2013 .ዓ.ም ድረስ የነጻ አዉጭነት የፖለቲካ ንግድ ምልክታቸዉን አግባብነት የሚጠይቅ አልነበረም፡፡

ይህ ነዉ ቅድመ ኢህአዴግን ከድህረ ኢህዴግ     አስከ በኩር ልጁ ብልፅግና የነበረዉን እና ያለዉን የነጻነት ስያሜ የሚለየዉ፡፡

ሆኖም ልጅ ብልፅግና በድንገት እና ሊታመን በማይችል አባት እና አዉራ ፓርቲ – ህዋህት- ትግራይ በሚገኝ ጦርኃ ሃይል  ሰፈር መዳፈር የተነሳ እዉነተኛ እና ገላጭ የቀደመ ስሙን (በቀደመዉ መንግስት የሚገለጥበት) ይህም ወደ ስልጣን ከመምጣቱም በፊት፣ ከስልጣን ዘመኑ አስካሁን ለሚፈጽማቸዉ  ዕኩይ ተግባር ይመጥናል ያለዉን ጥቅምት ፳፭ ቀን ፪ ሽ ፲፫ ዓ.ም. የኢትዮጵያ መንግስት በሠጠዉ ወቅታዊ መግለጫ “ከሀዲ እና የዕናት ጡት ነካሽ ”የሚለዉን የክት ልብሱን አከናንቦታል፡፡  

ይህን ታረክ ራሱን ይደግማል ሳይሆን ይደጋግማል ብንለዉ የሚሆን ይመስለኛል ይኸዉም የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መሪ ኮ/ል መንግስቱ እና አስተዳደራቸዉ በዚያ ዘመን እንደ ትንቢት ደጋግመዉ ይጠቀሙት የነበረዉ የአገር አንድነት ጠንቆች እና ወንበዴዎች መጠሪያ“ ከሃዲ እና ጡት ነካሽ ”እንደነበር በየትኛዉም ብሄራዊ ጉዳይ ላይ በተደረገ የመንግስት መግለጫ የድምጽ መልዕክት መረዳት የሚቻል እና የተገለፀ ሀቅ ነዉ  ፡፡  

ታሪክ ራሱን ከመድገም አልፎ ሲደጋግም ያየነዉ ደግሞ ዛሬ በአገራችን መሪዎች በተለያየ ሠዓት በተለያዩ ባለስልጣናት እንደወረደ ከሀዲ እና የናት ጡት ነካሽ የሚለዉ ቅድመ ኢሀዴግ መንግስትነት ስያሜ መስማት ከሁለት በላይ ሶስት ስለሆነ ነዉ ፡፡

ይህም የሚያሳየን ይዋል ይደር እንጅ “ስምን መላክ ያወጣል ” እንዲሉ ከ60 ዓመታት በፊት የተሰጠ መጠሪያ ዛሬ እንደተዳፈነ አሳት ሲገለጥ ለባለቤቱ የሚሰጠዉ ትርጉም መራር ቢሆንም ምግባር እና ተግባር (ስራ) በጎም ይሁን ሌላ ማዘግየት እንጅ ማስቀረት እንደማይቻል ዛሬ ጊዜዉ ደርሶ በአደባባይ ሲገለጥ ማየት ለየትኛዉም ግለሰብ፣ቡድን ወይም የህዝብ ወኪል በተለይም ለእኛ አገር አለን ባይ የፖለቲካ ድርጅቶች ጠቃሚ እና አስተማሪ በመሆኑ ከምንም በፊት በምግባር እና ተግባር ልቆ ከህዝብ እና አገር ፊት መቅረብ አኩሪ እና ተሻጋሪ መልካም ስም ሲያሰጥ በአጉል እና ድብቅ ፍላጎት ህዝብ እና አገር እየገደሉ በነጻነት ትግል ስም  በራሱ ህዝብ እና አገር ባርነት ለማስፈን ለሚተጋ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ተግባሩ ከትናንት አስከዛሬ ስለሚታወቅ ተመሳሳይ ዕጣ  ስለሚጠብቀዉ በይቅርታ እና በአዎንታ ሳይመሽበት ሊታረም ቢችል ለሁሉም ወገን የሚበጅ ይሆናል ፡፡

 

እናት አገር ምንጊዜም ትኑር !!!

2 Comments

 1. ዘሓበሻ፣ ጎልጉል፣ ወወዘተዎች፣ ባታስነብቡትም አንብባችሁ ትደብቁታላችሁና እነሆ የአስተዋይነት ምክር ልገሳ!

  ጦርነት ጥፋትን እንጂ ልማትን አያስከትልምና፣ ከመዋጋት ይልቅ መግባባት ይመረጣል!
  ጦርነት የሚባል ነገር ላንዴና ለመጨረሻው ጊዜ ተካሂዶ በድል ተደምድሟል፣ በነ ጀነራል ሓየሎም ኣርኣያና ጓዶቹ ተመርቶ መላ የትግራይ ህዝብ የተሳተፈበት የ17 ዓመታቱ የሽረ (ናቅፋ) – ህንድ ውቅያኖስ ጦርነት:: የኢትዮጵያ ህዝቦችን ከፊሎቹን በባርነት የመያዝና ሌሎችንም ለኮሎኒያሊስቶች ገምሶ ሻጮች የምኒልክ ልጅ ልጆችን ለዘወትሩ ለማባረር የተደረገውና በቂ የመነሾ ምክኒያት የነበረው ጦርነት፣ በርግጥ ውጤቱ የድሉ ባላባቶችን እነ ሓየሎምንና እነ በርሀ ሻዕቢያን እስከነ የትግል ጓዶቻቸው በባንዳ ልጆች አስገድሎ ሲያበቃ (አብዮት ልጆችዋን ትበላለች እንዲባል)፣ ከዚያም በባንዳ ልጆች ቁማር ተበልቶ ገቢው በውጭ አገር ባንኮች ውስጥ ስለተቀበረ ኢትዮጵያውያን የውጤቱ ተጠቃሚዎች ሳይሆኑ ስለቀሩ፣ በክፉኛ የሚያሳዝን የኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የታሪክ ሂደት:: ማለትም ውጤቱ ክሽፈት ሆነ መለት ነው::
  ይሄንን ክሽፈትን የታዘቡ የምኒልክ ወምኒልካውያን አራተኛና አምስተኛ ወለዶ በሎምበጭ ላይ ሎምበጭ እየጨመሩና ኢትዮጵያውነታቸውን ከድተው በከንያ ወይንም በካርቱም በኩል አልፈው እንደምንም አሜሪካ ከደረሱ በኋላ፣ ጀግና ኢትዮጵያውያን ነን ይሉና በክሽፈት ላይ ክሽፈትን በመጨመር ዋናው ትግላቸው አሁን ከዲሲና የመሳሰሉ ከተሞች ውስጥ ሆነውና የሞቀ ቤታቸውን ይዘው ከፍተኛ ከኢትዮጵያ ጋራ የተያያዘ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ Anti-Vernunft – (Anti reason) ጦርነቶችን በማፋፋም ላይ ይገኛሉ::
  ክሽፈት ሲበዛ ብቻ ነው ወደ ጥንት ምኒልክነት ግዛት የምንመለሰው ባዩ ሞረተኛው ህልማቸው ክሽፈትን ከግቡ ለማድረስ በተለይ ሰላምንና በጎን የሚሰብኩ ኢትዮጵያውያንን ድራሽ ማጥፋት ነው መንገዱ የሚለው ምቀኛና ቅናተኛ እኩይ አላማቸው፣ ሳዲስቶችን አስተባብሮ ጤነኛን ኢትዮጵያዊ አፍን ለማስደፈን ቀጭን ኩታ ሁሉ እየታጠቁና እያወነዘፉ በየመዲያው banal ልፈፋዎችን እያስፋፉና እያንሸባረቁ፣ ቁምነገር አዘል አባባሎችን ዚደኢዙና ሲሰርዙ መሽቶ ይነጋባቸዋል::
  በአሁኑ ጊዜ እኩይ ተስፋቸው፣ በአዲስ አበባና በመቐለ መሃከል የጦፈ ጦርነት እንዲነሳና በጨረሻውም እልቀት በልቀት ተኩኖ ለነሱ እኩይ አላማ መንገዱ ወከክ ብሎ የሚከፈት ይመስላቸዋል፣ የማያስታውሱት ያለ ጉዳይ ግን፣ ከትላንት ወድያ እንኳን አሜሪካና ባህር ዳር በ Facebook አማካኝነት ተማምለው ኢትዮጵያን እንደገና በመዳፍ ስር የማስገባቱን አላማ ውጥን ሳይሳካ ቀርቶ የመጀመርያው ተበዪው የነሱው የጅብ ችኩሉ አሳመነው መሆኑን እንኳን የክሽፈት አራማጆች ከመቸው ረሱት? ለመሆኑ እነሱ እንደሚያስቡት አዲስና መቐለ መሃከል ፊልሚያ ቢጀመር፣ በመቐለና አዲስ መሃከል በሚገኘው ጦር ሜዳ ላይ እንደሚካሄድ አስበውበታልን? ወይንስ እንደተለመደው እኩይነታቸው እዚያው ስላለው ህዝብ ሃሳብ የላቸውምን? ግን በኋላ ህዝብ ካለቀ በኋላ ደግሞ የሙታን ስእልን እየዘረጉ ጆኖሳይድ ብሎ ለመጮህ ነውን? ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅን እንዲሉት አስቡበት እንጂ፣ ለምእራብ ወለጋ ፍጂቶች ምክኒያቶች የአሜሪካ ሆኖ የማስፈራራት ዛቻዎችንም ጭምር ናቸውና ይልቁንስ ወይኔ ቀን ሲመጣልኝ አጠፍሃለሁ ከማለት ይልቅ፣ አብሮ ጎን ለጎን በሰላም ለመኖርን ብትሰብኩና Vernunft- reason’ንም አስፋፊ ወገኖቻችሁንም ባትጠሉ እንዴት ባመረባችሁ……………….!!!

 2. ሲመስለኝ እኮ Bob Marley እንጂ Frank Zappa’ም የኢትዮጵያን ባንዴራ ይዞ ይወራጭ ነበር እንዴ? ሁለተኛው ሰውዬ ልክ Zappa’ን ይመስላል እና ለዮሃንስ አራተኛ ሌላ ንፁህ ስነ መልክ ይፈለግ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.