ሰሞኑን በጉራፈርዳና እንደዚሁም መተከል ወዘተ በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ  በማውገዝ የተሰጠ መግለጫ

ከኦሞ የኢትዬጵያ አንድነትና ፍትህ ማዕከል
OMO Ethiopia Unity and Justice Center

October 27th 2020
ሰሜን አሜሪካ

OMOእኛ ኦሞ ኢትዮጵያ አንድነትና ፍትህ ማዕከል አባላት በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተፈጸሙትን ዘር ተኮር ጥቃቶች በጥሞና ተከታትለናል::

ላለፉት ተመሳሳይ ድርጊቶች በጥፋተኞች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው እየተባለ ባለበት በአሁኑ ወቅት በመተከልና ጉራ ፈርዳ እጅግ ዘግናኝ የሆኑ ዘር ተኮር ጥቃቶች ያውም በተደጋጋሚ መፈጸማቸውን ስንረዳ  ልባችን ተሰብሯል:: ሐዘናችን ከባድ ሆኗል::

እስከዛሬ  እንደዚህ ያለ ጉዳት በሕብረተሰቡ ላይ በሚያደርሱት ላይ ሁኔታው እንዲገታ የሚያደርግ ተከታታይና የማያዳግም ጠበቅ ያለ ሕጋዊ እርምጃ  ሲወሰድ አይታይም !

ሰዎች ታሰሩ ሲባል ይሰማል: ግን ተፈረደባቸው ሲባል ብዙም አይሰማም::

መንግሥት ቀዳሚ ተግባሩና ሚናው የሕዝብን ሰላምና ደሕንነት በአራቱ የአገሪቱ ማዕዘናት የመጠበቅና የማስጠበቅ ኃላፊነት ከመንግሥታዊ ተግባሩ ዋነኛው ማድረግ ምንግዜም ይጠበቅበታል ፤

ስለዚህ የሚመለከታቸው ሰላምንና ደሕንነትን የማስጠበቅ መንግሥታዊ ተቋማት ሁሉ በተናበበ መልኩ ይህ መቋጫ ያጣው የዜጎች እልቂት እንዲገታ የማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት ፤ ስለሆነም መጪውን ተመሳሳይ አደጋ  ለማስወገድ ግልጽ የሆነ መርህና ስልት እንዲኖረው የግድ ይላል::  ያለዚያ ጠባሳው መጪውንም ትውልድ ከቶውንም አይለቅም::

በዚህ ረገድ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ሞት የኦሞ ኢትዬጵያ አንድነትና ፍትህ ማዕከል ከባላት ልባዊ ሃዘናችንን ስንገልፅ እምላክ ሟቾችን በገነት ያኑራቸው: ፣  ለቤተሰቦቻቸው ዘመድ አዝማዶቻቸው ሁሉ መጽናናት ይስጥልን እንላለን።

በዚህም ሰላምና መረጋጋት በአገራችን ይሰፍን ዘንድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ የመጫወት ኃላፊነት እንዳለው ስናሳስብ በሕዝባችን መካከል ማንነትን መሠረት ሳያደርግ አብሮን ለብዙ ሺህ ዓመታት በኢትዬጵያዊነት ብቻ የዘለቀው የትብብር የመደጋገፍና የመተሳሰብ መንፈስ እንዲኖርና እንዲቀጥል ድርጅታችን በበኩሉ በአካባቢያችን የጀመርነውን ሰላምና ትስስርን የማስፈን ዓላማና ተግባር አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማረጋገጥ እንወዳለን።

OMO Ethiopia Unity and Justice Center.
4017 Harvest Run Clarkston, GA-30021 USA,
Phone-1+571-470-2353, Email [email protected] OR [email protected],
Website -OMOEthiopia.org

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.