በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ባለው ማንነትን መሠረት ባደረገው ጥቃት እጅግ ማዘኔን እገልፃለሁ

የኢትዮጵያ ጠላቶች፤ “ወይ እኛ እንገዛለን፤ ወይ ሀገር አትኖርም” ብለው ተነሥተዋል። ለዚህም የጥፋት ዐቅማቸውን ሁሉ እየተጠቀሙ ነው። አንደኛው ዒላማቸውም የሕዝባችንን ቅስም መስበር ነው።
ታዬ ደንድአ
ታዬ ደንድአ

ለዚህ እየተጠቀሙበት ያለው ስልት ግራ ቀኝ የማያውቁ ሰዎችን እየሰበሰቡ በማሠልጠንና በማስታጠቅ በየአካባቢው ማንነትን መሠረት ያደረገ አረመኔያዊ ጥቃት ማድረስ ነው። ይህ ተግባር ሕዝቡ እንዲደናገጥ፣ እንዲፈራና በስሜት ያልተገባ ርምጃ እንዲወስድ የታለመ ነው።

መንግሥት በተለያዩ ቦታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ያላቸውን ጥፋቶች በቅድሚያ መረጃ ሰብስቦ ርምጃ በመውሰድ ሲያከሽፍ ቆይቷል። ነገር ግን ያለፈው ሥርዓት ያወረሰንን ቀዳዳዎች ሁሉ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ደፍኖ መጨረስ አልተቻለም።
የጥፋት ኃይሎች ከውጭ ላኪዎቻቸውና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በሚገኙ ባልጠሩ አድር ባዮች ትብብር በሕዝባችን ላይ አሳዛኝ ጥቃት እያደረሱ ነው። ሁኔታው እንደ መሪም እንደ ዜጋም ልብ ይሰብራል።
ይህ ግን ከመንገዳችን ወደኋላ፣ ከግባችን ወደ ሌላ አያደርገንም። ተስፋ ቆርጠን እንድናቆም፣ ተሸንፈን እንድናፈገፍግ አያደርገንም። ከምንጊዜውም በላይ ኃይላችንን አሰባስበን እንድንነሣ ያደርገናል እንጂ።
መንግሥት ሁሉንም ዓይነት አማራጮች ተጠቅሞ የችግሩን ሰንኮፍ ይነቅለዋል። የጸጥታ አካላት ጥቃቱ ወደተፈጸመበት አካባቢ ተሠማርተዋል። ርምጃም እየወሰዱ ነው። በቀጣይም የሕዝባችንን ደኅንነት ለማስጠበቅ መንግሥት የመንግሥትነቱን ሥራ በቁርጥና በጽናት ይሠራል።
ሕዝቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ ምሁራንና ሌሎችም፧ መንግሥት ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ የሚወስደውን ርምጃ በመደገፍ የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ።

3 Comments

 1. አቶ ታዪ እስቲ መንግስቶትና ፓሪቲዎት የት ነው ጥፋት ከመድረሱ በፊት መረጃ ደርሶት ያከሸፈው? እርግጥ ነው መረጃ ይደርሰዋል መረጃውን ሲጠቀምበት አልታየም። ለምሳሌ የትላንትናግ ጆኖሳይድ የተፈጸመው ህዝባች የጦር ሰራዊቱን እታውጡብን እያሉ ሲለምኑ መንግስቶትና ፓሪቲዎት ሰራዊቱን ባስወጣ በሰአታት ግዜ ውስጥ ነው ዛሬ ጠዋት ጠ/ሚ አብይ እንደተናገሩት” በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ባለው ማንነትን መሠረት ባደረገው ጥቃት እጅግ ማዘኔን እገልፃለሁ።” ማለታቸው። ይህም አነጋገራቸው ለዓለም ህዝብ መንግስታቸው ሃላፊነት እንደሚወስድ ነው ያመኑት። ፈረንጆች እንደሚሉት ምክንያቱን ማወቅ 50 % የችግሩ መፍትሄ ታወቀ ማለት ነው ይላሉና ። ይህ ከሆነ ዘንዳ ገሌ ነው እገሌ ነው የሚለው አያዋጣም ስለሆነም አሁን ምን ይደረግ በአጋራችን ጆኖሳይድ ተፈጽሞል መንግስትና ህዝቡ በአንድነት ሆኖ ምን የደረግ ወደሚል ስምምነት መምጣት የግድ ነው። ጠ/ሚ አብይ ወደ መረጣቸው ፓርላማ ሄደው በቆራጥነት አገራችን ለዚህ ያደረሰው ህገ መንግስቱ ስለሆነ ህገ መንግስቱ መሻሻል እንዲኖርብርት ማጸደቅ አለባቸው። ሌላው ደሞ ከአሁን ጀምሮ በዘር፤ በጎሳ፤ በሐይማኖትና በቋንቋ ምንም አይነት የፖለቲካ ድርጅት አያስፈልግም የርሳቸውንም ፓሪቲ የኦሮሞ ብልጽግና፤ የአማራ ብልጽግና ወዘተ የሚለው በአንድ አገራዊ ብልጽግነ ፓሪቲ እንዲዋሀድ ማጸደቅ ይጠበቅባቸዋል።

 2. ወንድማችን፣
  1. ከላይ እንደተገለፀው በሀገራችን ለተፈጠረው የዘር እልቂት መሰረቱ ፍሺስት ጣልያን ኢትያጵያን ከፋፍሎ ለመግዛት ያዘጋጀው ሰነድ ውላጅ የሆነው ህገ መንግስት መሻር ይኖርበታል።በህዝብ የተመረጠ መንግስት ያሻሽለው የሚለው አዘናጊ ሀሳብ ውድቅመሆን አለበት። ቢያንስ ሀሉን ዜጋ እኩል የሚያደርግ ፣ ለminorities እከል መብት የሚሰጥ። ጊዚያዊ ህገመንግስት ወጥቶ ሀገራዊ ምርጫ መካሄድ ይኖርበታል።በዚህ ከፋፋይ እና አበላላጭ ህገ መንግስት ላይ ተመስርቶ በምርጫ የሚመሰረት መንግስት እንዴት አድርጎ የራሰን privileges. ይክዳል ? እውን ከቤኒሻንጉል በክልልሉ ባለቤትነት የተመረጠ የባለቤትነት ጥቅሜ ባለቤትላልሆነው አማራና ትግሬ ላካፍል ይላል ብለን እንጠብቃለን ?? ክልል ለጎሳ በባቤትነት በተሰጠበት ሀገር፣ ከክልሉ ጎሳ ውጭ የሆነ ዜጋ የንብረት ባለቤትነት መብቱ እንዴት ይጠበቅለታል?
  2. የጎሳ ፓለቲካ ለጊዜው ስልጣን ለመያዝና በስግብግብነት ለመዝረፍ ያመች እንደሆነ እንጂ የማታ ማታ አቀንቃኞቹን ነው የሚበላቸው። ይልቅስ ለታሪክም ሆነ ለህሊና የዲሞክራት ስብእና ይዞ ከራስ በፊት የሌላው መብት ለመከበሩ መታገል፣ለደካማው ፣ለአናሳው ድምፅ መሆን የሰው ክብር ያላብሳል። ከ ኦባንግ ልዋስና “No one is free until all are free !! ”
  3.Call a spade a spade . እየተጠቃ ያለው ” አማራ ” እና ለሱ sympathy. ያሳዩ የሌላ ጎሳ አባላት ናቸው።ቢያንስ ስሙን ጠርተን ቁስለ ይሰማን !!
  4. በገጀራ ሊያርደው የመጣውን ባልሞት ባይ ተጋዳይ ባለው መሳሪያ እርምጃ እንድዲወስድ እና ሀላፊነቱን አጥቂው እንዱወስድ ማረግ፣ ክተቻለ ማደራጀት።መንግስት አለ ብሎ እንደ በግ መታረድ ይቁም !!

 3. አቶ ታየ የህግ ምሩቅ ሁነህ ከእለት ወደ እለት ከህግ መንፈስ በተጻራሪዉ ስትቆም አዝኛለሁ ዩኒቨርስቲ የገባ ሰዉ አስተሳሰቡ ዩኒቨርሳል እንጅ ነገዳዊ ይሆናል ብለን አንገምትም ነበር። አንተ በታሰርክበት ጊዜ ዘርህን ሳንጠይቅ በበረዶ በጸሀይ ታየ ይፈታ ብለን ስንጮህ ነበር ለበቀለ ገርባም እንዲሁ ።በልጅ ቀመር አስባችሁ ከእኛ በላይ የለም ብላችሁ በ2 አመት ታይቶ ተሰምቶ የማያዉቅ ጥፋት ሰራችሁ።
  ያልገባችሁ ነገር ግን በሀገራችን የመንግስቱ ሐ/ማርያምና የትግሬዎች መንግስት አለፍ ሲልም የሒትለር መንግስት ወድቋል ህዝብን በፍቅር እንደ አጼ ምንሊክ ካላስተዳደራችሁ የተዳፋት መንገድ ነዉ የሚጠብቃችሁ | በዚህን ጊዜ ሰዉ በማይሞኝበት ጊዜ ነዉ ወደ ስልጣን የወጣችሁት። ጌም ቲዎሪ የሚሏትን ነገር ሰታዉቃት አትቀርም። አማራዉን አትረዱት ያጠፋዉ የለም እናንተን ጠብቆ ከማቆየት በቀር የተጠቀመዉ የለም ዛሬም ከዚህ መአት የሚያወጣችሁ እመነኝ አማራዉ ነዉ ግራዝማች ግሪሳንና በቀለ ገርባን ረጋ እንዲሉ አድርጋችሗል ሺመልስ አብዲሳንም ብትችሉ አደብ አስይዙት እንደ ጠገበ ጥጃ መቧረቅ ጥሩ አይደለም ካድሬ ሁኖ ምን ይሰራ እንደነበር መረጃዉ አለን።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.