ልዩ ጥበቃ ለትግራይ ሕዝብ፣ ለትግራይ የለውጥ ኃይሎች – አንድነት ይበልጣል – ሐዋሳ

(አጣዳፊ ጥሪ፣ ከዜጋ ለዜጋና ለመንግሥት)
ልዩ ጥበቃ ለትግራይ ሕዝብ፣ ለትግራይ የለውጥ ኃይሎችና ለትግራይ ተወላጆች፤
ልዩ ድጋፍ ከትግራይ ሕዝብ፣ ልሂቃንና ተወላጆች፣
 

Tigray ልዩ ጥበቃ ለትግራይ ሕዝብ፣ ለትግራይ የለውጥ ኃይሎች   አንድነት ይበልጣል   ሐዋሳአንድነት ይበልጣል – ሐዋሳ – ጥቅምት 25 / 2013

ጊዜው ግድ ብሎ – ጊዜው ደርሶ ሞልቃቃውንና አጉራዘለሉን ሕወሐትን ልክ ማስገባት ተጀምሮአል፤ እግዚአብሔር ይመስገን! አሁን በደረስንበት በዚህ ደረጃ ብዙዎቻችን ብዙ ትዝብትና ምክረ ሃሳብ ሊኖረን ይቻላል፤ እኔ እንደ አንድ ተራ ዜጋ በስጋትና በጥድፊያ ስሜት ውስጥ ሆኜ የመረጥኩት ልዩ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ የልዩ ጥበቃና የልዩ ድጋፍ ጉዳይ ነው፡፡ ልዩ ጥበቃ ለትግራይ ህዝብ፤ ልዩ ድጋፍ ከትግራይ ሕዝብ!!

መላው የትግራይ ሕዝብ ለውጡንና የኢትዮጵያን አንድነት መደገፍ ይኖርበታል፡

የትግራይ ሕዝብ ከማንም በላይ የትሕነግ/ሕወሐትን የጭቆናና የዘረፋ ገፈት የቀመሰና እየቀመሰ ያለም ሕዝብ ነው፡፡ ትሕነግ/ሕወሐት ከማዕከላዊ ሥልጣን ሲባረርና በተለይ ዛሬ ዙሪያ ገባው ሲጨልምበትና ሲጨንቀው፣ የበላውን የኢትዮጵያ/ውያን ሐብትና የደም ዕዳ በትግራይ ሕዝብ ኪሣራ ሊያወራርድ በሕዝብ ጉያ ውስጥ ተደብቋል፡፡ የትግራይን ሕዝብ ሰብዓዊ ጋሻ አድርጓል፡፡ በአንጻሩ በትግራይ ያሉም ይሁኑ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የለውጥ ኃይሎች የትግራይንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ከአፈናና ከግዞት ቀንበር የሚያላቅቅ ለውጥና ነጻነት ለማምጣት ውድ መሥዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና መላው የጸጥታ ኃይላችንም መስዋዕትነት የሚከፍሉትም የትግራይንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰላምና ደህንነት፣ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ከተጋረጠበት የሕልውና አደጋ ለመታደግ ነው፡፡ ስለዚህ የትግራይ ሕዝብ እነዚህን ለውጥ አራማጅ፣ ድንበርና ሉዓላዊነት ጠባቂ ልጆቹን  ካልደገፈ ማንን ሊደግፍ ነው?! የትግራይ ሕዝብ የተከፈለውን መስዋዕትነት ከፍሎም ቢሆን ለውጡን፣ የለውጥ ልጆቹንና የህልውናውና የኢትዮጵያዊነቱ አለኝታ የሆነውን መላ የጸጥታ / የመከላከያ ኃይላችንን ሊደግፍ ይገባል፡፡

የፌዴራል መንግሥት በመላ ትግራይ ለሚገኙ የለውጥ ኃይሎች ጥበቃ ማድረግ አለበት፤

ወያኔን ልክ ለማስገባት ከሚወሰደው የማያዳግም እርምጃ ጎን ለጎን የሚደረግ ልዩ ጥንቃቄ አለ፤ ይኸውም መላውን የትግራይ ሰላማዊ ሕዝብ፣ በመላ የትግራይ ክልል የሚገኙና የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የለውጥ ኃይሎችንና ደጋፊያቸውን፣ በክልሉ ውስጥ የማንነት ጥያቄ አራማጆችንና ደጋፊያቸውን፣ የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ አባላትና ደጋፊዎችን ከወያኔ በኩል ሊቃጣ ከሚችል የተስፋ መቁረጥና የብስጭት ጥቃት መጠበቅ ነው፡፡ ለዚህ ልዩ ስምሪት ያስፈልጋል፤

የፌዴራል፣ የክልል መስተዳድሮችና መላ መዋቅራቸው ከሕዝቡ ጋር ሆነው  ለትግራይ ተወላጆች ልዩ ጥበቃ ሊያደርጉ ይገባል፤

አካባቢውን ሐገሬ፣ ሰዉን ወገኔ ብለው በመላ ኢትዮጵያ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጀች ልዩ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል፤ እነዚህ ወገኖቻችን ከተቀበላቸው አካባቢ ሕዝብ ጋር ተጋብተው ተዋልደው የተቀላቀሉ ናቸው፤ ትሕነግ ራሱ ለድብቅ ዓላማው ሲል በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ሊሰነዝር ወይም እንዲሰነዘር ሊያደርግ ይችላል፤ ወይም  በትህነግ ክፋትና ጥፋት የተማረሩ የየአካባቢው ዜጎች ሕወሐትንና የትግራይን ሕዝብ ወይም በአካባቢያቸው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን በአንድ ዓይን የማየት ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፤ ትግሬ – ጠል መጥፎ ስሜቶችም መታየት ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ ይህን ጥርጣሬና ስሜት ተከትሎ በትግራይ ተወላጅ ወገኖቻችን ላይ የማሸማቀቅና የአድልዎ፣ ከበዛም የጥቃት ዘመቻዎች ሊቃጡ ይችላሉ፡፡ ይህ እንዲሆን መሰሪው ሕወሐት በጥብቅ ይፈልጋል፤ ነገር ግን በአንድ በኩል ድርጊቱ ኢሕገመንግሥታዊ በሌላው በኩል ደግሞ ኢሰብዓዊነትና ጸረ አንድነትም ስለሚሆን የፌዴራልና የክልል መስተዳድሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በመላ ኢትዮጵያ ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ልዩ ጥበቃ ሊያደርጉላቸው ይገባል፤

በመላ ሐገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ወገኖቻችን አዎንታዊ ሚና ሊጫወቱ ይገባል፤

በመላ ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ወገኖቻችንም ያለይሉኝታ ከውጡን በመደገፍ ከአንድነትና ከለውጥ ኃይሎች ጎን በተግባር መቆም ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ባይቻል እንኳ ለጥፋት ዓላማቸው ሊጠቀሙባቸው በሚፈልጉና በሚሞክሩ የትሕነግ/ሕወሐት ወኪሎች ባለመታለል፣ ፊት ሊነሷቸው – አሳልፈው ሊሰጧቸውም ይገባል፡፡

 

ፈጣሪ ይርዳን!!

2 Comments

  1. No battle was fought between TPLF and PP . It is just a made up story fake news to distract Amaras from demanding explanation about why the ongoing genocide us being perpetrated against Amaras with Abiy failing to secure Amaras intentionally . All that happened recently in Tigray was foolish soldiers of the Ethiopian defence forces tresspassed and were captured right away while they were trying to steal drones and helicopters from the an airbase in Tigray , so far it is not clear if Abiy ordered them to steal the drones and helicopters or if the individuals did try to steal on their own accord ..

    Both Abiy Ahmed and Isayas know that TPLF got the strength and the ability to fight not only the Ethiopian defence forces but also the Eritrean defence forces defeating both Abiy and Isayas at the same time.

    TPLF defeated borh Derg and Shabiya without having a strong military as TPLF does have now. The TPLF leaders fighting skills is no match for Abiy and Isayas so Amaras should not get fooled by the psychopath Abiy, he will send the mostly Amara soldiers of his to the line of fire where they are not expected to survive.Tegaru will not fail from defending Tigray no matter what.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.