ይደረስ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ፤ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዪስ፤ እንዲሁም ለኢፌዴሪ ምክትል አቃቤ ህግ አቶ ተስፋዪ ዳባ።

34ከታምራት ይገዙ

የዛሬን ጹሁፊን በዚህ መንደርደሪያ ልንደርደር !

ነፍሳቸውን ይማረውና በጠ/ሚ መለስ ዘናዊ የአገዛዝ ዘመን አያት ቅድም አያቶቻቸው ተወልደው ባደጉበት ሰፈር በአዲስ አበባ ተወልደው ይሆሩ የነበሩ ውሾች ቀያቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት አገር ለመሰደድ ወደ ዳር አገር በብዛት ጉዞ ጀመሩ። እነዚህ ውሾች ከተወለዱበት እና ካደጉበት ሰፈር መሰደዳቸው ግራ ያጋባቸው የዳር አገር ውሾች ግራ በመጋባትና በማዘን እንዲህ በማለት ጥያቄ አቀረቡላቸው  እንንተ አያት ቅድም አያቶቻችሁ ተወልደው ከአደጉበት እናንተም ተወለዳች ካደጋችሁበት እየነቀላችሁ ወደ ጎረቤት አገር የምትሰደዱት ለምንድን ነው ብለው? ጥያቄ አቀረቡ። እነዚህም አያት ቅድመ አያቶቻቸው በተወለዱበት ከተማ ተወልደው ያደጉ ውሾች ሲመልሱ ”ጠ/ሚ መለስ ዘናዊ በከተማ ውስጥ ያሉና አንድ የዘር ፍሬ ያላቸው ውሾች ሁሉ እየታደኑ ይገደል የሚል በውስጥ ስልክ ተዕዛዝ ባስተላለፉት መሰረት ወንድሞቻችን እየተለቀሙ በብዛት ሲገደሉ ስላየን ከመሞት መሰንበት ብለን ነው ብለው ይመልሳሉ” እነዚያ በዳር አገር ያሉ ውሾች መልሰው እኛ ውሾች እኮ ሁለት የዘር ፍሬ ነው ያለን ብለው እነሱም የዘር ፍሬያቸው ስንት እንደሆነ ለማረጋገጥ በህይወታቸው ለመጀመሪያ ግዜ የየራሰቸውን የዘር ፍሬ በመንካት ማረጋገጥ ገቡ። ቡዙ ሳይቆዩም ሁሉም በአንድ ድምጽ ሁለት ነው ያለን ሁለት ነው ያለን አሉ። እነዚያ የአዲስ አበባ ውሾች በትዝብት አይን እያዩ እንዲህ አሉ አይ እናንተ የአቶ መለስ መንግስትንና የህግ አስፈጻሚያቸውን አልተረዳችሁም እነርሱ የሚያረጋግጡት ከገደሉ ቦሃላ ነው ብለው መንገዳቸውን ቀጠሉ።

ለተከበሩ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፤ የተከበሩ ዶ/ሮ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የፊርዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ፤ የተከበሩ አቶ ተስፋዪ ዳባ የፌዴራል ምክትል አቃቤ ህግ። ይህንን ጹሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ሰሞኑን በአገራችን እየታየ ያለው የህግ ጥሰት በተለያዩ ደረጃ ያሉ የመንግስት ባለስልጣኖችም ሆኑ የህግ አስከባሪ ፖሊሶች ደጋግመው የህግ ጥሰት በማሳየታቸው እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የተሰማኝን ቅሬታ ለመግለጽ ነው።

እኔን ይበልጥ ያሳሰበኝ ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ነጻ ነን ብለው ቃል የገቡት የፍትህ አካላት እንደ አንድ ተራ ካድሬ ለግለሰቦች የስልጣን ሙስና ሲከራከሩ ስንሰማ በጣም የሚያሳፍር ነው። ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እርሶ ይህንን ከፍተኛ ቦታ በሃላፊነት በተቀበሉበት እለት ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዲህ ብለው ነበር ”የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሪዝዳን ሆኔ በመመረጤ የኔ ተቀዳሚ ስራ የሚሆነው ህብረተሰቡ በፍትህ ስራአቱ ላይ  እምነት እንዲያድርበት ማድረግ ነው።” November 2/2018.

አሁን ከሁለት ዓመት ቦሃላ በእርሶ እምነት ያንን ያደረጉ ይመስሎታል? ይህንን ዓይነት ጥያቄ ለመጠየቅ ያስገደደኝ ሁሉንም ትቼው ሰሞኑን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በታሰረበት ወቅት በእርሶ ስር በቅርብ ያለትና የፖለቲካ ንኪኪ የላቸውም በመባል ምክትል አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት አቶ ተስፋዪ ዳባ ለወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመወገን የተናገሩት ንግግር ከአንድ አቃቤ ህግ የሚጠበቅ አይደለም ፈጽሞ የሚታሰብ አይደለም ታዴያ እንዴት ነው እንደዚህ አይነት ለመብላት የሚኑሩ ሰው ከአጠገቦህ አስቀምጠው ህዝብ በፍትህ ስርዓቱ ላይ እምነት የሚኖረው? በርሶ ስልጣን ስር የሆኑ ሰዎች ይህንን ዓይነት ቅሌት ሲፈጽሙ አይቶ አንዳላየ ማለፉን ሒሊናዎት እንዴትስ ፈቀደ ምክንያቱም ስለእርሶ በህዝብ ፊት የሚነገረውና እርሶ የሚሰሩት ለየቅል ሆኖ ተመልክቼዋለው። እንደ አቶ ተስፋዪ አይነት የህግ ጥሰት የሚፈጽሙ ግለሰቦችን ከተቀመጡበት ወንበር ማንሳት እና ለሌሎቹ ትምህርት መስጠት ተገቢ ነው እንጂ አብሮ መስራት ቀስ በቀስ እርሶንም ማስናቁ አይቄሬ ነውና ቢታሰብበት ይሻላል። ሌላው ጥያቄዪ እውነት ስልጣኑ አሎት ወይስ ለይስሙላ ነው ወንበሩ የተሰጦት? ምክንያቱም በእርሶ የስልጣን ዘመእን ልክ በአቶ መለስ ዘምን እንደነብበሩት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሪዝዳንቶች ዜጎች ያለ ጥፋታቸው በማንነታቸው ሲገደሉና ሲታሰሩ የእለት ተእለት ዜና በመሆኑ ነው።

የተከበሩ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶ/ሮ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በአዲሱ ዓመት እንዲህ ብለው ነበር ”የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሙያዊ ብቃትን እና ስነ-መግባርን መሰረት በማድረግ መንግስትና ህዝብን በሚገባ ለማገልገል ይሰራል።” መስከረም 2013 ይህንን ባሉበት ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ የርሶ ምክትል የሆኑት አቶ ተስፋዪ ዳባ የወ/ሮ አዳነች አቤቤ አፈቀላጤ ሆነው ሲያገኞቸው ምን ተሰማዎት? የርሶስ የበላይ መሆን ፋይዳው ምንድን ነው? ያሰቡትንና ያለሙትን እንዳይፈጽሙ ምክትሎት ተግተው የሚሰሩ ከሆኑ የርሶ የበላይ መሆን ምኑ ላይ ነው ቁም ነገሩ። የሚገርመው ከሁለት አመት በፊት ህወሀት የሚሾማቸውን ባለስልጣኖ በምክትሎቻቸው ነበር የሚያስገመግማቸውና እንዲዋረዱ የሚያደርጋቸው ለውጥ መጣ ከተባለም ቦሃላ እያየን የለው ያለፈውን ፊልም ወደ ኋላ እያጠነጠኑ የሚመለከቱት ይመስላል ታዲያ እርሶ ለንደዚህ ዓይነት ሴራ ይበገሩ ይሆን?

አቶ ተስፋዪ ዳባ ምንም አይጠራጠሩ ትላንትና ምን እንደነበሩና ምን ይሰሩ እንደነበር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቀዋል ነገሩ ትላንትን እያሰብን ወደ ነግ እንሂድ በማለት ነው እንጂ ሲሾሙም ህዝቡ ቅሬታ ነበረው እርሶ ግን አልታወቀብኝም በማለት ነጻ ሆነው ለመታየት ቢሞክሩም “ደመት ሞልክሳ አመሏን አትረሳ” ነውና ያው ባልጠበቁትና ባላሰቡት ሰዓት አመሎት ብቅ አለ። አለቆቾትም ለእርሶን የተሰጠውን ወንበር ቀምቶ ሙያዊ ብቃትን እና ስነ-መግባርን መሰረት በማድረግ መንግስትና ህዝብን በሚገባ ለሚያገለግል ሰው መስጠት ሲገባቸው ሆድ ይፍጀው ብለው የተቀመጡ ይመስላል ምናልባት እርሶም ያንን አይነት ቅብጠት የቀበጡት “ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ከበራፍ ውጪ ታሳድራለች” ሆኖ ይመስለኛ ይህንን ዓይነት በለጊዜነት አያዋጣም እነ አቶ በረከት ስሞኦን የት እንዳሉ ላያ ሰው።

በማስከትል በመላው ኢትዮጵያ ላላችሁና በዳኝነት ሞያ ተሰማርታችሁ አገራችንንና ኢትዮጵያን እና  ህዝባችንን በግልጽነት ፤በቅንነት እንዲሁም በተጠያቂንት የምታገለገሉ ዳኖች የሚደርስባችሁን ጫና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቅዋል ይህንን ጫና ተቋቁማችሁ የምታሳልፉትን ዳኝነት ህግ አስከባሪው ፖሊስ በተለያየ ምክንያት ተግባራዊ እንዳይሆን ጫና ሲፈጥር እያየንና እየሰማን ነው ይህ ከህግ በላይ የመሆን አባዜ የሚቀጥል ከሆነ ሞያችሁን የምታስከብሩት እንደ ሞያ ማህበር አባላትነታችሁ በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁ ዳኞች በማንኛውም መንገድ ተነጋግራችሁ የምንወስነው ውሳኔ የማይሰማ ከሆነ ከዚህ ቀን አንስቶ እስከዚ ቀን ድረስ የስራ ማቆም አድማ እናደርጋለን ብላችሁ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በጹሁፍ ማቅረብ ነው። ያን ግዜ በሳምንት ግዜውስጥ አደለም  በመጀመሪያዋ ቀን የናንተን ዋጋ ምን ያህል እንደ ሆነ ይገነዘቡታል። ይህንን የማታደርጉ ከሆነ ከራሳችሁ ሂሊና ጋር እየተቃረናችሁ መኖር ነው የሚጠብቃችሁ ይህ ደሞ ።

በመጨረሻም ለተከበሩ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እንዲሁም ለተከበሩ ዶ/ሮ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የፊርዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያለኝ መለእክት ህዝቡ በናንተ ላይ እምነት እንዲኖረው የተሰጣችሁን ስልጣን በሚገባ ተጠቀሙበት ህዝቡ የሚገነዘበው ወንበሩ ላይ ስትቀመጡ ስልጣናችሁ ሳይሸራረፍ እንደ ተሰጣችሁ ነው። እናንተ እንስራ ስትሉ የማያሰራ ሃይል ከለ ግን በህዝብ ፊት ለመስራት ቃል እንደገባችሁት ሁሉ እንዲሁ መስራት የሚያስችል ሁኔታ ስለሌለ ስልጣናችንን በፈቃዳችን ለቀናል ብላችሁ ለህዝብ ማሳወቁ ይጠበቅባቸዋል የሚል እምነት አለኝ ያለዚያ ግን በናንተ የስልጣን ዘመን እየተሰራው ላለው በደል ከመጠየቅ አትድኑም ከናንተም አልፎ ለልጅ ልጆቻችሁ የሚተርፍ የታሪክ ጠባሳ ነው ትታችሁ የምታልፉት በተጨማሪ ያለው የግፍ ስራን ስላልታደጋቹት  በሒሊናችሁም በህዝብም ዘንድ ስትወቀሱ ነው የምትኖሩ መሆኑን ከወዲሁ ልትገነዘቡ ይገባል።

ፈጣሪ አገራችንን ኢትዮጵያ በይቅርታው ይታደጋት !!

 

 

 

1 Comment

  1. ተጠያቂነትን እንዲህ ዘርዘር አድርገን ባለቤት ስንፈልግለት የህግ የበላይነትን ከማስከበር እና ለዲሞክራሲው ልምምድ ትልቅ አስተዋጻኦ ይኖረዋል፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.