ተዓምረኛው ጋላ ጊዮርጊስ (አገሬ አዲስ)

ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓም(30-10-2020)

ጋላ ጊዮርጊስ በወሎ ክፍለሃገር በየጁ አውራጃ ስሪንቃ በተባለው ወረዳ የሚገኝ አንድ ታሪካዊ ጠበል የሚፈልቅበት ደብር ነው።ስሪንቃ ከወልዲያ ከተማ በትንሽ ኪሎሜትር እርቀት ላይ ይገኛል።የጁ አውራጃ እንደሚታወቀው ታላላቅ የኢትዮጵያ መሪዎችን በተለይም የዘመነ መሳፍንት ስርዓት የመጀመሪያው መሥራች የሆኑትንና የጎንደርን ቤተመንግሥት ይቆጣጠሩ የነበሩትን  ትልቁንና ትንሹን እራስ አሊዎች፣እቴጌመንንን የመሳሰሉ ከዚያም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ገናና ሥራ የሠሩትን የዳግማዊ ምኒሊክን ባለቤት እቴጌ ጣይቱ ብጡልን ያበቀለ አካባቢ ነው። ይህ አካባቢ መሪዎችን ብቻ ሳይሆን  እንደ ጋላ ጊዮርጊስ አይነቶቹን የመንፈሳዊና የእምነት ማእከላትን አቅፎ የያዘ ቦታ ነው።

የጋላ ጊዮርጊስ በወሎ ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም ክፍላተሃገር የሚታወቅ እንደ ወሊሶ የአይምሮ በሽተኛና የደዌ ህሙማን ከበሽታቸው የሚፈወሱበት  ተአምራዊ ጠበል የሚፈልቅበትና መንፈሳዊ ቦታ ነው።በዚህ  ጠበል ለመፈወስ የሃይማኖት፣የጎሳና የጾታ ገደብ አይጣልም።ችግር የገጠመው ሁሉ በሰው ልጅነቱ የሚስተናገድበት የጤና ጣቢያ ነው።እስላሙ፣ክርስቲያኑ፣አማኙም ሆነ አላማኙ በደብሩ መጥቶ ይጠመቃል፣በመስቀል ይታሻል።ሁሉም ከበሽታው መዳኑን እንጂ በማንና እንዴት መዳኑን አያስብም።የዳነው በዓመቱም ቢሆን እንዳመቸውና እንደቻለ ስለቱን ይዞ ከቦታው ተመልሶ በመምጣት ምስጋና ያቀርባል።

ከሚከናወነው ተአምራዊ ሥራ ጋር አያይዘን  የዚህን የጋላ ጊዮርጊስን  የአመሠራረት ታሪክ ብናነሳ ታሪኩን የተሟላ ያደርገዋል።በአስራ አምስተኛው ክፍለዘመን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር አጋማሽ የግራኝን ወረራ ተከትሎ በተከሰተው  የጋላ ጎሳ ፍልሰት ወትሮ ይጠራበት የነበረው ላኮ መዛ ወይም ቤተአማራ የሚባለው ስሙ ወሎ  በሚባለው የጋላ ጎሳ መሪ ስም ከተቀዬረ በዃላ  በዘለቀው የጋላ ጎሳ መስተጋብር ከከባቢው ማህበረሰብ ጋር በተለይም ከአማራው ጋር በመጋባትና በመዋለድ  የክፍለሃገሩ ባለስልጣንና  ባለቤት የመሆኑን ሂደት ተከትሎ የመጣ ነው።በከባቢው የበቀሉት የዚህ ጥምር ጎሳ ትውልድ የሆኑት እራስ አሊ (ትልቁ) 1777-1782 የነባሩ የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ በመሆናቸው ይህንን ቤተክርስቲያን  እንደመሰረቱት ይነገራል።የራስ ዓሊን የጎሳ ሃረግና በሥራው የተሳተፉትን  መሰረት  በማድረግም በከባቢው ሕዝብ ቤተክርስቲያኑ  የጋላ ጊዮርጊስ በሚለው ስያሜ ለመጠራት በቃ።የራስ ዓሊን ከጋላው ጎሳ ጋር የሚያያይዘውን የጋላውን እንቅስቃሴና መስፋፋት በተመለከተ ብዙ የውጭና ያገር ውስጥ የታሪክ ጸሃፊዎች በስፋት የተነተኑት ሲሆን አንዳንዶቹን በተለይም የአማራ ጎሳ ተወላጆች የሆኑትን ከጎሳቸው ጋር በማያያዝ የሚያቀርቡትን የታሪክ ትንታኔ የዘመኑ የጋላ ጎሳ ተወላጆች ሲያጣጥሉት ይሰማሉ።ይህም ብቻ ሳይሆን ጋላ ተብሎ መጠራትን በጣም ይጠሉታል።ጋላ ማለት ግን እነሱ እንደሚሉት መጥፎ ትርጉም ያለው ሳይሆን የተለዬ  ምግባር ገላጭ ትርጉም ያለው ቃል  ነው።

በ1985ዓም በጋላው ተወላጅ በሆነው በባህሮ ቢያንሳ ተተርጉሞ “የገዳ ሜልባ፣ኦሮሚያ”በሚለው መጽሃፍ ውስጥ በገጽ 14- 15 ላይ ስለ ጎሳው መነሻና ስለስሙ እንዲህ ይላል “……የኦሮሞ ጥንተመሠረቱ አገሩ (አጽመ ርስቱ )በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ በዛሬዋ ባሌ ክፍለሃገር ውስጥ የምትገኝ ለምለሟ ማዳ ዋላቡ ነች።ካለ በዃላ በሌሎቹ ታሪክ ጸሃፊዎች ከአፍሪካ ቀንድ ምሥራቃዊ የጠረፍ አካባቢ በተለይም ምሥራቃዊው የሶማሌ ልሳነምድር  ነው ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ከዛሬዋ ሱዳን ሲናር እንደሆነ መግለጻቸውን ያትታል።ስለ ጋላ የሚለው ስያሜም የተለያዬ ትርጉም የተሰጠው ቢሆንም “ኦሮሞዎች የሚታወቁበት ሌላው ስማቸውጋላ የሚባለው ነው።…….ለስሙ አጠራር በርካታ ግምቶች አሉ።ሌሎች እንደሚሉት “ጋላ”ገላና ከሚል የኦሮሞ ቃል የወጣ ነው ይላሉ።ገላና ማለትም ትልቅ ወንዝ ማለት ነው።”ሲል ያስቀምጠዋል።ይህ ደግሞ ከጎሳው ብዛት የተነሳ ትልቅ ለማለት ታስቦ የወጣ ስያሜ ሊሆን ይችላል ወደሚለው ድምዳሜ ሊያደርሰን ይችላል እንጂ ጎሳውን ለማኮሰስና ለማዋረድ የወጣ ነው ከሚለው ትርክት ላይ አያደርሰንም።

ታሪክ በማንም ቢሆን ሊቀለበስና ሊካድ የማይችል እውነት ስለሆነ በእውነተኛ የታሪክ ጸሃፊዎች ሲቀርብና ሲተነተን ይኖራል።በመሆኑም የጋላን አነሳስና በኢትዮጵያ ያካሄደውን እንቅስቃሴና መስፋፋት በተመለከተ በተለይም በወሎ የተካሄደውን የጋላ  መስፋፋት እንቅስቃሴ ከውጭ አገር ተወላጆቹ ብቻ ሳይሆን ከጋላው ተወላጆች የታሪክ ጸሃፊዎች የተጻፉ እውነተኛ ታሪኮችም መኖራቸውን በማስታወስና ታሪኩንም በማቅረብ ለአሁኑ ትውልድ በተለይም ስሙን ኦሮሞ ብለው የለወጡበት የጋላ ትውልድ ማንነቱንና ታሪኩን እንዲያውቅ ለማድረግ ይረዳዋል። ከነዚህም የታሪክ ምሁሮችና ምስክሮች አንዱ የጋላው ጎሳ ተወላጅና በኢትዮጵያ ዘውዳዊ ስርዓት፣በአጼ ሃይለሥላሴ ዘመነመንግሥት በገንዘብ ሚኒስቴርነት ለብዙ ዓመታት ያገለገሉትና ለኢትዮጵያ ብዙ ውለታ የሠሩት የምጣኔሃብት (ኤኮኖሚክስ)ምሁር  አቶ ይልማ ደሬሳ ናቸው።

በ1959 ዓም እኢአ በጻፉት “ የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራስድስተኛው ክፍለ ዘመን” በሚለው መጽሃፍ ስለጋላ እንቅስቃሴና መስፋፋት በተለይም  ይህ ጋላ ጊዮርጊስ የተባለው ደብርና ጠበል የሚገኝበት አሁን ወሎ ተብሎ ወደሚጠራው ያገራችን ክፍለሃገር እንዴትና መቼ ሄደው በመስፈር ለጋላ ጊዮርጊስ መመሥረት ምክንያት እንደሆኑ በሚከተለው የታሪክ ትንታኔ ይመሰክራሉ።

በመጽሃፋቸው ውስጥ የጋላን ታሪክ በብዛት የተነተኑ ሲሆን ከዬት ተነስቶ የት እንደደረሰም በገጽ 214 ላይ “የጋላ ጎሳ ከኤደን ሰላጤና ከአሁኑ የአፍሪካ ቀንድ በተባለው የሱማሌ አውራጃ መካከል በሚገኘው መሬት ሲኖሩ በ10ኛው ክፍለዘመን  ሶማሊ የተባለው ጎሳ ከታጁራ ወደብ ተነስቶ በጋሎች ላይ ጦርነት ባደረገ ጊዜ የኖሩበትን አገር ለቀው ወደ ምሥራቅ ደቡብ መጓዝ ግድ ሆነባቸው።ዃላም የአፍሪካ ቀንድ ከምትባለው ሦስት ማዕዘን ወረዳ ተነስተው በዋቢ ሸበሌና በጁባ ወንዞች መካከል ቤናድር  በተባለው አውራጃና በቆላው የባሌ ምድር ሰፍረው እንደኖሩ በአፈታሪክ ሲነገር የቆዬ ነው። ጋሎች የዋቢንና የጁባን ወንዝ ተከትለው ወደ ደቡባዊ ኢትዮጵያ የገቡበት ዓመተምህረት ባይታወቅም አለቃ ታዬ የኢትዮጵያ ታሪክ በተባለው መጽሃፋቸው  ስለ ነገደ ጋላ በገለጹበት ምዕራፍ ውስጥ ከአጼ ይስሃቅ ዘመነ መንግሥት ከአንድ መቶ ዓመት በፊት ሜጫ ከሚባለው የጋላ ጎሳ መካከል ተሰደው ለአጼ ዐምደጽዮን ማደራቸውንና ንጉሡም በጣና ባሕርና በዳሞት መካከል ርስት ተክሎላቸው በዚያው ሰፍረው እንደቀሩ ጽፈዋል።”

በጥቂቱም ቢሆን የጋላ ጎሳ ከዬት ተነስቶ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባና ከገባም በዃላ እንዴት እንደተሰራጨ  በአቶ ይልማ መጽሃፍ ውስጥ በሰፊው ተተንትኗል።ከርዕሱ ጋር ወደ ተያያዘው ወደ ወሎ ጋላ ጊዮርጊስ ታሪክ ለመግባት ያስችለን ዘንድ ስለ ጋላ እንቅስቃሴ ታሪክ በመጽሃፋቸው ውስጥ ይህንን እናገኛለን።

ስለወሎ ጎሳ መሰደድ በሚለው እርዕስ ስር በገጽ 244-245 እንዲህ ሲሉ አስፍረዋል።

የጋላ ጎሳ በተለያዩ ቤተሰቦች የሚከፋፈል ሲሆን እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ የሆነ ስብስብ እዬፈጠረ በቤተሰቡ አንጋፋና መሪ ወይም የገዳ አባት በሆነው ስም እዬተጠራ ለየብቻው በየአቅጣጫው የፈለሰ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎች ያሳያሉ።ከነዚህም መካከል በሸዋ መሬት ላይ የነበረውን ብቻ በመጥቀስ አቶ ይልማ ደሬሳ የወሎን ጎሳ እንቅስቃሴ በሚከተለው መልኩ ይገልጹታል።

“በዘመናችን የሸዋ ጋላ ምድር የሚባለውን አገር በዕጣ ለለቱ ለማ ጎሳ ለቀውለት የሄዱትን የሌሎቹን ጎሳዎች ታሪክ ከመፈጸም አስቀድሞ የወሎን ጎሳ ታሪክ በአጭሩ እናስረዳለን።የወሎ ጎሳ ከቱለማዎች የተለያዬው ሜጫዎች አዋሽን ተሻግረው ወደ ምዕራብ ከተጓዙ በዃላ ነው።በ1554 ዓም በገዳ ሮቤሌ የጀመረው የአምስቱ ገዳ ዙሪያ ተፈጸመ።በዚሁ ዓመተምህረት ቡታ አርደው የነገዱን ያስተዳደር ስልጣን የተረከቡት ሉባዎች ገዳቸውን ሐንፋፋ ወይም ዱሉ ብለው ሰየሙት።እነዚህ ሉባዎች የሚልባ ባለገዳ ልጆች ስለሆኑ እንደ ደንቡ ገዳቸው ሚልባ ሊባል ይገባ ነበር።ነገር ግን ጋሎች ከወላቡ ተንቀሳቅሰው ሰፊ ምድር ለመያዝ ከተለያዩ በዃላ አንዳንድ ጎሳዎች የገዳዎችን ስም እንደለወጡ ከዚህ ቀደም ተገልጿል።ይሁንና የወሎን ጎሳ ወይም ነገድ ዘመቻ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሩት የሐንፋፋ ወይም የዱሉ ባለገዳዎች ናቸው።ታላቁ ወረራ ከመጀመሩ አስቀድሞ ወላቡንና ቱሉ አምዱልን የጋሎች መነሻ ቦታ አድርገን ስለቆጠርን የወሎ ጎሳ ከመንቀሳቀሱ አስቀድሞ መካከለኛው ደጋ ቱሎማዎች፣ በምስራቁ ደጋ ቱለማዎች፣ በምዕራብ ደጋ መጫዎች ሰፍረውበት እናገኛለን።አራተኛ ነገድ ለሆነው ለወሎ ጎሳ የቀረው ክፍያ ወይም ድርሻ ከሰሜኑ ኢትዮጵያ ደጋ መሻማት ብቻ ነበር።ስለዚህ ይህ ጎሳ ወደ ሰሜን የሚጓዝበትን መንገድ ማግኘት ነበረበት።ይልቁንም በነዚህ አውራጃዎች ውስጥ የደረጀ የንጉሠነገሥት ጦር ስለሚገኝባቸው እነሱን አቋርጦ ማለፍ የማይቻል ነበር።የሆነው ሆኖ የሐንሩፋ ገዳ መሪዎች ከአዳ ነቤ ተነስተው መጀመሪያ ወደ ምስራቅ ከተጓዙ በዃላ በደጋውና በቆላው መካከል በንጉሠነገሥት መንግሥት በሚተዳደሩ ወረዳዎችና በአዳሎች ድንበር ላይ አልፈው ወደ ሰሜን ለማቃናት መደቡ።የወሎ ክፍል ጎሳዎች በጉዟቸው ጊዜ አዋሽን ተሻግረው ካቲሲኖ ከምትባል ቦታ ላይ ጊዮርጊስ ሃይሌ የተባለው የንጉሰነገሥት ጦር መንገዳቸውን ለመዝጋት ሰፍሮ አገኙት።ከቲሲኖ ላይ ከዚህ ከንጉሠነገሥቱ ሃይለኛ ሠራዊት ጋር ታላቅ ውጊያ አደረጉ።በዚህ ዘመን የወሎም ጎሳዎች እንደወንድሞቻቸው እንደቱለማና እንደሚጫዎች የደረጀ ፈረሰኛ ስለነበራቸው ጊዮርጊስ ሃይሌን አሸንፈው መንገድ ማስለቀቅ ቻሉ።

ካቲሲኖ ላይ ጊዮርጊስ ሃይሌን ድል ካደረጉ በዃላ የደጋውን አፋፍ ተከትለው ጉዟቸውን ወደ ሰሜን ከቀጠሉ በዃላ ከዚያም ወጥተው በአንጎት አውራጃ አፋፍ ደጋውን አገር ያዙት።ከጎሳው መካከል ተከፍሎ በአንጎት በስተደቡብ ያለን አገር ይዞ ወሎ ብሎ ሰዬመው።ሌሎቹም ዛሬ የጁ የሚባለውን ወረዳ ከያዙ በዃላ ወደ ሰሜን ቀጥለው ያዘቦና የራያ ጎሳ ዛሬ የሚኖርበትን አውራጃ ይዘው ሰፈሩበት።እነዚህን አገሮች ይዘው ከሰፈሩበት በዃላ የሐንሩፋ ባለገዳዎች ጋይንትንና ሳይንትን መውረር ጀመሩ።ከነዚህም አንዱ ባርቱማ የተባለው ጎሳ ዋቃ የተባለውን የሐርቦን ወንድም ወግቶ ከገደለው በዃላ ቤጌምድርን ወርሮ ከመካከለኛው ያማራ አገር ጦር ከተዋጋ በዃላ ወደፊት መግፋት ተስኖት ከዚያው መቆም ግዴታ ሆነበት። አቶ ይልማ ደሬሳ ጽሁፋቸውን በመቀጠል እንግዲህ የወሎን ጎሳ በ16ኛው መቶ መጨረሻ አማራና ትግሬ ድንበር ላይ እንተዋቸውና ቀጥለን የቱለማ ጎሳ ከኦዳ ኖቤ በተነቃነቀ ጊዜ ወደ አደረገው ዘመቻ እንመለስ ይሉና ——-እላይ እንደተመለከትነው ሁሉ ከረዩዎች ወደ ምስራቅ መጫዎች ወደ ምዕራብ ወሎዬዎች ወደምስራቅ ሰሜን መጓዛቸውን ስናትት ቱለማዎችን ኦዳ ነቤ ላይ ተውናቸው።በ1582 ዓም ቱለማዎቹ ከኦዳ ነቤ ዙሪያ ተነስተው ሸዋን ለመውረር በተጓዙ ጊዜ በአዝማች ዘረዩሃንስ የተመራ የንጉሠነገሥቱ ጦር መንገድ ላይ ጠብቆ ገጠማቸው።ከጦርነቱም ላይ አዝማች ዘረዩሃንስ ሞተ፤ሠራዊቱም ተሸነፈ።በዚያን ጊዜ የሮበሌ ባለገዳዎች የሸዋና የጎጃም መንገድ እንደተከፈተላቸው ቆጥረው በግስጋሴ ወደፊት ተራምደው ዛሬ የሸዋ ጋላ ከተባለው አገር ላይ ሰፈሩ።”በማለት የጋሎችን ወረራና መስፋፋት ይገልጻሉ።

በታሪክ ጸሃፊው በተክለጻድቅ መኩሪያ ከአጼ ልብነድንግል እስከ አጼ ቴዎድሮስ በሚለው መጽሃፋቸው ከገጽ 266-272 ባለው  ደግሞ የጋላ ጎሳ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የነበረውን የሥልጣን ድርሻ ካቀረቡት ውስጥ አለፍ አለፍ ብለን ብንመለከት የሚከተለውን እናገኛለን።ገጽ 266 ምዕራፍ 65 ላይ  ቱርኮች በያዙት ቦታ ላይ መንገድ ዘግተው መውጫ መግቢያውን ተቆጣጥረው ማለፊያ  ባሳጡበት ጊዜ  አጼ እያሱ ለማስለቀቅ ዘመቻ ሲያደርጉ  ከቱርኮች ጋር የተመሳጠረው የተንቤኑ ሥሑል ሚካኤል የተባለው ባላባት የራያና አዘቦን ጋላ ውስጥ ውስጡን ቀስቅሶ ሊወጋቸው ሲነሳ ፣ጋሎቹ ዘረፋ ለማግኘት ጭምር በፈረስና በእግር በመምጣት ከንጉሱ ጦር ጋር ውጊያ  ቢገጥሙም ሳይሳካላቸው ተሸንፈው እንደተመለሱ ይገልጻሉ። ቀጥለውም በገጽ 270 ላይ“ አጼ እያሱ ከወሎ ጋላ እስላም ቤተሰብ የሚወለዱትን  ውቢት(ወቢ)የሚባሉትን  ክርስትና አስነስተው ስማቸውንም ወለተ ቤርሳቤህ ብለው ስላገቧቸው ከወሎና ከየጁም በዚሁ ጋብቻ ለመዛመድ ቻሉ። ከወሎና ከዬጁም ብዙዎችን እያመጡ በሥልጣን ላይ አስቀመጡ።” አጼ ኢያሱ አርፈው ከውቢት የወለዱት ልጃቸው ኢዩአስ በነገሰበት ጊዜም በተነሳው የቤተሰብ የሥልጣን ሽኩቻ  የነበረውን የጋሎቹን ድርሻ  በገጽ 271  ምዕራፍ 66 ላይ እንዲህ ያቀርቡታል። “በወይዘሮ ወለተ ቤርሳቤሕና በአጼ ኢዩአስ ጥሪ የወለተ ቤርሳቤሕ ወንድሞች ሉቦና ብርሌ የሚባሉት ሽህ ፈረሰኛ አስከትለው ጦርነት የሆነ እንደሆነ ለእህታቸው ለመርዳት ከወሎ ለመዠመሪያ ጊዜ ጎንደር ገብተው ተቀመጡ።እንደዚሁም እያደር የፈረሰኛም የእግረኛም የጋላ ወታደር በያለቃው እዬሆነ ከወሎም ከየጁም ከራያም እዬመጣ ጎንደር ከተማ በጋሎች ተሞላ።”በዚህ የተነሳ  በጎንደር ቤተመንግሥትና ዙሪያ ጋልኛ ቋንቋ በሰፊው ይነገር እንደነበር በሌሎች የታሪክ መጽሃፍት ተገልጿል። በጣም የሚገርመው ይህ የአቶ ይልማ ደሬሳ መጽሃፍ በድጋሚ በ2007 ዓም ሲታተም ጋላ የሚለውን ስም ኦሮሞ በሚለው ለውጦ ማቅረቡ ነው።ያሳተሙትም ልጃቸው ወይዘሮ ሶፍያ ይልማ ደሬሳ ናቸው።ያባታቸን የታሪክ አቀራረብ ለምን እንደለወጡት ግን ማብራሪያ አላቀረቡም።

ይህንን ታሪክ እንዳነሳ ያስገደደኝ የዘመኑ ምሁራን ነን ባዮች የጋላ ጎሳ ተወላጆች የጋላ ሕዝብ ለብቻው ኦሮሚያ በተባለ አገር በነጻነት የኖረ ፣ከመቶ ዓመት ወዲህ በተፈጠረች ኢትዮጵያ በተባለች አገር ተወሮ ነጻነቱን ያጣ ሕዝብ እንደሆነ የሚነዙት የውሸት ትርክት ትክክል እንዳልሆነ ለማሳዬት ሲሆን ፤በዚህ የውሸት ትርክት ተኮትኩቶ ያደገው የዘመኑ የጋላ ልጅ እውነቱን ተረድቶ እራሱንና አገሩን ኢትዮጵያን ከጥፋት እንዲታደግ ለማሳሰብ ነው።

ጋላ የሚለው ስያሜ ስድብና ንቀት የሚመስለው የዘመኑ ጋላ እራሱን ኦሮሞ ብሎ መጠራትን ይፈቅዳል።ይህ ስያሜ ግን በ18ኛው ክፍለዘመን አጋማሽ ላይ ዮሃን ክራፍ የተባለ ጀርመናዊ ሚሲዮናዊ መነኩሴ  የምሥራቅ አፍሪካን አካባቢ በሃይማኖት ስም አሰሳ ባደረገበት ጊዜ ለጀርመን ቅኝ ግዛትነት ከመረጠው ቦታ የሚኖሩትን የጋላ ጎሳ ተወላጆች መጠሪያ አድርጎ ያወጣላቸው የወራሪዎች የዳቦ ስም ነው።የሚያሳፍረውና ስድብ የሚሆነው የጋላ ማህበረሰብ በጥንት ይጠራበት የነበረውን ስሙንና ማንነቱን በሚገፈው የወራሪዎች ስያሜ ኦሮሞ ተብሎ መጠራቱ ነው።ይህ ኦሮሞ የሚለው ስያሜ የጋላውን ታሪክና ማንነት የሚገፍ እንጂ የሚያስከብረው አይደለም።ስለሆነም በታሪኩና በማንነቱ የሚያምን  የጋላው ማህበረሰብ ወደ ታሪካዊ ስሙ መመለስ ይኖርበታል።ሌላውም ኢትዮጵያዊ ጋላ ወገኖቹን ኦሮሞ ብሎ መጥራቱ ከጀርመኑ የወረራ መልእክተኛ ከሆነው ከዩዋን ክራፍ ጋር አባሪ ያደርገዋል። ለዚህ አንድ ምሳሌ የሚሆን በ1970 መጨረሻ እአአ  ሩት(ROOT)የሚል  ፊልም ወጥቶ ነበር።ፊልሙ የሚያሳዬው አንድ ኩንታ ኪንቴ(Kunta Kinte)የሚባል  አፍሪካዊ በባርነት ተሽጦ የገዛው ነጭ መጠሪያ አፍሪካዊ ስሙን ለውጦ ቶቢ(TOBBI)ብሎ  ባወጣለት ስም እንዲጠራና እሱም ስሜ ነው ብሎ እንዲቀበል በጅራፍ እዬገረፈ ሲያስገድደው ወጣቱ አፍሪካዊ ለሚሰነዘርበት የጅራፍ ቅጣት ሳይንበረከክ ስሜን አለውጥም ፤እምቢ አሻፈረኝ እንዳለ የሚያሳይ ነው።እንግዲህ ከዚህ ፊልም በመማር የጋላ ተወላጆች ባርነትንና የባርነት ምልክት የሆነውን ኦሮሞ የሚል ስያሜ እንደዚህ ጀግና አፍሪካዊ አሻፈረን ብለው ሊጥሉት ይገባል። ወደ ጥንቱ ማንነታቸው ብዛታቸውን ወደ ሚገልጸው ወደ ጋላነታቸው ቢመለሱና ለተከታዩ ትውልድ ቀጣይ ታሪክ ቢያወርሱ የበለጠ ሊያኮራቸው ይችላል።የጀርመኑ ፕሮቴስታንት መነኩሴ ለጋላ ማህበረሰብ  ያወጣውለት ስሙን ብቻ ሳይሆን እምነቱንና ባንዲራውንም እንዲሸከም አድርጎታል።አሁን የሚታዬው እራስ ጠል ስሜትና እምነት እንዲሁም የገዳ ባንዲራ ፍቅር የዚያው ውጤት ነው። እስከቅርብ ጊዜ ድረስም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታወቀው እራሱንም ጋላ ብሎ የሚጠራው ማህበረሰብ እንጂ ኦሮሞ የሚባል ማህበረሰብ አይደለም።ቋንቋውም ጋልኛ እንጂ ኦሮምኛ አይደለም።ይህ ስያሜ ጎልቶ የወጣውና የተራገበው ከአምሳ ዓመት ወዲህ ሲሆን የፕሮስታንትን ሃይማኖት ተቀብለው በፕሮቴስታንት ትምህርት ቤቶች ባደጉና በዃላም  በጀርመኖችና በሌሎቹ  ጸረ ኢትዮጵያ በሆኑት  ድጋፍና እንክብካቤ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በጀመሩት በነበሩትና አሁን ባሉት የኦነግ ድርጅት መስራቾች ነው።

የአማራው፣የትግሬው፣የጉራጌው፣የአፋሩ፣የሱማሌው፣የሲዳማው፣የሽናሹ፣የአገው፣የጋምቤላው፣የጋሞው፣የወላይታው…..ወዘተ ጎሳ ተወላጅ ስምና ታሪኩን እንዲሁም ማንነቱን አክብሮና አስከብሮ፣በማንነቱ ኮርቶ ሲኖር የጋላው ተወላጅ በተለጠፈበት ሰሌዳ (ታፔላ)መኩራቱ ለትውልዱ ሃፍረት ነው። ለግንዛቤ የአፍሪካዊውን ኪንታ ኩንቴ እምቢባይነት የሚያሳይ የታሪክ ምስክር ትዕይንትን(ፊልም) ማዬቱ ይጠቅማልና መግቢያ ባምቧውን(ገንዳውን) ከዚህ በታች አስፍሬዋለሁ። ጋላዎቹም ጋላ ነን ብለው እንዲኮሩ፣ሌላውም  በወራሪዎች ስያሜ ኦሮሞ ብሎ እንዳይጠራቸውና በነባሩ ስማቸው ጋላ ብሎ እንዲጠራቸው ያሳስባል። የጋላ ጊዮርጊስም በዚህ ነባር ስሙ ሲጠራ ይኖራል።ጋላ ጊዮርጊስ ተብሎ በመጠራቱ ምንም ጉዳት አላመጣም፤በሽተኞችንም አልፈውስም አላለም።በሽተኛውም ጋላ ስለተባለ ወደ ቦታው አልሄድም በጠበሉም አልጠመቅም አላለም።

https://youtu.be/BVf4NZIMRrc (ctrl+click) የሚለውን በመጫን መክፈት ይቻላል።ወይም ኩንታ ኪንቴ(ROOT) ብሎ ጎግል በማድረግ ለማዬት ይቻላል።

ጋላነት የተጠላው ጋላ በመባል የተፈጸመ አሳፋሪ ታሪክ በመኖሩና ከዚያ ለማምለጥ ታስቦ ከሆነ ግን አሁን ኦሮሞ በመባል የሚፈጸመው አሳፋሪ ተግባርና ወንጀል ቢበልጥ እንጂ አያንስም።በጋላነት ብልት ይቆረጥ እንደነበረው ሁሉ አሁንም በኦሮሞነት ብልት መቁረጥ ብቻ ሳይሆን በሰው ልጅ ደም መታጠብንም ጨምሯል።ያም ብቻ ሳይሆን በማህጸን ውስጥ ያለን ሽል ሰንጥቆ የማውጣትና የስድስት ወር ህጻን፣የወለደች አራስና ጨቅላ፣የታመሙ አዛውንትና አሮጊቶች በግፍ የተጨፈጨፉበት ጄኖሳይድ የተፈጸመው አሁን ኦሮሞ ነኝ በሚል ትውልድ  ዘመን ነው።ለሰው ልጅ ክብርና ውርደት ወሳኙ ስሙ ሳይሆን ንቃተ ህሊናውና ስነምግባሩ ነው።

ስለ ኦሮሞ ስያሜና ስለሚያውለበልቡት ባንዲራ አነሳስ አቶ አቻምየለህ ታምሩ በቅርቡ ያሰናዳውንና ለሕዝቡ ተደራሽ ያደረገውን ጽሁፍ በሚከተለው አባሪ ማንበብ ይቻላል

ee4 ተዓምረኛው ጋላ ጊዮርጊስ  (አገሬ አዲስ)በተጨማሪም ከቀናት በፊት ከታሪክ ማህደር፣ከባለቤቱ አንደበት በሚል እርዕስ በጻፍኩትና ባሰራጨሁት ጽሁፍ ላይ ነጮች አፍሪካን በተለይም ኢትዮጵያን እንዴት አድርገው ለማዳከምና ለመውረር የሚችሉበትን ዕቅድና መንገድ ለማሳዬት ሞክሬያለሁ፤አሁንም ለማስታወስ ከዚህ በታች ቀንጨብ አድርጌ አስፍሬዋለሁ።

 

ሎርድ ማኩላይ የተባሉት የእንግሊዝ ባለስልጣን በፍብሩዋሪ  2 ቀን 1835 እ.አ.አ አፍሪካን ፣ኢትዮጵያን ዞረው ካዩ በዃላ ለእንግሊዝ ፓርላማ አባላት የሰጡት ማብራሪያ ይህን ይመስል ነበር።   “ በአፍሪካ ከዳር እስከዳር ተጉዣለሁ፤በዚህ አገር ግን አንድም ለማኝ ሆነ ሌባ አላጋጠመኝም፣አላዬሁም።ሃብታምና የሞራል ልእልና ያለው ፣ብልህ የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት  አገር ነው።ይህንን አገር በቀላሉ  ለማንበርከክና በቁጥጥራችን ሥር እናስገባለን ብዬ አልገምትም።ይህ ሊሳካ የሚችለው የአገሩን የጀርባ አጥንት የሆነውን የእምነትና የባህል ጠንካራ እሴቱን ስንሰባብር ብቻ ነው።ስለሆነም ነባሩን የትምህርትና የባህል ተቋሙን በእኛ በመለወጥ የራሱን እንዲንቅና ኩራትና ክብሩን ጥሎ የእኛን እንዲያከብርና እንዲቀበል ስናደርግ ብቻ ነው በመዳፋችን ሥር ሊወድቅ የሚችለው ”በማለት ምክርና አስተያየታቸውን ሰጡ።ያንን ተከትሎ የሆነውን ነገር ታሪክ የሚያውቀው ሲሆን  አሁን ያለንበት ሁኔታም የዚያ ቅጥያ ነው። 22 ተዓምረኛው ጋላ ጊዮርጊስ  (አገሬ አዲስ)

የፈረንሳይ ፕሬዚዴንት የነበሩት ዣክ ሺራክ ደግሞ ስለአፍሪካ  እንዲህ ብለው ነበር-

“ ለአራት ተኩል ዘመን( 450 ዓመታት) አለብናት፤የተፈጥሮ ሃብቷንና ማዕድኗን በዘበዝናት፣ዘረፍናት።ቀጥለንም አፍሪካውያን የማይረቡና ዋጋ ቢሶች መሆናቸውን አምነው እንዲቀበሉ አደረግን።በሃይማኖት ስም ባህላቸውንና እምነታቸውን አጠፋን።አሁን ደግሞ የስልጡን ትህትናና አሳቢ   በሚመስል መንገድ ብቃት ያላቸውን በትምህርት ዕድል(ስኮላርሽፕ) ሰበብ እያወጣን የምሁር ደሃ አደረግናት።የቀረውን ያልታደለ ምስኪን ሕዝብ ብቃት የሌለው ፣እርስ በርሱ እንዲጋጭና አንድነቱ እንዲላላ፣ለአገሩ ልዑላዊነት እንዳይቆም በማድረግ  በእርሱ ድህነት ጀርባ እራሳችንን አበልጽገን በባዶ ቃላት እንሸነግለዋለን”

        

Jacques Chirac did say this about Africa!

PARU LE LUNDI, 06 AOÛT 2018 17:32

In these statements attributed to the 22 French president by social media users, it is

said :

“We drained Africa for 4 and a half centuries. Next, we plundered its raw materials. After

that, we said: they (Africans) are good for nothing. In the name of religion, we destroyed

their culture and now, as we have to act with elegance, we are picking their brains with

scholarships. Thereupon, we are claiming that the unfortunate Africa is not in a brilliant

condition, and is not making elites.We divide them to fight to each other and make them unable to defend their sovereignty. Having enriched on its back, we are now lecturing”

የምዕራባውያንን ተንኮልና ፍላጎት በተጨማሪ የሚገልጸው መረጃ ደግሞ ከዚህ በታች  የመረጃ ቧንቧ(ዩቲዩብ)የተለቀቀው ነው።በመረጃው አፍሪካ በተለይም ከሰሐራ በታች ያሉት አገሮች  እንዳያድጉ ፣የጥሬ ዕቃና ማዕድን አቅራቢ በመሆን ብቻ በዕዳ ተተብትበው ወለድ አገድ አገሮች እንዲሆኑ የተሸረበውን አሻጥር የሚያጋልጥ ነው።

https://youtu.be/d7KEp9wuFSE (ለመክፈት ctrl +click)ወይም Why the West want Sub-Sahara Africa to stay poor በሚለው ጎግል በማድረግ ለማዬት ይቻላል።

 

ማጠቃለያ

ታሪክ እውነተኛና ልብ ወለድ ተብሎ ቢመደብም ልብ ወለዱ ወሬ እንጂ ታሪክ አይባልም።የልብ ወለድ ወሬው ደግሞ ለተወሰነ ጥቅም ሲባል የሚፈጠር አሉባልታ ነው።በዚያ አሉባልታ ደግሞ ማህበረሰብ ሲጋጭና እርስ በርሱ ሲተላለቅ ይኖራል።በአገራችንም በአሁኑም ሆነ ቀደም ሲል የተፈጠሩት ግጭቶችና የእርስ በርስ እልቂቶች የተወሰኑ ሰዎች ወይም ቡድኖች ለራሳቸው ጥቅምና ለሥልጣን  ሲሉ በነዙት ልብ ወለድ ታሪክ ወይም ወሬ ምክንያት ነው።

የሰው ልጅ ከተወለደበትና ከኖረበት ቦታ በልዬ ልዩ ምክንያት ወይም የኑሮ አስገዳጅነት እዬፈለሰ በሌላ አካባቢና መሬት ላይ መኖሩ ዛሬ ወይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተፈጠረ ሂደት አይደለም።የረጅም ዘመን ሂደት ነው።ሌላውን ትተን አሁን በታላቅ አገርነት ብቻ ሳይሆን አህጉር በሆኑት የአሜሪካ፣የአውስትራሊያ፣የካናዳ አገሮች ምስረታና የሕዝብ አሰፋፈር ከአራት መቶ ወዲህ የተከሰተው የሕዝብ ፍልሰት ውጤት ነው።በዚህ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ባላቸው አገሮች ውስጥ በጊዜው የነበረባቸውን ግጭትና አለመግባባት አሶግደው መጤው ከነባሩ ጋር ተቀላቅሎና ተስማምቶ በሕግ ማእቀፍ ሥር የትልቅ አገር ባለቤትና ዜጋ ለመሆን ችሏል።

በኢትዮጵያ አገራችን የተካሄደው የሕዝብ ፍልሰትና መስተጋብር ግን ከነዚህ አገሮች መፈጠር በፊት የብዙ ዘመናት ዕድሜ ያለው ነው።በዚህ የእድሜ ጠገብ ግንኙነት ግን እንደ ሌሎቹ አገሮች የሰላምና የአንድ አገራዊ ስሜት ባለቤት ለመሆን አልረዳውም።ሥልጣን ባሰከራቸው ጥቂቶች በሚያስተጋቡት ጥቃቅን ልዩነቶች በፈጠረው ክፍተት የውጭ ጠላቶች ሰርገው በመግባት በሚነዙት ተንኮል ይበልጥ እንዲራራቅ እርስ በርሱ እዬተጋጨ እራሱንና አገሩን ለውጭ ጠላቶች አሳልፎ ከሚሰጥበት ደረጃ ላይ ወድቋል።

መፍትሔው ሁሉም ተከብሮና ተከባብሮ የሚኖርበት የጋራ አገርና አንዱ የበላይ ሌላው የበታች የማይሆንበት የጋራ መንግሥት መፍጠር ነው።አዲስ አገር መፍጠር ሳይሆን በሁሉም ዜጎቿ ደምና መስዋእትነት የተፈጠረችውን፣ሁሉንም ጎሳ አቅፋ ይዛ የኖረችውን ኢትዮጵያን በጋራ ባለቤትነት አስከብሮ መኖር  ነው።ተበጣጥሶ የመንደር መንግሥታት መመሥረት ከችግርና ከዃላ ቀርነት አያድንም።ይባስ ብሎ ለውጭ ወራሪ ሃይሎች የተመቹ ደቃቃና ደካማ  ቅኝ ግዛቶችን መፍጠር ይሆናል።

ለእያንዳንዱ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖር ጎሳ አብሮት ከኖረውና ከተዋለደው ጎሳ የበለጠ የውጭ አገር መንግሥትና ሕዝብ አይቀርበውም፤አያስብለትምም።ጉዳቱን ፣ችግሩን፣ ባሕሉን፣ታሪኩን፣ በቤተሰብነት በጋራ ተካፍሎት የኖረው ኢትዮጵያዊ  ወገኑ ይሻለዋል።

ስለ እውነት ለመናገር ድፍረቱና እውቀቱ አይለዬን!

አገሬ አዲስ

1 Comment

  1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ውድ አገሬ አዲሥ። ስለጋላ የተባለው እውነት መሆኑ እንዳለ ሆኖ ብዙ ስለተሠራበት አሁን የዘገዬ ይመሥላል። በፊት ጊዜ ኦሮሞ መባል እንደብርቅ በመሥፋፋት ላይ ሣለ አንዳንድ ትልልቅ ሰዎች አዲሱን መጠሪያ አንቀበልም ብለው “አኒ ጋላ’ዳ፤ ኦሮሞን እምቤኩ”ይሉ እንደነበር አስታውሣለሁ። “ኦሮሞ እሚባል አላውቅልህም ጋላ ነኝ” ለማለት ይመሥለኛል። የሆነ ሆኖ ማንም ባሻው ይጠራ፤ አንገታችንን ግን በተውልን። አሁን ባገር ውሥጥ ያለን ዜጎች ሥጋታችን ከመቼ መቼ በየቤታችን መጥተው በሜንጫቸው ይከትፉናል ነው። ሰዎቹ ከላይ ከጠሚው ጀምረው እሥከታች በሥልጣንና በገንዘብ ፍቅር ለይቶላቸው አብደዋል፤ በአብሮነት ያሣለፍነውን ደጉን ዘመን ሁሉ ረሥተዋል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.