እምቢ በል አማራ! – በላይነህ አባተ

arbegnaእንደ አርበኛ አያትህ እምቢ በል አማራ፣
ለጂላንፎች አትሁን ቁማር መጫወቻ!

እንደ በጎች አርደው እንደ አውሬ ዘንችረው፣
ለበሉት ወገንህ አለሁ እንዳትለው፣
ድምጥህንም ዘጉት ጉረሮህን አንቀው፡፡

ተእነሱ ተባብረው ምሁር ነን የሚሉት፣
ወንጀል ሊሸፍኑ ጀመሩ ዓባይ ስብከት፣
ደምህ ግምጃ ሆኖ ኢትዮጵያን ሲያለብሳት፡፡

ጨካኝ ተማርን ባዮች ለነፍስ የማያዝኑ፣
የአማራን ዘር ፍጅት ጀሮ ዳባ እያሉ፣
ግድብ ትራንፕ ብለው ያረጠርጣሉ፡፡

እምቢ በል አማራ እያዘናጉህ ነው፣
ደምህን ረግጠው ውሀ ሊቀዱ ነው፡፡

አለዚያማ ለዓባይ ተአንተ ቀርበውት ነው፣
ባሳረዱህ ቁጥር ግድብ ስብከታቸው?

በመላ አገሪቱ አጥንትህን ቆርጥመው፣
ተዓባይ ውሀ ቀድተው ሊያወራርዱት ነው፣
ዘራፍ በል አማራ ጨፍጫፊህ አውሬ ነው፡፡

ለዓመታት ለወራት በዓይንህ እንዳየኸው፣
የኢትዮጵያ ሱሴ እቅድና አላማው፣
አንተን አደንዝዞ ደምህን መምጠጥ ነው፡፡

ስንሞት ኢትዮጵያ እያሉ የዋሹህ፣
በስብከት መጫኛ ጠልፈው እየጣሉህ፣
በካራ እያረዱ ቀርጥፈው ሊበሉህ፡፡

ድፍን አማራ ሆይ ልቡናህን አንቃው፣
እንደ ቅድመ አያትህ ቆቅን ሁንባቸው፣
ምላስ መስማት ትተህ ልባቸውን እየው፡፡

እናት ኢትዮጵያን እንጀራቸው አርገው፣
አንተን ልጇን ደሞ የዶሮ ወጥ ሰርተው፣
እንደ ጆፌ አሞራ ጥርግ አርገው በልተው፣
እርሷንም አንተንም ታሪክ ሊያደርጉ ነው፡፡

ለግማሽ ምእተ ዓመት ሲያድሙ የኖሩ፣
አማራን ቆራርጠው ቅቅል እየሰሩ፣
ኢትዮጵያን ቀዳደው እየፈተፈቱ፣
ስልቅጥ አርገው በልተው ተካርታ ሊያጠፉ፡፡

ልክ እንደ አያቶችህ ጎራው በል አማራ፣
እንደ ቅድመ አያትህ ሞረሽ ተጠራራ፣
ተኢትዮጵያ አውሮጳ ተአውሮጳ አሜሪካ፣
ተሜልቦርን ኤስያ ተኤስያ አፍሪካ፣
እንደ አንበሳ አግስተህ እምቢ በል አማራ!

በላይነህ አባተ ([email protected])
ጥቅምት ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.ም.

6 Comments

 1. ታዲያ ሲከለከሉ ለምን ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለኦቦ ሽመልስ አብዲስ እና ለኮ/ል አብይ አህመድ ጥያቂያቸውን አያስገቡም፡፡ ምንአልባት ችግሩ ደብዳቢያቸውን ለጥበቃ ክፍል ሃላፊው ለኮንስታብል ተመስገን ጥሩነህ ማቅረባችው ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛውም ያበሳጫል፡፡

 2. ዘሃበሻ
  ፎቶው ደስ ይላል፡፡ በአንድ ወቅት አዲሳባ ላይ የተነሳ ይመስላል፡፡ እንደዛ ከሆነ ሰዎቹ ሽዋዎች ናችው ማለት ነው፤ ሽዋ ደግሞ በፍጹም ከአንድ ጎሳ ጋር አይያያዝም፤ ስለዚህ ፎቶው ለዚህ አማተር ግጥም በፍጹም አይሆንም፤ ለጥቁር ሱሪና ጫማ ቢጫ ካልሲ እንደማድረግ ነው፡፡

  • ትክክል ብለሀል ፎቶው የሰላሌ ኦሮሞ አርበኞች ሲዘምቱ ነው “History of the African warriors by Herman Cohen ” መጽሀፍ እንደዘገበው።

 3. ከድር ሰተቴ ያንተ አያት ለጣልያን እንቁላል ሲያቀርብ አማራ ባየኸዉ መንፈስ ነዉ አገር ጠብቆ ዛሬ አንተ አንተን እንድትሆን ያደረገዉ። አማራ ጠብቆ ባያቆይህ ይሄን ጊዜ እራስህን ወይ ሶማሌ ወይ ኬንያ ወይ ሱዳን አለፍ ሲልም ደግሞ አሳልፈዉ ሺጠዉህ እራስህን አንዱ አገር ታገኘዉ ነበር። የምንሊክን ነብስ ይማር ከሰዉ ደረጃ ሳትወርድ አሁንም አለህ ተምረህ መሳደብም ችለሃል። በርታ የምትናፍቀዉ በነጭ መገዛት እሩቅ አይደለም እንደ አያትህ እንቁላል ታቀርባለህ ለጥልያን ወይም ለአረብ።

 4. ያምሃል ልበል? ወይስ የአማርኛ ችግር አለብህ? ከፈለክም ሃቁን ልንገርሃ!
  እንደው ወገኛ ቢጤ ነህ እንጂ ይሄኔ በፈረንጅ ብር ልጆችህን የፈረንጅ እንቁላል እያበላህ ነው፡ ፈረንጅ የምትሳደበው፤
  በሸዋ እና በአማራ መካከል ያለውን ልዩነት እንድታጠና እመክርሃለሁ; ሁለቱ አንድ አይደሉም፤ ሸዋ ቅልቅል (ወልመካ) ነው፡ የቅድሞውን ሸዋ ከፍለ ሃገር አርበኞች ስም ዝርዝር እና የጎጃም፤ ጎንደር ወሎ አርበኞች ስም ዝርዝር አውጣና አወዳድር፡፡ እርግጠኛ ነኝ ይደብርሃል፡፡
  “ጓዶች፤ ባናወራው ይሻላል፡ ስንት ጉድ አለ” ብሎ ነበር መንግስቱ ኃ/ማርያም፡፡ (ስለ ጣሊያን ጊዜ ባንዳዎች ማለቱ ነው!)

 5. በላይነህ አባተ፣ አቻምየለህ ታምሩ፣ ሰርፀ ደስታ፣ ወዘተ ሥራ ፈትቶችና የጥላቻ ቋት ናቸው። አማራን አይወክሉም። ኢትዮጵያን አይወክሉም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.