ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ምን እየሆኑ ነው? – ከተማ ዋቅጅራ

abiyሰው ሊሞት ሲል አንድም ወሬ ያበዛል አንድም ያምርበታል ይባላል። ህውአት መለፍለፏ መሞቻዋ ስለደረሰ መቃብሯ ላይ ሆና ነው። ብልጽግናስ ጥቁር በለበሰች አገር መናፈሻና የእርሻ ማሳውስጥ ፎቶ መነሳት  ምንድነው መልእክቱ? የብልጽግና ውበት የሞሞቻው ግዜ መድረሱን እየነገረን እንዳይሆን እሰጋለው።
ህውአትን ያባረረው ህዝብ ብልጽግናንም ሊያባረው የመጨረሻው ምዕራፍ ለይ መድረሱን አመላካች ነገሮች እየታዩ ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጡዘቱ በሚያስደነግጥ ሁኔታ በሁሉም አቅጣጫ ከባድ እንቅስቃሴዎች እያየን ነው። አማራ ክልል ሞታችን ይብቃ በማለት የመረረና የመጨረሻ ፊሽካ ተነፍቶ በመንግስት ተስፋ ቆርጦ ከአገር ቤት እስከ ውጪ በመናበብ ህዝባቸውን እያነቁና እያደራጁ ይገኛል። የአማራ እንቅስቃሴ ከመጠቃት ወደ ማጥቃት እንደሚለወጥ ለመናገር ነብይ መሆን አያስፈልግም ምክንያቱም ይሄ የተፈጥሮ ህግ ነውና ማንም በሃገሩ እየሞተና እየተሰደ መኖርን አይመርጥምና ነው።
በኦነግ በኩል ደግሞ ከቀላል መሳሪያ እስከ ላውንቸር እና መትረየስ የታጠቀ ሰራዊቱን በየግዜ በተለያየ ቦታ ፎቶ በመነሳት በሶሻል ሚዲያ ላይ እያሳየ ይገኛል። መንግስት በየግዜው ደመሰስኩት የሚለው ኦነግ በየግዜው እየተጠናከረና የጥቃቱን አድማስ እያሰፋ እንጂ መንግስት እንደሚለው እየተደመሰሰ አይደለም። ህውአትን እና ኦነግን መንግስት የማያጠፋቸው አያጅቦ መጣብህ እየተባለ ልጆችን እንደሚያስፈራሩት ህውአትና ኦነግ መጡብህ እነሱ ከመጡ ይጨሩሱሃል እያሉ ለማስፈራራትና ሚዛን ማስጠበቂያ ተቋም አድርጓቸው ይሆን ብዬ እጠይቃለው? የዶክተር አብይ መንግስት ይሄ አካሄድ ምነው በእንቁላሉ በቀጣሁት የሚልበት ግዜ እሩቅ አይሆንም ሁሉ ነገር ከመንግስ ቁጥጥር ውጪ እንደሚወጣ የምናየው ሃቅ ነው።
በደቡብ ክልል ሁሉም በሚያስብል መልኩ ክልል የመሆን ጥያቄዎችን እያነሱ እየሆኑ ይገኛሉ። ይሄ ሃሳብ በራሱ ችግር የለውም ችግሩ ያለው ከህገ መንግስቱ ላይ ስለሆነ ሲዳማ ክልል በሆነ በወራት ግዜ ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመሬት ይገባኛል ግጭት ፈጥሮ የሞቱ እና በብዛት የተፈናከሉ ማህበረሰቦችን ተመልክተናል። ይሄ ጅምር እንጂ ፍጻሜ አይደለም 82 ብሄር በይገባኛል ጥያቀ ወደማይቀረው ግልጽ ጦርነት ይገባል።
በትግራይ ከመግለጫ ጋጋታ በተጨማሪ የመንግስትንም ሆነ የምርጫ ቦርድ ውሳኔን አላከብርም ከማለት በተጨማሪ ኢትዮጵያ መሪ እንደሌላትና መከላከያም ሰራዊት ለመንግስት መታዘዝ እንደሌለበት በግልጽ በመናገር የሃገርን ህልውና የህዝባችንን ሰላም የማወክ ስራውን ካለምንም ከልካይ ሲፈነጭ እየተመለከትን ነው። ለዚህም በተግባር የታየ ድርጊት በማድረግ አሳይተዋል በሰሜን እዝ ዋና እና ምክትል አዛዦችን አልቀበልም ከማለት በጨማሪ ያገር ክብር የሆነውን ጀነራል ከመቀሌ መልሰውት ተመለከትን። ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰሜን ያለውን መከላከያ የማዘዝም ሆነ መሳሪያ የማንቀሳቀስ ስልጣን የለውም በማለት ቀይ መስመር ያለፈ ነገር ሲያደርጉ ይሄ ምን ማለት እንደሆነ  ጠቅላይ ሚንስትሩ ካልገባቸው እንዳማረባቸው ሞታቸው  መድረሱን አመላካች ነው።
ጠቅላ ሚንስትር አብይ አህመድ በጣም አደገኛና ሊታረም የማይችል ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍላቸው የሚችል ስህተቶችን እየሰሩ ነው።
ስህተት አንድ. በዚህ ሁለት አመት ከመንፈቅ ከተናገሩትና ከሰሩት ነገሮች በጣም በጢቂቱ እንመልከት
በኔ ዘመን ማንም አሳዳጅ ማንም ተሳዳጅ አይኖርም ብለው ነበረ። እውን አሁን እየሆነ ያለው እንደነገሩን ነውን ብዬ እጠይቃለው?
እኔ ባልነበርኩት ግዜ ስለሆነው ወይንም ስለጠፋው አትውቀሱኝ ባልነበርኩበት ዘመን ለጠፋው ጥፋት ተጠያቂ አታድርጉኝ ብለው ነበረ ይሄንን ተቀበለን። አሁን በርሶ ዘመን የደረሱትን ጥፋትና እልቂት ይቅርታ የመጠየቅ ፍላጎት አሎትን ብዬ እጠይቃለው? ለጠፋው ነብስ እውነተኛ ፍርድን ለጠፋው ንብረት ካሳን የመክፈል ሞራሉና ፍላጎቱ አሎትን ብዬ እጠይቃለው?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትሪያርኩ እና ሊቃነ ጳጳሳቱ በቢሮዎ ጠርተው ሲያናግሯቸው ሊቃነ ጳጳሳቱ በእርሶ ዘመን ቤተክርስትያን በብዛት ተቃጥለዋል ካህናቶቿ እና ምእመናኖቿ በገፍ ተገድለዋል ለጠፋው የሰው ህይወትና ለጠፋው ንብረት በይፋ ይቅርታ ጠይቀው ካሳ መንግስ ይክፈል ብለው ለቀረበው ጥያቄ እኔ ባላጠፋሁት እና ባላደረጉት ይቅርታ ልጠይቅ አልችልም መንግስትም ካሳ አይከፍሊም በማለት ከዚህ በፊት የተናገሩትን ቃል የሚያፈርስ ብቻ ሳይሆን ታአማኒነቶን ጥያቄ ውስጥ የከተተ ንግግር አድርገው ሊቃነ ጳጳሳቱን ከሸኙ በኋላ በማግስቱ ከመንግስት የማይጠበቅ ለማናደድ በሚመስል መልኩ ፓስተር ዮናታን በሚሰብክበት አዳራሽ ሄደው የኢትዮጵያ ካርታ ያለበትን የአንገት ሃብሊና 25 ሺ ዩሮ መሸለሞን ታሪክ መዝግቦታል። መንግስት ለተጎዱት እና ለሞቱት ግድ ሳይለው አዳራሽ ውስጥ ሰብስቦ ስለሚያስተሚር ፓስተር ይሄንን ማድረጎ ከምን የመነጨ ነው ብዬ ለመጠየቅ እገደዳለው?
ሌላው አገርን በቡድን እና በክልል ከአፍ እስከአፍንጫቸው ታጥቀው አገርን ወጥረዋት ባለበት በዚህ ወቅት ለአገርና ለህዝብ አደጋ የሆኑትን ቅድሚያ አደብ ሳያሱዙና ሳያስተካክል በፓርላማ ደረጃ የግለሰቦችን መሳሪያ ማስፈታት በሚል ህግ ማውጣት እና እራሱን የሚከላከሊበትን መሳሪያ ለመውረስ የሚደረገው እንቅስቃሴ አደገኛ  ነው። መንግስት በቡድን ታጥቀው አገርንና ህዝብን ላደጋ የጋረጡትና ህዝብን ያለምንም ርህራሄ የሚረሽኑትን ሳያጠፋ ወደ ግል መሳሪያ ማስፈታት የሄደብት ከምን የመጨ ነው ብዬ እጠይቃለው? ቅድሚያ አገሪን የሚያተራሚሱትን ሳይቆጣጠር ወደግለሰቦች ወርዶ መሳሪያ አስመዝግቡ በሚሏት የውሸት ፈሊጥ መሳሪያ ወደማስፈታቱን ቢሞክረው ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍለው ሊረዳው ይገባል።
አሁን በአገር ደረጃ እየተከሰተ ያለው ሁኔታ በጥቃት ፈጻሚዎቹ ብቃት ሳይሆን በመንግስት እንዝላልነትና ሃላፊነትን አለመወጣት ችግር ነው። ቤተሰብ ያለው ሰው በአገርና በህዝብ አይቀልድም ምክንያቱም እዚህ ቤት ብቻ ሳይሆን እዛም ቤት እሳት እንዳለ ማወቁ ተገቢ ነው።
ነገሮችን በግዜውና በሰአቱ መቆጣጠር እየተቻለ ወንበዴዎችን ለመያዝ የሌላውን ሰው ህይወት አናጠፋም የሚል ልፍስፍስ አነጋገርና አቋም ወጥቶ በግዜው ካላስተካከለ ዶክተር አብይ አህመድን ሃሳባቸውን ሳንረዳና እቅዳቸውንም ሳንገነዘብ እንዳማረባቸው ፍጻሜአቸው በቅርብ የሚመጣ ይመስለኛል።
ከተማ ዋቅጅራ
04.11.2020
ተጨማሪ ያንብቡ:  “ይታደሏል እንጅ….!” - አሰፋ ጫቦ

2 Comments

  1. ሰሚ ባይኖረውም ለታሪክ ፍጆታ ያህል በጣም ግሩም ዕይታ ነው። ሰውዬው ዶን ኪሾት ቢጤ በመሆኑ ከንፋሱም ከተራራውም እንደተጋጨ ዕድሜውን ማሣጠሩ ያሣዝናል።

  2. ለክ ብለህ ነበር፤፤ ያው የምትፈልገው ተጀምሯል – although your advise was taken over by events! ነገር ግን ተመልሰህ ህዝባችን ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋረ እንዲቆም ጥሪ እንደምታደርግ እንጠብቃለን፤፤

    Ethiopia shall prevail!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.