እውን ዲሞክራቶች ለኢትዮጵያ የተሻሉ ናቸው? – አሁንገና ዓለማየሁ

በአሜሪካ ያሉት ሁለት ፓርቲዎች ሪፐብሊካን እና ዴሞክራት ተብለው ይታወቃሉ። ሥርዓቱን ያነበሩት ሃብታሞች እንደመሆናቸው የሥርዓቱ ተቀዳሚ ዓላማ የካፒታሊስቱን መብት ባስጠበቀ መልኩ ሀገርን ማስተዳደር ነው።  በዚህ መሃከል አንደኛው ለሠራተኛው መደብ የተሻለ ተሟጋች መስሎ አንደኛው ደግሞ ለከበርቴው ሽንጡን ገትሮ በመከራከር ይታወቃሉ። እርግጥ አሜሪካን በሚያህል ግዙፍ ሀገር ያሉት ብዙ ፖለቲካዊ አስተሳሰቦችና ዝንባሌዎች በሁለት ፓርቲ ብቻ የሚወከሉበት ሥርዓት ራሱ ዲሞክራሲ የሚባለው በጥበብ የተበጀ ፌዝ ነው። በመንደር ደረጃ የተለያየ ፖሊሲ ለውጦችን እያመጣ በሀገር ደረጃም የፊት ለውጥን እያሳየ የሕዝብን የለውጥ ፍላጎት እያስተነፈሰ የሚሄድ ውጤታማ ሥርዓት እንጂ የከበርቴውን  ሥርዓት የሚያናውጥ አንዳች የለውጥ ፍላጎት ቢነሳ ፈጽሞ ሊስተናገድበት የማይችል ነው። በውጭ ፖሊሲው ደግሞ ይበልጥ በወጥነት የአሜሪካን ኩባንያዎችን ጥቅም በማስጠበቅ ላይ የተመሰረተ ነው — የየትኛውም ፓርቲ ሥልጣን ላይ ቢወጣ። እንደዚህም ሆኖ የትኩረት አቅጣጫዎቹ ሁለቱን ፓርቲዎች እንደሚቆጣጠሯቸው ኩባንያዎች ይወሰናሉ።

Democratይህንን እንደመንደርደሪያ ካየን እስኪ ዲሞክራቶች ሥልጣን ላይ በወጡ ዘመን በኢትዮጵያ እና ምሥራቅ አፍሪካ በአጠቃላይም አፍሪካ ላይ ያላቸውን ውሎ እንይ። ከሪፐብሊካኖች የተሻሉ ናቸው ወይ? ይህንን የምናየው ኢትዮጵያውያን በምርጫ ትራምፕን አባርረን ዲሞክራቶችን የመሰየም የተሟላ አቅም ባይኖረንም ብዙዎቻችን በተለይም በሰሞኑ የትራምፕ ንግግር ዲሞክራቶችን ለመምረጥ የቆረጥን ስለሚመስል ነው። (በግሌ ትራምፕን ባልወደውም የአንድ ሀገር መሪ ሆኖ ሲመረጥ እጅግ ብልህነትና የሕዝቡን ሥነ ልቡና ማወቅን ስለሚጠይቅ ለመናቅና ለመስደብ አልፈልግም። እሱ ተሳዳቢ ቢሆንም። ነጋዴ ስለሆነም ለመደራደር ሲል የሚያወራውና የሚሠራው እንደማይገናኙ የታወቀ ነው። ዛሬም የአረብና የይሁዲዎችን ድምጽ ለመጠቅለል ጥቅም—ጉዳቱን cost-benefit analysis አጥንቶ የሚለውን ብሎ በ“ሚስጥር” ለቅቶታል። ) ዲሞክራቶች የእኛንም ድምጽ ባያገኙ ሊመረጡ ይችላሉ። ሥልጣን ላይ ሲወጡ ግን ከትራምፕ የከፋ ጉዳት በሀገራችን እና ከባቢዋ ላይ ያመጣሉ የሚል ሥጋት አለኝ።  ይህንን ሥጋት በመግለጽ ሰዎች ትራምፕን እንዲመርጡ ለማድረግ ሳይሆን ሰዎች ዐቢይ አህመድ ሥልጣን ላይ ሲወጣ በከንቱ ተስፋ ተሸውደው ሀገርን ለአጥፊዋ እንደተዋት በዚህም ረገድ ለመጭው ጥፋት ሳይዘጋጁ እንዳይቀሩ ስለመጪው አደጋ ከወዲሁ የሥነ ልቡና ዝግጅት እንድናደርግበት ለማሳሰብ ነው። ለዚህም  ዲሞክራቶች ሥልጣን ላይ በወጡ ዘመናት የደረሰብንን በደል በማስታወስ ማንነታቸውን እንድናይ እመክራለሁ።

ኮሚኒዝም በኢትዮጵያ የመንግሥት ሥርዓት ሆኖ ሀገራችን ለአሥራ ሰባት አመታት የውድመት ቀጠና እንድትሆን የፈረደባት ማን ነው? በካርተር የተመራው የዲሞክራቶች መንግሥት ነው። ሶማልያ በሶቪየት ዩኒየን እስካፍንጫዋ ታጥቃ ለወረራ እንደተዘጋጀች እየታወቀ ምንም ዓይነት ወታደራዊ ድጋፍ ሳያደርግ ቆየ።  ሶማልያ ወረራውንም አካሄዳ ከ700 ኪሜ በላይ ስትገባ፣ የጦር ስምምነት እና ሦስት ወታደራዊ ቤዞች በኢትዮጵያ የነበረው የአሜሪካ መንግሥት የክህደት ተግባር የፈጸመው በዲሞክራቶች አመራር ሥር ነው። በሚመራት ሀገር ላይ የሕልውና አደጋ የተደቀነበት ደርግ ወደ ሶቭየት እቅፍ የገባው በዲሞክራት መሪዎች  እብሪት ነው። ስሌታቸውም ኢትዮጵያ ብትወድምና ብትፈራርስም እነሱ ቀደም ብሎ ያስፈለጋቸው የአስመራ ቤዝ በሳተላይት ቴክኖሎጂ ምክንያት የማያስፈልጋቸው መሆኑ እና በኢትዮጵያ ልዋጭ ሰፊ የሕንድ ውቅያኖስ ጠረፍን በሱማልያ በኩል የማግኘት እድል እንዳላቸው ስላወቁ ነበር።

ቀጠናውን በተመለከተም ቀጥሎ የመጡት ዲሞክራት መንግሥቶች እነ ክሊንተን የመሩት ኤርትራን ያስገነጠለ፣ ሶማልያን መንግሥት አልባ ያደረገ፣ በኢትዮጵያ ላይ የአፓርታይድ ሥርዓት ያነበረ ነው። ቀጣዩ የዲሞክራቶች መንግስት ኦባማ እና ሂላሪ ክሊንተን የመሩት ሊቢያን ከማፈራረሱ ሌላ ኢትዮጵያም ውስጥ የተጭበረበረውን ምርጫ የሚያደርግ አሸባሪ መንግሥትን ዲሞክራሲያዊ ነው እያለ እያሞካሸ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሰቆቃ ላይ ያላገጠ ነበር። በኦባማ ጊዜ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰላሳ በላይ ሀገሮች የአሜሪካ ጦር/ የጦር መሣሪያ ማስፈሪያ የተደረጉበት ከቅኝ ግዛት በመከራ የተላቀቀች አፍሪካ 50 ዓመት ሳይሞላት መልሳ በነጮች ጦር የተወረረችበት አሳፋሪ የውርደት በር ከፋች ዘመን ነበር። ነጮች አፍሪካን ጥቁር ማስክ (ኦባማን) አጥልቀው ዳግም የወረሯት ዘመን ነው ለማለት ይቻላል።

ዛሬም ከዴሞክራቶች ጀርባ የሕዝብ ቅነሳን የሃይማኖት ድምሰሳን አጀንዳ ያደረጉ ታላላቅ ሃብታሞችና ሃብታም ኩባንያዎች ከትራምፕ አፍ እላፊ እጅግ ለከፋ ጥፋት የተዘጋጁበት ወቅት ነው። እነዚህ ሰዎች ወደ ሥልጣን እንዳይመጡ ማድረግ የማይቻለው ወገናችን ቢያንስ ግን በአጉል ተስፋ ተሞልቶ በሀገሩ ስልጣን እንደተቆናጠጡት አስብቶ አራጆች እነዚህንም ተዘናግቶ በመጠበቅ ለከፋ ጥፋት እንዳይዳረግ የራሱን የቤት ሥራ ሠርቶ መጭውን ዘመን በንቃት መከታተል ይገባዋል። ከነዚህ ዴሞክራት ተብዬዎች ውስጥ በአፍሪካ ዴስክና በኢትዮጵያም ተመድበው የመለስ ዜናዊን አፓርታይድ ሥርዓት መሠረት ሲጥሉ፣ ምሶሶ ግድግዳና ማገር ሲያዋቅሩ የነበሩ የሀገራችን ጉድጓድ ቆፋሪዎች አሉ።

የዘረኝነትን አጀንዳም ከፈተሽን በኦባማ ጊዜ ነው በትራምፕ ብዙ ሕዝብ ከአሜሪካ እንዲባረር የተደረገው? በትራምፕ

በኦባማ ጊዜ ነው በትራምፕ ብዙ ሚክሲካኖች የተባረሩት? በትራምፕ

በኦባማ ጊዜ ነው በትራምፕ ብዙ ጥቁሮች በፖሊስ የተገደሉት? በኦባማ

ኦባማ ራሱ የተማረበት የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆነው ሰው በገዛ መኖሪያ ቤቱ በር ላይ ፖሊስ ሊባ ብሎ ይዞ አስሮ እያዳፋ ጣቢያ እንደወሰደው ሰምቶ ኦባማ ይህን ድሪጊት ደደብ (stupid) በማለቱ ወንጀለኛውን ነጭ ፖሊስ ኦባማ ይቅርታ እንዲጠይቅ የተደረገ ነበር። ዋይት ሃውስ ውስጥ ቁጭ ያረጉት ጥቁር አሻንጉሊት ፕሬዚዳንት ነበር ለማለት ያስደፍራል። ኦባማ ሥልጣን ላይ ስለነበር ጥቁሮች እንደውሻ በፖሊስ እየተገደሉ በየጥሻው ከመውደቅም ሆነ በሁሉም ረገድ ከእድገትና ብልጽግና መንገዶች በተጻፉና ባልተጻፉ ሕጎች የተገለሉ ከመሆን አላዳናቸውም።  በኦባማ መመረጥ የጥቁሮች ትግል ቀዝቃዛ በረዶ ነው የተቸለሰበት። ልክ ዶ/ር ዐቢይ ሥልጣን ላይ ሲወጣ በድቡሽት ላይ በተመሠረተው የኢትዮጵያውያን አጉል ተስፋ ምክንያት ዲሞክራሲያዊና ጸረ ኢህአዴግ ትግሉ ብትንትኑ እንደወጣው።

ዲሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች በአሜሪካ ውስጥ እንደየሰፈሩና እንደየ “ኢንተረስት ግሩፑ” የተለያየ ጥቅምና ጉዳት ያላቸው ፖሊሲዎችን ያራምዳሉና እያንዳንዱ አሜሪካዊ ከዚህ አኳያ ምርጫውን ያደርጋል። በአፍሪካ ደረጃ ግን ሁሉም የአሜሪካን ጸረ—አፍሪካ ጥቅም ተኮር ፖሊሲ አራማጅ ቢሆኑም፣ የምሥራቅ አፍሪካን ፖለቲካ በተመለከተ ታሪካቸው በጉልህ የሚያመለክተው ዲሞክራቶች የበለጠ የከፉ እንደሆኑ ነው። ዛሬ ደግሞ በአድማሱ ላይ ረሃብ፣  የእርስ በእርስ ጦርነት እና የጎረቤት ሀገራት ጦርነት ቆመዋል። ሚሊዮናትን ለማፈናቀል ሚሊዮናትን ለማውደም እየተደገሰ መሆኑን ተሸፋፍኖ ያልተኛ ሁሉ የሚያየው ጉዳይ ነው። ከዚያ በከፋ ደረጃ ደግሞ በክትባት መልኩ እየመጣ ያለ ምንነቱ በውል የማይታወቅ ከሕዝብ ቅነሳ እስከ ሲዖል ጭፍራነት ድረስ መዘዝ አለው ተብሎ  የተሰጋ አደጋ ተደቅኗል።

ጠላቶቻችን ለራሳቸው ዓላማ በገደቡት ግድብ ዙሪያ የእቴጌ ጣይቱን ማስተዋል ተጠቅመን ተንኮላቸውን መግለጥ እንጂ ዓይናችንን ጨፍነን ዘራፍ ዘራፍ ብንል “በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ” ይሆናልና እናስተውል። ሰሞኑን ግድቡ ለምን እንደተገደበ ብቻ  ሳይሆን የተገደበበት ቦታ (ከሦስቱ ተሻይ አማራጮች) ለምን እንደተመረጠ ሁሉ እስከዛሬ ከቀረበው ማደናገሪያ የተሻሉ አሳማኝ ትንተናዎች እየወጡ ስለሆነ ልብ ገዝተን ቀኝና ግራ አይተን ጠላት ወዳጅ ለይተን እንጓዝ። ባድሜ! ባድሜ! ብለን ሀገር ሻጮች ያውለበለቡልንን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ተከትለን ሻዕቢያ ጉድጓድ ውስጥ እንደተቀበርነው ዓይነት ጅልነት ልንደግም አይገባም።  ያንን ሥነልቡናችንን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ዛሬ ደግሞ ዓባይ! ዓባይ! እያሉ ሌላ ጉድጓድ ውስጥ ሊቀብሩን ሩጫ ላይ ናቸውና። መጀመሪያ ሀገር ሲኖር፣ ሰላም ሲኖር፣ ፍትሕ ሲኖር፣ ወጥተን መግባት ስንችል ነው — ሁሉም ከዚያ በኋላ ነው።

በቸር ያሰንብተን

ብሔርና እምነት ተኮር የሰላማውያን ጭፍጨፋ ይብቃ!

ከወረርሽኝ ተርፈን በክትባት ከማለቅ ያድነን።

 

አሁንገና ዓለማየሁ

5 Comments

 1. Small business owners Ethiopians are better off with democrats for all the tax breaks we get when democrats are in office. Currently the majority of Ethiopians in America are ride share car UBER or Lyft drivers who are considered as owners operators small business owners who can benefit highly if democrats are in office that is why it looks like the democrats got the Ethiopians vote in USA. Democrats got the majority of the Ethiopians votes not because the democrats got better foreign policies towards Ethiopia but for the generosities the democrats have towards poor immigrant business owners because the foreign policy they got towards Ethiopia is not so different.

 2. ወጣም ወረደ ም ምእራባውያን ለአፍሪካ ያችን የርዳታ ብር ስንዴና ቦንዳ ከመላክ በስተቀር ጥሩ የእድገት ወዳጆች አይደሉም:: ህዝቧን ይንቃሉ:: ማእድንዋን ይዝርፋሉ:: ከአምባገነኖች ጋር በመተበር ገንዘቧን ይዘርፋሉ:: ትረምፕ ደግሞ ለየት ይላል:: በሪፐብሊካኒነቱ እንኳን ባይሆን:: እርሱ ለአለም ና ለአሜርካ ራሷ ሴኩሪቲ ሪስክ ነው::
  አፍሪካዊ ዘር ያላቸው ዜጎቹ “from shit hole country “, ስደተኞችን “low IQ”. እያለ ሚሳደብ : ዘረኛ: የአለም አገሮችን ዲፕሎማሲ ባፍ ጢሙ የገለበጠ…ወዘተ: ስው በመሆኑ ብዙ የራሱ ሪፐብሊካን አባላት ሳይቀር (Lincoln project) እንዳይመረጥ እየጣሩ ነው::
  ስለዚህ ትረምፕን ያለመምረጡ ምክንያት ዲሞክራቶች ጥሩ ስለሆኑ ታስቦ ብቻ ሳይሆን ስውየው ባህሪው ለቢሮው የሚመጥን ስላልሆነም ጭምር ነው:: ኢትዮዽያ ላይ ካሳየው ዛቻና ክፋት በተጨማሪ:
  ከሌሎች ምክንያቶች በተጨማሪ ስውየው በለፈው ምርጫ ከግብፅ ለምርጫ ከ 10 ሚልዮን በላይ ድጋፍ እንደተስጠው CNN ሲዘግብ ስለነበረ የግብፅ ውለታ መክፈል ነበረበት ::
  እርሱን ከመምረጥ አርፎ እቤት መቃመጥ ወይም እንዲሽነፍ ዲሞክራት መምረጥ ግድ ነው!!

 3. የአሜሪካ ምርጫ የአሜሪካዊያን ነው፤ እኔ አያገባኝም። ትራምፕ ለተናገረውም ከሰልፍ ይልቅ በዲፕሎማሲ ቋንቋ መልስ ተሰጥቶ ቢታለፍ ይበቃ ነበር እላለሁ፤
  ሁለት ነገር ብቻ ላንሳ፡፡
  1። እርስዎ ያሉት ሁሉ ሆነ፤ ታሪክ ሆኖ አለፈ፤ አሁን እዚህ ደረስን፡፡ ዛሬ Oct 30 2020 ነው፡፡ አሁን የተጀመረውን ግድብ ምን እናድርገው? አድበሰበሱት፤ በተለይ የመጨረሻው ፓራግራፍ ውስጥ የሚያውቁት “ትልቅ ሚስጥር” ያለ ይመስላል፡፡ ግልጽ አድርገው “እንዲህ ይሁን” ቢሉ!
  2። የደርግ አስርአለቆችን፤ የኢሰፓን [እነዚህ እንኳ ምሁራንም ነበሩበት ብቻ ምን እንደነካችወ እንጃ!] እና የጥራዝ ነጠቅ “ግራ ህይሎች” ስህተቶችን ሁሉ ወስደው ለአሜሪካ አሽክሙት? የደርግ ባለስልጣኖችና ኮ/ል መንግስቱ የሚነግሩንን ማለት ነው፡፡ ስላቅ ሆኖ “የአሜሪን ኢምፔሪያልዝም ይውደም” እያልን በየአደባባዩ ግራ እጅ እያነሳን እንዳላቅራራን በመጨረሻም እነሱው አሜሪካኖች ናችው ጥገኝንት ሰጥተው ማትረፍ የቻሉትን ያተረፉት፤ እዚያ ተወልደው ያደጉት ልጆቻችንም “I’m an American: my parents immigrated from [Ethiopia]” አሉና አረፉት፡፡ የማንም ኢሚግራንት ልጅ እንደሚለው ማለት ነው፤ cos it is by system design! ታዲያ ለሆነው ነገር ትንሽ እንኳ የራስ ሃላፊነት መውስድ አይገባም?

  እንዲህም “ተቀልዶ” ነበር፡፤ ጓድ አብደላ ሶኔሳ የሚባሉ በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ገበሬዎች ማህበር ሊቀመንበር ነበሩ፤ የኢሉባቦር ሰው ናቸው፡፤ “ሰው በላው የአሜሪካን ኢምፐሪያሊዝም…….” በተደጋጋሚ እያሉ ካድሬዎች ሲያስተምሩ ሰምተው ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አሜሪካን ሲሄዱ ያዩት ነገር ድንቅ ሆኖባቸው “አንግዲህ ይህ ነው ሰው በላው የሚባለው ማለት ነው?” ሲሉ ጠየቁ፡፡ ካድሬው “አዎ” ሲላቸው፤ ጓድ አብደላም በፍጥነት እና በለሆሳስ “ምነው እኔንም በበላኝ” አሉ ይባላል፡፡

  በስተመጨረሻ ያሉትን ሁለት መፈክሮች እኔም ደግሜ አሰምቻለሁ፤ ቅን አስተዋጽኦዎ ይታክልበት!

 4. ረስቼው ለሬኮርድ፡
  የካርተር መንግስት የጦር መሳሪያውን የከለከለው ደርግ [በተለምዶ] 60ዎቹን ሚንስትሮች ያልፍርድ፤ ይባስ ብሎ እጅ እያወጡ በድምጽ ብልጫ፤ ሞት ፈርደው ከረሸንዋቸው በሁዋላ “እነዚህ ሰዎች [ደርግ] ወዴት እየሄዱ እንደሆነ ግልጽ እስኪሆን ድረስ” በሚል ነው፡፡ ይቺ “አሜሪካኖች ገፍተውን ነው ወደ ሶሲያሊስት ካምፕ የገባነው” የምትል ምክንያት ሌላ ችግርም አለባት፡፡ ይኀውም “ሶሺያሊስት ካምፕ የሄድነው ያለፍርድ መግደልን እንድንቀጥል ባያበረታታም ተጠያቂ ሰለማያደርግ ነው፤” እንደማለት ነው፡፤ ለነገሩ ሊሆንም ይችላል!

 5. 1) Well, your piece sounds informative about the very well-known game of world politics and international relations .It is the right thing to remind ourselves that any ruling parties or governing body’s first and foremost responsibility and objective is to protect and advance or promote the national interests it represents. It goes without saying that you call it world politics or international relations of foreign policy or diplomatic relations is the function of fulfilling this principle and objective of national interest.
  But, it must be noted here that although the protection and advancement of national interest is the bottom line, the question of how to approach and deal with world politics and international relations differs from one ruling party to another. Any person with his or her basic knowledge and observation about the very dangerous white nationalist movement which has been and is being clearly promoted by a person who has neither the knowledge nor the willingness to listen to his own advisors and do what is right cannot accept your very generalized comparison between the Democratic party and the Republican party.
  The Republican Party is badly hijacked by the very dangerous white nationalists and frankly it has become the party of Trump. This guy is extremely narcissist, racist, ignorant, addicted liar. He speaks the language that should not be okay even to a very street person or kid. There is no doubt that if he stays in power, he would firmly stand with Egypt including any financial and material support to jeopardize the right and fair negotiation. Some compatriots may say I am dead wrong when I say that even the negotiation being facilitated by African Union has very little if not zero positive result if this guy stays in power .
  This is not to mean that democrats will not continue the protection and promotion and advancement of the basic principle and objective of national interest. But, there is no doubt that they would not go crazy and dangerous like what this guy has been doing and want to do it without any sense of what is wrong and right as far peace and security of that part of Africa is concerned.
  2) It is so stupid and sad for us to continue what those foreign powers have done and continued to do negative things to our2) It is so stupid and sad for us to continue what those foreign powers have done and continued to do negative things to our country whereas we have totally failed and continued failing to do our own home work on the question of how to challenge the very deadly hypocritical and cynical ethnocentric ruing elites of EPRDF now renamed themselves as Prosperity. Like or not, as the very national interest protection and promotion critically dependent on the very internal or domestic political, socio-economic, defense, security , psychological make up, moral and spiritual strength; talking about the danger that may come from this or that external force is painfully clumsy if not stupidly.
  That is why it is absolutely true to say that if we are serious enough about the very heartbreaking situation in our country, we desperately need to deal with those deadly ethnocentric politicians in power with our coordinated and maximum effort while we stay vigilant and prepared to fight back those foreign powers who are trying to exploit the internal situation we are facing. In other words, our challenge and struggle is two-fold!!! It is only and only when we are willing and able to face this very tough situation and do what is right whatever it takes. The rest of it will follow accordingly!! It is this only and only this patriotic and heroic way of doing things that could force those foreign powers to recognize and accept that we are the people who have our own national interest and pride and desperately need to be part of world politics accordingly!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.