ብሶት “በቃ” ማለት ሰሚ እና ባለቤት በሚኖሩበት  !! – ማላጂ

ጥቅምት ፲፮ ቀን ፪ ሽ ፲፫ .ዓ.ም.  ከምሽቱ  አንድ ሠዓት አካባቢ በአንድ የዉጭ መገናኛ ብዙሃን  የአብን የህዝብ ግኝኙነት ኃላፊ እና የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጣሂር  ወቅታዊ እና ህዝባዊ ችግሮችን ለመንግስት ለማሰማት ህዝባዊ ጥሪ ማድረጋቸዉን እና ይህም “በቃ” በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ብሶት ማስተጋባት የያዘ ሠላማዊ ድምፅ የማሰማት መርሃ ግብር እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

አቶ ጣሂር መሃመድ፦ የአብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ
አቶ ጣሂር መሃመድ፦ የአብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ!

ይህን ሰጣ ገባ መስማት ብዙዎቻችንን እንደ ሠዉ አሳስቦን ነበር ዳሩ በነጋታ መሰረዙ ሺሸማ ደግሞ ሃሳባችንን ቀለለ፡፡

በአገራችን ህዝብ ትክክል ነዉ ያዉቃል የሚባለዉ ዞትር በሞግዚትነት  ህዝብን ስማ ልናገር እንዴት እና አስከመቸ እንደሚቀጥል ስናስብም ሌላ ሸክም ይሆንብናል ፡ ፡

ወደ ጉዳዩ ስገባ  የክልሉ  የብአዴን  ህዝብ ግንኙነት (ኮሙኒኬሽን) ኃላፊ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቷ እና ክልሉ ባለዉ አጠቃላይ ሁለንተናዊ ሠዉ ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ ምክነያት  በስመ ህዝባዊ እና ሠላማዊ ብሶተ ድምፅ ሽፋን  የቅርብ  እና ሩቅ ሰርጎ ገቦች መንገድ መክፈት እንዲሁም በሌላዉ የአገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩት የአካባቢ ተወላጅ ላይ ጥቃት ይደርሳል በሚል መልስ አይሉት  ማድበስበስ ከአንደበታቸዉ ሰምተናል፡፡

እዚህ ላይ የፖለቲካ ድርጅታቸዉ እና አመራር ዕዉቅና እና ይሁንታ ይኑረዉ አይኑረዉ ግን አላብራሩም ፡፡

የሆነዉ ሆኖ ሞት እና ስደት ይብቃ ማለት ተጨማሪ ችግር ያስከትላል ሲሉ በዚህች አገር ዜጎች ተፈጥሯዊ እና ሠባዊ መብታቸዉ በማን አለብኝነት ራሳቸዉ በገዛ አገራቸዉ ወዝአቸዉን አንጠፍጥፈዉ በመስራት ከሚያገኙት የዕለት ገቢ ቀንሰዉ በግብር እና መሰል ስም ደምዎዝ የሚከፍሉት እነርሱን ከቢጤ ግብር አበር ጋር ሲያሳድድ እየተመለከቱ ሞት ይብቃ ማለት እንዴት እና በማን ሞት ያስከትላል ፡፡

የረጅም ዓመታት ችግሮችን ትተን የትናቱን የቤንቺ ማጅ እና የመተከል ዕልቂት ዕኮ የሚቀነባበረዉ ፣የሆነዉ በአመራር እና አመራሩ በፈጠረዉ ኢ-ህጋዊ አደረጃጀት ነዉ የሚለን ዕኮ መንግስት ነዉ ፡፡

ዕኮ በህዝብ ስም እየኖረ የህዝብ እና አገርን አንድነት ለማዳከም የሚሰሩትን ከህዝብ እና አገር ችግር በላይ የነርሱን ምግባር እና ተግባር ማለባበስ ካልሆነ በቀር ቀድሞም ሆነ አሁን የዜጎችን አካላዊ እና ዕዕምሯዊ የማይገሰስ ጥበቃ ማድረግ የመንግስት መሆኑን እየታወቀ ህዝብ እሻ የሚል መጨረሻ የት ሊያደርስ እንደሚችል እንኳን ማገናዘብ ተስኖናል፡፡

እንዲያዉ ለመሆኑ “ብአዲን ” ላለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት ኢትዮጵያዉያን በአገራቸዉ ፤በቅያቸዉ እንደ ባዕዳ እና  እንግዳ  ሆነዉ መጣተኛ በመባል የበይ ተመልካች ፣ተሳዳጅ፣ ሟች፣ ተንገላች የመከራ ገፈት ቀማሽ ሲሆን በንግግር  የኢትዮጵያ ህዝብ ሠባዊ እና ህጋዊ  መብት ይከበር በማለት ወይስ ባለማለት ያለፈዉ ሳይበቃ ዛሬም ሞት እና ዕንግልት በቃ አይባልም ለማለት የሚያስችል  ፡፡

ከዚህ በተቃራኒ ኢትዮጵያዊነት መሰደቢያ እና አንገት ማስደፊያ ሆኖ ለመኖሩ ትናንትን ወደ ኋላ ሳናይ ዛሬም እየተደጋገመ ኢትዮጵያዊነት ዛሬም እንዳለፉት ዘመናት ዕርግማን አስከሚመስል እየኖርነዉ መሆኑን ሠዉ የሆነ ሁሉ የሚገነዘበዉ ጠጣር እዉነት ነዉ ፡፡

የብአዴን ቃል አቀባይ ያለዉን እና የነበረዉን የዜጎች ሰቆቃ በንግግር ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነዉ ማለታቸዉ ይህ በአንድ አገር ህዝቦች ላይ ያለዉ አድሎዋዊ እና ኢፍትሃዊ የመልካም አስተዳደር ዕጦት መኖሩን ማመናቸዉ የሚያስመሰግን ቢሆንም ከሃያ ሠባት አመታት በላይ  ለሆነዉ የዜጎች ሞት ፣ፍልሰት እና  ስደት/ መፈናቀል ዛሬ የተጀመረ እንዳልሆነ እናደማያጡት መጠራጠር አንችልም  ፡፡

ዞትር በዚህች አገር የምንሰማዉ እና የተለመደዉ ከህዝብ እና አገር ፊት ሳይሆን ከኋላ ሆኖ ስለ ህዝብ እና ዜጎች መብት ሆነ ስለ አገር መናገር ፤መነጋገር ጅብ ከሄደ ዉሻ ጮኸ እንዲሉ ካልሆነ በቀር ጎምርቶ እና አፍርቶ የሚታይ የተግባር ንግግር ታይቶም ፤ ተሰምቶም አይታወቅም ፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ያልተባለ ንግግር እና ስምነት የለም ነገር ግን የአገር እና ህዝብ ጥቅም፣ የህግ መከበር ከግለሰብ እና ቡድን ስር በመዉደቃቸዉ እና ተጠያቂነት ባለመኖሩ ላይስማሙ የሚስማሙ የተናገሩት ከአንደበታቸዉ እንደወጣ፣ የፊርማ ቀለም ሳይደርቅ እና እግራቸዉ ከቆሙበት ሳይነቃነቅ በድርጊት መደጋገም እንደገና ነግግር፣ አብሮ መስራት …….መግባባት ይባላል ፡፡ ይህ ሁሉ በአገር እና ህዝብ መከራ እና ስቃይ በሚከፈል የህይወት እና የአካል ጉዳት ብሎም የሀብት ዉድመት ነዉ ፡፡

እናም ለዚህ ነዉ ንግግር…….ንግግር……. ያለ ተጨባጭ እዉነት ከንቱ ድካም እና አልቦ ተግባር መሆኑን የረጅም ዓመታት ልማድ  በመሆኑ እንደ ሰባዊ ፍጡር ሀቁን መግለፅ  ግድ የሚለን፡፡

ይህ የመፈናቀል ስደት ፣ሞት እና ኢሰባዊ ዕንግልት በዜጎች ላይ ሲደርስ የአሁኑ የመጀመሪዉ አለመሆኑን እየታወቀ በንግግር ይፈታል እያሉ ጊዜ ማጥፋት ተአማኒነቱ ከመሰረቱ ሲታይ እንዲሁ ጉም የመዝገን የህልም ሩጫ ነዉ ፡፡

የዜጎችን  የዓመታት ተከታታይ ስደት ፣ዕንግልት እና ሞት ከማህበረሰባዊ መመዘኛ ወይም እንደ ዘመናችን ብሄር ጋር እያየያዙ  ከማለባበስ እና ከማደባበስ ሶስቱን ዐዕማድ ይህም አገረ-ኢትዮጵያ፣ ህዝበ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ያለዉን ድብቅብቅ በግልፅ እና በማሻማ አኳኋን መመልከት እና መፍታት ለሁሉም የሚበጅ ይሆናል፡፡

ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ አበዉ ዛሬም ኢትዮጵያዊነት ዉርደት ፣ድህነት እና ሞት የሚሸመትበት የጥቃት ምልክት ከሆነ መቆየቱን  ኢትዮጵያዊ እና ሠባዊነት ለሚሰማዉ ፍጡር ሁሉ የሚረሳ አይሆንም ፡፡

የሆነዉ ሆኖ  ሁለቱም አካላት አብንም ሆነ ብአዴን ያልተገነዘቡት ዕዉነታ ግን ለአገር እና ወገን ለሚጠየቅ የአደባባይ ብሶት ማስተጋባት ሠላማዊ ጥያቄ  ማቅረብ በኢትዮጵያ ልሳነ ምድር መግለፅ አይደለም ማሰብ በማይቻልባት አገር ይህን ያህል መድከማቸዉ ከየዋህነት ዉጭ ሌላ ማለት ይከብዳል ፡፡

በእኛ አገር መናገር ለባለጊዜ(ባለስልጣን) እንጅ ባላገር እና ዜጋ እንደማይፈቀድ ከህግ እና ደንብ አኳያ ሳይሆን ባስፈለገ ጊዜ ሁላ በማቀብ እና መገደብ ያልተጻፈ ግን የተለመደ አስገዳጅ ተለምዶ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም ፡፡

ህዝባዊ ጥሪዉ የመከራ ጊዜ ይብቃ ማለት እና ለዚህም መንግስት የፍላጎት ማነስ ካልሆነ  አቅም አለዉ ብለዋል የአብን ቃል አቀባይ ይሁንና ፍላጎት ኃይል ነዉ ይህ ኃይል ከሌለ የአቅም ጉዳይ አጠያያቂ መሆኑን መገመት ይቻላል፡፡

ሞት እና ዕልቂት ይቁም ማለት እና ይህን ማስተጋባት አይቻልም ብሎ ዱላ እና ዘገር መምዘዝ ዕኮ የፍላጎት  ዕጥረት ስለመኖሩ ማሳያ ነዉ ፡፡ የፍላጎት ዕጥረት የአቅም ዉሱንነት መኖሩን  ጠቋሚ ምልክት ነዉ ፡፡

ይህም በምሳሌ ፡ የምግብ ፍላጎት መቀነስ የአካል ድቀት እና አቅም ማጣት ሊያስከትል የሚችል መሆኑን ሁሉም ሠባዊ እና ህይወት ያለዉ ፍጡር የሚገነዘበዉ ሀቅ ነዉ ፡፡

ፍላጎት ካለ ዞትር አቅም ይገነባል ፤ ይኖራል ፡፡ የመመገብ ሆነ በጎ ነገር የማድረግ ፍላጎት በሌለበት አቅም እንዲኖር መጠበቅ በጨለማ እንደማፍጠጥ ነዉ ፡፡

የብአዴን ህ/ግ/ ኃላፊ  የአብን ህዝባዊ ጥሪ ህጋዊ መሰረት የለዉም ሲሉ ሞት እና ስደት የሚፈራረቁበት የኢትዮጵያ ህዝብ

ሁሉን አሜን ይበል ሲሉ በሌላ አገላለፅ የህዝባዊ ብሶት አስተጋቦት ትክክለኛ እና ወቅታዊ መሆኑን እና ይህም በክልልም  ሆነ በማዕከል ደረጃ የሚታወቅ ግን ለመፍታት የፍላጎት እና ቁርጠኝነት ችግር መኖሩን የሚያሳይ ነዉ ፡፡

ይህ የዜጎች ሠባዊ እና ተፈጥሯዊ በህይዎት የመኖር መብት ጥሰት ጥያቄ ተገቢ እና ወቅታዊ ቢሆንም ሰሚ ያጣ ብሶት ዛሬም እንትናንቱ የቁራ ጩኸት ስለመሆኑ የሚያሳይ ነዉ እና ህዝባዊ ብሶት ሰሚ በሌለበት ላም ባልዋለበት ነዉ ፡፡

ስለዚህ የህዝባዊ ጥሪዉ ቀሪ መሆን ወይም መሰረዝ ተገቢ እና ድሮም እንዳይሆን ስለሆነ እንኳን ተሰረዘ ፡፡ለህዝብ እና አገር የሚበጀዉ በጋራ ችግር በጋራ ትስስር እና ህብር ወደፊት መጓዝ እንጅ ላአላስፈላጊ እና እርባነ ቢስ ድካም የሚደረግ መስዋዕትነት መቆም አለበት ፡፡

አንድ የአበዉ ብሂል ማሳረጊያ ልጨምር “ዳኛ ሲኖር ተናገር ፤ ወንዝ ሲጎድል ተሸገር”፡፡

 

 

እናት አገር ምንጊዜም ትኑር !!!

3 Comments

 1. አቶ ጣሂር ልብ የሚነካ ነዉ እናመሰግናለን እነዛን ሆዳሞች ብአዴን ከማለት በድን ቢሏቸዉ ይቀል ነበር ለዚህ ለቁሳዊ ኑሮ ብለዉ እራሳቸዉን አዋርደዉ ቤተሰባቸዉን የሚያዋርዱ አደባባይ መዉጣት የማይችሉ ዉስጣቸዉ ባዶ የሆነ የመጣዉ ሁሉ የሚጭናቸዉ ደካሞች ናቸዉ። ዉጭ ሁነዉ የድሮ ጌታቸዉን በረከት ስምኦንን ስሙን ሲሰሙ ይደነብራሉ። ቀደም ሲል አብዛኞቹ የመምህራን ማሰልጠኛ ድጎማ አለፍ ሲል ደግሞ ከትግሬ ነጻ አዉጭ ድርጅት ስር ሁነዉ ኢትዮጵያን የወጉ መላ ቅጣቸዉ የጠፋ ዜጎች ናቸዉ። እነዚህ ደካማ አጋሰሶች ካልተወገዱ የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ መከራ መቀጠሉ አይቀርም።ኢትዮጵያም ሆነ አማራ የጊዜ ጉዳይ ነዉ እንጂ ነጻ መዉጣታቸዉ አይቀርም ይበርቱ እናመሰግናለን።

  • ስመረ
   እስቲ ይቺን ያልካትን አስረዳን፡፡
   1። “እነዚህ ደካማ አጋሰሶች ካልተወገዱ የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ መከራ መቀጠሉ አይቀርም።ኢትዮጵያም ሆነ አማራ የጊዜ ጉዳይ ነዉ እንጂ ነጻ መዉጣታቸዉ አይቀርም ይበርቱ እናመሰግናለን።”
   እንደው በናትህ ይህ [ከምርጫ ውጭ] እንዴት ተፈጻሚ እንደሚሆን እና መሬት ሲዎርድ ምን ማለት እንደሆነ አስረዳ?

   2፡ “……ከትግሬ ነጻ አዉጭ ድርጅት ስር ሁነዉ ኢትዮጵያን የወጉ…..”
   ልከ! ድሮ እነሱ ወጉ፤ አሁን ደግሞ እነሱ ቦታ ሲቀይሩ ፤ አንተም ቦታ ቀየርክና የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆንክ (በርግጥ ፈልገህ ሳይሆን የአቢይ ጥላቻ አውሮህ ሊሆን ይችላል!)

 2. Good writing thank you. It seems like the killil politics supporters including beden, and the old ehadeg the current poverty(i.e so called biltsegena) are scared to death of ABEN. All that is needed to break them is a little push by ABEN. Kudos to ABEN for being the voice of the murdered, the displaced, the oppressed Amhara (ie Ethiopians). We can see there is hope for Ethiopians through you. We are proud to know Ethiopianness is not dead inside Ethiopia. Keep up the good work. There is one option for Amhara ie zEthiopian is fight now or they will slowly kill us all.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.