“የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወለጋ ውስጥ ከ 300 በላይ አማራዎችን ለስብሰባ ጠርተዋቸው በሙሉ በጥይት ገደሏቸው” የሚለውን መርዶ ስሰማ አላለቀስኩም:: እምባዬ ስለደረቀ ግን አይደለም::

ለገዛ አራጁ የአብይ መንግስት የሚያሸረግድ አማራ /ከታዛቢውDemeke“የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወለጋ ውስጥ ከ 300 በላይ አማራዎችን ለስብሰባ ጠርተዋቸው በሙሉ በጥይት ገደሏቸው” የሚለውን መርዶ ስሰማ አላለቀስኩም:: እምባዬ ስለደረቀ ግን አይደለም:: ይልቅስ አማራ የሚባለው ሕዝብ ዋና የራሱ ጠላት እራሱ ስለሆነ ከዚህ የከፈ እልቂ እንደሚደገስለት አስቀድሜ ስለማውቅ ነበር:: ኢትዮጵያ የምትባለውን የደም ምድር ለብቻው ያቀና እስኪመስል አልያም ከዛች የጉድ ምድር የተለየ ጥቅም የሚያገኝ ይመስል ዘር ማንዘሩ በአሰቃቂ ሁኔታ እየታረደ በዓይኑ እያየ እሱ ግን “ኢትዮጵያ ወይም ሞት!” በሚል ከንቱ ግብዝነት ከ 30 ዓመታት በፊት በጎሳ ተኮር ፌደራሊዝም ተሸንሽና የፈረሰች ተስፋይቱን ምድር እያለመ በቀን ቅዥት የሚኖር ማህበረሰብ ነውና በሃሰት ትርክት ጥርሳቸውን ነቅለው ያደጉት እንደ ሕወሃት/ትህነግ ያሉ የእድሜ ልክ ጠላቶቹ መሳቂያና መዛበቻ ሲሆን ማየት ከሞቱም በላይ በእጅጉ የሚያም መራር ሃቅ ነው:: ይህ በሶስት ስለት የሚታረድ ህዝብ ተደራጅቶ ዘር ማንዘሩን ከእልቂትና ከጥፋት እንዳይታደግ ቀዳሚ ጠላቶቹ የገዛ ወገኖቹ አማራ ነን ባይ መሆናቸው ደግሞ የበለጠ ስቃይና መከራውን እንዲከፋ አድርጎታል:: ተደራጅቶ እራሱን ከ እልቂት ለመከላከል የሚንቀሳቀሰውን ሃይል “ፀረ-ኢትዮጵያ እና ጠባብ ብሄረተኛ” የሚል ስም አጥፊና አሸማቃቂ ታፔላ በመለጠፍ የአራጆቹን የትህነግና አብይ አስተዳደር ቡራኬ ለማግኘት የሚታትሩ ከአማራ ዘር የተወለዱ ባንዳ የእንግዴ ልጅ የራሱ ጉዶች ምግባራቸው ከገዳዮቹ ቢከፉ እንጂ የሚያንስ አይደለም::

465556ዛሬ የአማራውን ሕዝብ ለአመፅ አነሳስቶ አማራው በሚከፍለው የደም ዋጋ በሕዝባዊ አመፅ የተነጠቀውን ስልጣን በእጁ ለማስገባት “ስልጣን ከማጣ ኢትዮጵያ ትፍረስ ብሎ” ምሎ የተነሳው ትህነግ በከፈተው የውክልና ጦርነት /proxy war/ አማራው በክልሉም በመላ ሀገሪቱም ከአይሲ.ስ አልሽባብ እና አልቃይዳ በከፋ መልኩ አደራጅቶ አሰልጥኖ እና መሳሪያ አስታጥቆ ያዘመታቸው ነፍሰ በላዎች አማራውን ገለው ሆድ ዕቃውን ሲበሉ አሳይቶን ይህ አረመኔ ከትግራይ የበቀለ ቡድን በህግና በታሪክ የምንፋረደው ብቻ ሳይሆን በሕይወት መስዋዕትነት ጭምር የምንበቀለው እጅግ አረመኔያዊና ሰይጣናዊ የአማራ ሕዝብ ቁጥር አንድ ጠላት መሆኑን አስመስክሯል:: አማራው በለውጡ ሂደት “የኦሮሞ ደም ደሜ ነው” በሚል መፈክር ደሙን አፍሶና ላለፈው በደሉ ይቅር ብሎ ለስልጣን ያበቃው አብይ መራሹ ቡድንም በኢትዮጵያ ስም እየማለ መስዋዕትነት ከፍሎ ከስልጣን ማማ ላይ የሰቀለውን አማራውን ሲክደው አፍታም አልፈጀበትም:: ለዚህም ማረጋገጫው በለውጡ ማግስት የስልጣን ኮርቻው ላይ ሲደላደል የኢሬቻን በዓል አስታኮ “ነፍጠኛን አከርካሪውን ሰብረን ፊፊኔን ተቆጣጥረናል” ሲል ልክ አማራን ተፋልሞ ከጦር አውድ በድል እንደተመለሰ አርበኛ በአደባባይ ፉከራ በእነ ሽመልስ አብዲሳ ጅምላ የዘር እልቂጥ ፍጅት በአደባባይ ታውጆበታል::

ከ 25 ዓመታት በላይ በኤርትራ በረሃ የኢሳያስን የእርሻ ማሳ ሲያለማ የኖረውን ከአንድ ሺህ የማይልቅ ሸማቂ ሃይል የነበረው ኦነግ ተብዬ አሸባሪ ቡድን እነ ለማ መገርሳ አስመራ ድረስ ተሻግረው ትጥቁን ሳይፈታ ኢትዮጵያ ውስጥ በስውር እንዲደራጅ አግባብተውና ሁኔታዎችን አመቻችተው ከ 20 በላይ ባንኮችን በጠራራ ፀሃይ ዘርፎ በፋይናንስ አቅሙ እንዲፈረጥም የራሱን ገዢ መሬትም ተቆጣጥሮ በርካታ አማራ ጠል ወጣቶችን መልምሎና አሰልጥኖ እንዲያደራጅ መንግስታዊ የሽብር ተግባር እና ክህደት ሲፈፅሙ ቆይተዋል:: ከዚህ ሌላ ለአማራ ተቆርቋሪ የነበሩት እንደ ዶክተር አምባቸው እና ጄኔራል አሳምነው ጽጌን የመሳሰሉ የቁርጥ ቀን ልጆችን እራሱን አዴፓ ብሎ በሚጠራ አማራ ጠል የትህነግና የኦዴፓ አሽከር ባንዳዎች ስብስብ እነ ደመቀ መኮንን ገዱ አንዳርጋቸው ሲሳይ ንጉሱና ተመስገን ጥሩነህ በመሳሰሉ አማራ ክልል ተወልደው ያደጉ የሌላ ብሄር ተወላጆች የፖለቲካ ሴራ እንዲገደሉ በማድረግ እንደነ ዮሃንስ ቧያለው ያሉት እኩያንም ከግድያው በተአምር ተረፍን እመኑን ሲሉ በየመገናኛ ብዙሃኑ የአዞ እንባቸውን እንዲያነቡና የአማራው ሕዝብ ብሶት በገነፈለ ቁጥርም የአማራው ተቆርቋሪ መስለው እንዲሁም የአዴፓ አመራር በአማራው ጥቃት የተከፋፈለ የሚያስመስል መረጃን በየፌስቡኩና በየማህበራዊ መገናኛ ዘዴው እያሰራጩ የሕዝቡን አመፅና ትኩሳት ለጊዜው በማብረድ ይህን ሕዝብ ሲያጃጅሉት እና ሲያቄሉት በተደጋጋሚ ተስተውለዋል::

ውድ የአማራ ሕዝብ ሆይ! ዛሬ በህዳሴው ግድብ እየደለለ በኢትዮጵያ ስምና አንድነት እየማለ ከትህነግ ጋር እየተናበበ መንግሥታዊ መዋቅር ባለው ስልት ከአዲስ አበባና ከመላ ሃገሪቱ የሚያፈናቅልህ ጭካኔ በተሞለባት ግፍ የሚያስገድልህና ሃገር አልባ ሊያደርግህ የሚሯሯጠው በተለይም በየ ዕለቱ በሚፈጽምብህ የጭካኔ ተግባር በጭንቀት ውስጥ ገብተህ ሳትወድ በግድ “እሱ ይሻለናል” በሚል እንድትደግፈው ለማድረግ ጠላቶች የሚያዘምትብህ አብይ መራሹ በኦሮሞ ስም የራሱን የበላይነት ለማንገስ የሚሯሯጠው መሰሪው የአብይ አህመድ መንግሥት መሆኑን ለአፍታም ልትዘነጋው አይገባም:: እነሱ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እንሆናለን” አልያም “ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው ” በሚሉ ሽንገላዎች እያቄሉህ ከጀርባ የሚያርዱህና የሚያሳርዱህ ለራሳቸው ጥቅም የስልጣንና የኢኮኖሚ የበላይነታቸውን ሙሉ ለሙሉ እስኪያረጋግጡ መሆኑንም አትዘንጋ:: እናም በመንደርና ጎጥ ሳትከፋፈል እራስህን አደርጅተህ ህዝብህን ከጥፋትና ከዘር ፍጅት ዛሬውኑ ለመከላከል በህብረት ተነሳ:: “አማራ ነን” ብለው አማራው በብሄሩ ተደራጅቶ እራሱን ከጥፋት እንዳይከላከል እንቅፋት የሆኑ እንዲሁም አብይ መራሹን ጨካኝ አሸባሪ ቡድንም ሆነ እራሱ ወያኔ በተዘዋዋሪ አማራውን እያስጨፈጨፈ “ሕወሃት ይሻለን ነበር” የሚሉ የእድሜ ልክ ታሪካዊ ጠላትህና ገዳይህ ትህነግ በራስህ ላይ እንዲሰለጥን መሰሪና ስልታዊ ፕሮፓጋንዳ የሚነዙ ምሁራን ተብዬዎች ከትህነግ እና አማራ ጠል ከሆኑ የኦሮሞ ድርጅቶች የከፉ የራስህ ነቀርሳዎች ናቸውና እንዲህ አይነቶቹን የእንግዴ ልጅ ባንዳዎች ከውስጥህ በአስቸኳይ እንዲገለሉ ልታደርግ ይገባል:: ኢትዮጵያ የ 85 ብሄረሰቦች ሃገር እንጂ በዘርህ ማንነትህ ተለይተህ ኢትዮጵያን ባልክ የምትታረደው ያንተ የአማራው የግል ንብረት ስላልሆነች ሌላው ንቆ ትቷት የራሱን የፌደራል ክልል ለመሰረትና ለማጠናከር በሚሯሯጥበት ዘመን አንተ ዘርማንዘርህ እየታረደ ኢትዮጵያን የሙጥኝ ማለት “የእጁን ነው ያገኘው ይበለው” ከማሰኘት ውጭ አንዳችም እርባና አይኖረውም:: ከዚህ ሌላ ውሎ አድሮ የራስህን በክልልህ ጭምር የመኖር ሕልውና ከማሳጣት አልፎ ሃገር አልባ እንዳያደርግህ ለመጨረሻ ጊዜ ቁርጠኛ ውሳኔ ልታሳርፍ ይገባል:: በተረፈ በትህነግ በአብይ መንግሥትም ሆነ በአማራ ጠል ባንዳዎቹ የአዴፓ አመራሮች የሰርክ ሽንገላ ጨርሶ እንዳትዘናጋ ምክሬን እለግስሃለሁ:: አማራ በጅምላ እየታረደ የዘር እልቂት እየተፈጸመበት “ኢትዮጵያ ወይም ሞት” እንድትል የሚሰብኩህ እነሱ ከገዳዮችህ የባሱ ጠላቶችህ መሆናቸውንም ሁሌም ልብ ልትል ይገባል:: በመጨረሻም 25 ዓመት ሙሉ ኤርትራ የቁም እስርላይ የኖረውን ኦነግ ሸኔ ተመሳጥሮ ሃገር ውስጥ አስገብቶ ትጥቅ ሳያስፈታ እንደውም በገንዘብ እና በጦር መሳሪያ እንዲደራጅ አድርጎ በየቀኑ አማራውን እንዲፈጅ በኦሮምያ ክልል የሚማሩ ተማሪዎችን እያገተ እንዲፈጅ መሪዎቹንም በአማራው የቀረጥ ገንዘብ በናጠጡ ሆቴሎች አስቀምጦ ሲቀልብና ግዙፍ ቢሮዎችን ሸልሞ ሲያንቀባርር ለከረመው ዘረኛው አማራ ጠሉ እና አማራ አስጨፍጫፊው የአብይ መንግስት የሚያሸረግድ አማራ ነኝ ባይ ባንዳ ሁሉ እሱ አማራ ነኝ ከሚል በቁሙ ሞቶ ቢቀበር ይሻለዋል የሚል መልዕክቴን ላስተላልፍለት እወዳለሁ:: ጊዜው የምናለቅስበት አልያም በጭቅጭቅና በሰላማዊ ሰልፍ ብቻ ድርጊቱን አውግዘን ቤታችን የምንቀመጥበት ሳይሆን ለመራራው ሰላማዊ የነፃነት ትግል እጅና ጓንት ሆነን በአንድነት የምንነሳበት መሆኑም ሊታወቅ ይገባዋል:: በዘር ፍጅት በግፍ የተሰው አማራ ሰማዕታትን ሁሉ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን!

 

ታዛቢው

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.