በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የዐማራ ኮምኒቲ ማህበራት እና ሲቪክ ድርጅቶች የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

Flagቀን: ጥቅምት 21/2013.

በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ እና የአለም አቀፉ የዐማራ ህዝብ ንቅናቄ አካል የሆንን የኮምኒቲ ማህበራት እና ሲቪክ ድርጅቶች ለጥቅምት 18/2013 ዓ.ም በዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የተጠራውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አስመልክቶ ባስተላለፍነው የድጋፍ መልዕክት በዐማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን መንግስት መር ስርዓታዊ የዘር ጭፍጨፋ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘብ እና ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥ በዚሁ በምንገኝበት ሰሜን አሜሪካ በተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንደምንጠራ መግለፃችን ይታወሳል::

በመሆኑም የተለያዩ የአገር እና ወገን ተቆርቋሪ ስብስቦችን ፣ የሚዲያ ተቋማትን እና ግለሰቦችን በማስተባበር በዋሽንግተን ዲሲ እና በሌሎችም የሰሜን አሜሪካ ከተሞች በአንድ ቀን የሚደረግ ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅተናል::

የሰላማዊ ሰልፉ አላማ ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት መዋቅር የቀጥታ ተሳትፎ እና ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ በሚመሩት ድርጅት ኦህዴድ የፋይናንስ እና ወታደራዊ ስልጠና ድጋፍ በሚደረግላቸው ፅንፈኞች አማካኝነት በዐማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማጋለጥ ነው::

የዶ/ር አብይ አስተዳደር የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ቀዳሚ መንግስታዊ ኃላፊነቱን ባለመወጣት ፣ በወንጀሉ በቀጥታ በመሳትፍ እና ፅንፈኞችን በፋይናንስ እና ስልጠና በመደገፍ የዘር ጭፍጨፋው አካል ከመሆኑም ባሻገር እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተራ ግጭት ለማስመሰል እና ወንጀሉን ለመሸፋፈን በታቀደ መንገድ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጀምሮ ልዩ ልዩ የትኩረት ማስቀየሪያ መንገዶችን በመተግበር እንዲሁም የዘር ማጥፋት ወንጀሉን በሰላማዊ መንገድ ለመቃዎም የሚወጡ ዜጎችን በማፈን ወንጀሉ እንዳይጋለጥ እና ጭፍጨፋውም እንዲቀጥል እየሰራ ይገኛል::

ውድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን የዐማራ ህዝብ በማንነቱ ተለይቶ በህይወት የመኖር ተፈጥሯዊ መብቱን ተከልክሎ በተገኘበት ቦታ ሁሉ ኢ-ሰባዊ በሆነ ሁኔታ ሲጨፈጨፍ ፤ ድርጊቱን ለመቃወም ሰው መሆን በቂ ሰለሆነ ፤ ከዛም በላይ አገር የሚባለው ፅንሰ ኃሳብ ያለህዝብ ከንቱ መሆኑን በመገንዘብ የዐማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን ስርዓታዊ የዘር ጭፍጨፋ ለመቃወም በጠራነው ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ በመሳተፍ እንደሰው ፤ እንደ ህዝብ እና እንደ አገር የሚያስተሳስረንን ውል ለወገናችሁ ድምፅ በመሆን በተግባር እንድታሳዩን እንጠይቃለን::

ሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበት ቀን: November-14/2020

ሰዓት: 10AM (EST)

ቦታ: US CAPITAL GROUND, WASHINGTON DC, 20016

ማስታዎሻ:

  • ሰልፍ ስትወጡ የአፍ መሸፈኛ ጭምብል(mask) ማድረግ እንዳትረሱ
  • በሌሎች የሰሜን አሜሪካ ከተሞች በተመሳሳይ ቀን የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችን ዝርዝር መረጃ ወደፊት እናሳውቃለን::

በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የዐማራ ኮምኒቲ ማህበራት እና ሲቪክ ድርጅቶች

1 Comment

  1. ኖቬምበር 14 አይረፍድም? ነው ወይስ እስከዚያው ሌላ ጥቃት ይፈጸማል ተብሎ ተነግሮአችኋል? ወያኔ እኮ ተንኮለኛ ነች፡፡ ነገረ ስራዋ ሁሉ ጭር ሲል አልወድም ነዋ! ሥዩም መስፍን በግልጽ ነገረን አይደል? በዚያ ላይ እነ አይጋ ፎረም “where are you our cousins” እያሉ የአድኑን ጥሪ እያቀረቡላችሁ ነው፡፡ በማውቅም ይሁን በስሜታዊነት ተባባሪ አይጠፋማ፡ ሌላው ደግሞ ሌላ ሃሳብ ይኖረዋል; እና ሰልፍ ብላችሁ ብቻ ጭራሽ የአማራውን ከፍፍል አደባባይ እንዳታሰጡት፤ በቅድሚያ አብኖችን በደንብ ጠይቋችው፡፡ ዉሽት ነው፡ ቋንቋ ብቻውን አንድ አያደርግም፤ ብዙ የህዝብ ቁጥር ሲኖረውና አካባቢው ሲስፋ ደግሞ የበለጠ ያስቸግራል፡ ጃዋርም የሳተው መሰረታዊ ነጥብ እሱን ነው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.