ህወሓት ገና አልተሸነፈም…..ህወሓትን ማዳከም ወይም ማስወገድ – ታደሰ ብሩ

tplf 2በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሜ እጽፋለሁ። ህወሓት ገና አልተሸነፈም፤ ተፈጥሮዉን ቀይሮ ሽብርተኛ ከፊል መንግስት (Terrorist Semi State) ሆኗል። እንዲህ ዓይነት ሽብርተኛ ድርጅት የምናውቀው ISIS ነው። ህወሓት ሳይሸነፍ አገር ማረጋጋት ፈጽሞ አይቻልም።
ህወሓት እንዴት ማዳከም እንደሚቻል ስልት ለመንደፍ ISIS እንዴት እንደተዳከመ ማጥናት ይጠቅማል። ፀረ-ህወሓት broad coalition መፍጠር በጣም አስፈላጊ ነው። ሁለገብ የትግል ስልቶችን መጠቀም ተመራጭ ነው። ህወሓትን ከውስጥም ከውጭም ማዳከም ይገባል፤ ማዳከም ካልተሳካ በትግራይ ክልል ከያዘው የመንግስት ስልጣን ማስወገድ ይገባል።
ህወሓት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው አገሮች ሁሉ ስጋት እንደሆነ የአካባቢው አገሮች መንግስታትን ማሳመን ተገቢ ነው። እየተደረገ ያለው ግን ወደዚያ የሚያመራ ስለመሆኑ በበኩሌ እርግጠኛ አይደለሁም። እንዲያውም ከራሱ የጎለበተ ሠራዊት በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ ያለውን የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ሊያማልልና ሊጠቀም ይችላል። ከወታደራዊ አቅሙ በተጨማሪ የፋይናንስ፣ የዲፕሎማሲና የፕሮፖጋንዳ አቅሙም ጎልብቷል። በድርድር የሚያራዝመው እድሜው ለተጨማሪ ጥፋቶች ራሱን ይበልጥ የሚያደራጅበት ይሆናል። ህወሓት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በቀጠናው የደቀነው አደጋ የማያባራ እልቂት ሊፈጥር የሚችል ነው።
በዚህ የመጨረሻ ሰዓትም ቢሆንም የዶ/ር አቢይ መንግስት ህወሓትን ከትግራይ ሕዝብ ነጥሎ የሚያዳክምበት ካልሆነም የሚያስወግድበት ስልቶችን ነድፎ ተግባራዊ ካላደረገ በራሱና በአገራችን ከዚያም አልፎ በአፍሪቃ ቀንድ የማያባራ እልቂት እየጠራ እንደሆነ ይገንዘብ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ቡድናችንና ግብፃዊ ዳኛ …… (አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)

2 Comments

 1. Well, with all due respect, you are not telling us new story about the very nature and behavior of TPLF elites at all. The story is well known to any ordinary person with his or her right or healthy mind let alone to an educated person with his or her mind of serious and genuine concern about what went terribly wrong for so many years and keep going horrifyingly wrong at this very moment. Yes, TPLF elites are and should be at the very forefront of taking responsibility and accountability.

  But, it is painfully clumsy if not stupid way of political thinking to see the political illness we are facing that has been made and is being made deeply and terribly horrifying by those deadly hypocritical, cynical , conspiratorial politicians of EPRDF who have been the very speaking tools of TPLF and of course active parts and parcels of the politically motivated crime . It is painfully disgraceful to see the very politics of Ethiopia which has been and continued to be stained with the blood and tears of countless innocent citizens as simple as just blaming the well know master minds but not mentioning the very deadly role played by those who simply replaced TPLF and engage themselves in unprecedented horror which we did not witness in the very dirty and cruel reign of TPLF-led politics.
  It is so clumsy if not stupid political thinking to believe that the country’s political situation which has been made deep-rooted, complex and complicated by those very cynical and deadly ethnocentric political elites including the ones who keep playing the same political game in a much more worse and dangerous manner can be fixed simply by attacking and destroying TPLF .

  It is both childish and irresponsible to argue and believe that it is possible to bring about a true sense of democratic change in a political situation where those politicians of the same brand (one from the Center is led by OPDO/Prosperity and the other from Mekele/TPLF) keep playing their bloody and deadly ethnocentric political games. It is a very disgracefull and stupid political thinking to argue that it is a good idea to ignore all venues of negotiations and wage war on one another as if it is as simple as that!
  Why you are not courageous enough to tell those so called opposition politicians such as EZEMA to get out of the very disgraceful and painfully damaging political dance dancing with politicians or ruling elites of the palace politics, and rejoin forces for fundamental democratic change, transition and establishment? Why you chose to add more contamination to the already and deadly contaminated politics of the country by those hypocritical and conspiratorial politicians of EPRDF who foolishly try to convince the people that they have cleansed their bloody hands and minds with a very dishonest way of apology and by simply renaming their bloody brand as Prosperity.
  You guys, what is wrong with your sense of decency and morality? What happened to your sense of understanding the very true and fundamental meaning of education? Why and how you missed that the very true and fundamental meaning and value of education is telling the truth and prevent the people from any type of catastrophic situation, not to worsen the already catastrophic situation? WHY you allow those veil-minded politicians of ethnocentrism (EPRDF/ODOP/Prosperity) to weaken and gradually destroy your conscience? So sad!!
  I am optimistic that those truly patriotic Ethiopians of true democratic change, transition, and realization under the very umbrella Democratic Ethiopia and Ethiopiawinet will prevail although it demands any necessary sacrifice!!!!

 2. ሃቁን አፈነዳኀው አባቴ፤ አፌ ቁርጥ ይበል! The MOMENT OF TRUTH is fast approaching – “to be” or “not to be”
  “የአውሮፓ ህብረት የፌደራል እና የትግራይ ክልል መንግስታትን ለማግባባት ጥረት መጀመሩ ተሰማ” በሚል ርዕስ ዛሬ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣው ዜና እውነት ከሆነ በጣም አሳሳቢ ነው፡፡ ዜናውን ለምን በዚህ ጊዜ በሪፖርተር በኩል እንዲወጣ እንደተፈለገ ለጊዜው ግልጽ አይደለም፡፤ “ሪፖርተር”ም ከትግራይ በኩል ጌታቸው ረዳን ጠቅሶ ሲዘግብ፤ ጉዳዩ እውነት መሆኑን ከፌደራል ወይም ፒፒ ወይም ከአውሮፓ ህብረት በኩል ማረጋገጫ አልጠየቀም ወይም ለመጠየቁ ፍንጭ አልስጠም፤፤ በምን ጉዳይ ላይ እንደተነጋገሩም ሪፖርተር ግምቱን ለአንባቢው የተወው ይመስላል፤፤
  ዜናው እውነት ነው ብለን ብናስብ፤ በሰላም ችግሮችን መፍታት በመሰረቱ ሊነቀፍ አይገባም፡፡ ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው የሚፈልገው ነው፡፡ ምናልባትም ዶ/ር አቢይ “ሰላም የማይፈልግ መሪ” መስሎ በአውሮፓ ህብረት ዘንድ ላለመታየትም ይሆናል ብለን ማሰብ እንችላለን፤፤ ለሚፈጠረው “ጉዳትም” በታሪክ ተጠያቂ ላለመሆን እስከተቻለው ድረስ ለመግፋት ነው ብንልም ያስኬዳል፤፡ ግን አቢይ “ምርጫ ቢያካሂዱ ችግር የለውም” ሲለን ከርሞ አሁን ጉዳዩ to the point of no-return ከደረሰ በኋላ ምንድነው የሚደራደረው? ህወሃትስ ምርጫ ያደረገችውን ትቀለብሳለች ወይ? በዚያም ቢሆን እኮ መጥፊያዋ ነው፡፤ መቼም ከዚያ ያነሰ ዉጤት መቀበል ምን ሊያስከትል እንደሚችል አቢይ ይጠፋዋል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፤፤ እንግዲህ “ማግባባት” የሚባለው፤ “በጀት” እንዴት በወረዳና ቀበሌ እንደሚደርስ ይሆናል ብለን አንጃጃልም፤፤ ታዲያ ጉዳዩ ምን ይሆን? የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ? ወይስ……
  እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ደግሞ አቢይ እንደ ፒፒ ፓርቲ መሪ እንጂ እንደ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መደራደር አይችልም፡፡ ሥራው የፌዴሬሽን ምከር ቤት የወሰነውን ማስፈጸም ነው፡፡ ካልተመቸው ወይም ካስቸገረው እንደገና ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ተመልሶ ለምን የታዘዘውን ማስፈጸም እንዳልቻለ ማስረዳትና አዲስ ውሳኔ መቀበል ነው፤፤ ካላስ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.