ትብብር እና ቅንጅት የሚፈጠርበት ጊዜ አሁን ነው – ዶ/ር በቃሉ  አጥናፉ  ታዬ

Abiy Ahmed parliamentጠቅላዩ  በቤኒሻንጉል ጉምዝ የሚካሄደውን ጭፍጨፋ እና ግድያ  እንደሚቀጥል ተናግረዋል (ጠ/ሚ/ ለፓርላማ ከተናገሩት የተወሰደ)፡፡  ይህ ንግግር ለቤኒሻንጉል ጉምዝ ብቻ የተነገረ ሳይሆን በሌሎችም ክልሎች አማራን የማጥቃት ስልት እንደሚቀጥል በስውር ማስታወቃቸው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሀገርን የሚመራ መሪ የህዝቡን ጥቃት ይታደጋል እንጅ ጥቃቱ ይቀጥላል ብሎ ሲናገሩ መስማት ይህ ንግግር መሪውን የመጀመሪያ ያደርጋቸዋል፡፡ መንግስት የተባለ አካል በተበየነበት ሀገር፤ መንግስት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ግዴታው መሆኑ እየታወቀ እንዲህ መነገሩ እጅግ ያሳዝናል፡፡ እጅግም ያሳፍራል፡፡

የመከላከያ ሰራዊታችን ብቃት እንኳን ለዜጎቹ ለጉረቤት ሀገራትም እንደሚበቃ በተግባር የተፈተነ ጉዳይ ነው፡፡ እውነታው ይህ ሁኖ እያለ የዜጎች ግድያና ጭፍጨፋ እንደሚቀጥል መነገሩ ጉዳዩ ግድያውን ለማስቆም የአቅም ማጣት ሳይሆን ፍላጎቱ እንደሌለ ማሳያ ነው፡፡ አማራ በራሱ ሀገር ይገደል፣ ይገለል እና ይሸማቀቅ ዘንድ  ህገ – መንግስታዊ ድንጋጌ ተጥሎበታል፡፡

ጎሳቸውን ተጠቅመው ወደ ስልጣን ለመውጣት የሚፈልጉ ብሄርተኞች ህገ – መንግስቱን እና የጎሳ ፖለቲካን ሙጥኝ ያሉበት ምክንያት ይኸው ነው፡፡ ብሄርተኞች ወደ ስልጣን ለመውጣት ይመቻቸው ዘንድ ህገ – መንግስቱን እና የጎሳ ፖለቲካውን እንዳይቀየር ሲሟገቱ እንሰማለን፤ ዳሩ ግን ህገ – መንግስቱ እና የጎሳ ፖለቲካው የአንድነት ፀር ከመሆኑም ባሻገር በዜጎች መካከል መቃቃርን እና ግጭትን እንደሚጋብዝ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡ ሁኖም ግን ሰሚ የለም፡፡ ምክንያቱም ይህ ብሄር – ተኮር ጥቃት ስልታዊ በሆነ መንገድ እንዲቀጥል ይፈለጋል፡፡ የሽመልስ አብዲሳ ንግግር ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ዘር – ተኮር ግድያዎች ጠቅላዩ ምንም አይነት ማፅናኛ አለመስጠታቸው ሌላው ማረጋገጫ ነው፡፡

ስለዚህ መላው አማራ እና ግፍን የሚፀየፉ ውድ ኢትዮጲያውያን በሙሉ በአንድ ድምፅ በጋራ በመቆም ይህንን ዘረኛ ስርዓት ልንታገለው ይገባል፡፡ በጥቃቅን ጉዳዬች መለያየትን አቁመን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተባብረን ይህንን የብሄርተኛ ስርዓት ልናስቆመው ግድ ይላል፡፡ ከብሄር ይልቅ በዜግነት እና በሀገር አንድነት ላይ የሚሰሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት፤ ህብርት፣ ትብብር እና ቅንጅት የምንፈጥርበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ጉዳዩ ለፖለቲካ ስልጣን የምንራኮትበት ሳይሆን ሀገርን እና ህዝብን ለመታደግ ኃላፊነታችንን የምንወጣበት ጊዜ ነው፡፡ እኛ ህብረት ፈጥረን ግድያና ግፍን ማስቆም እስካልቻልን ድረስ ሰቆቃው ይቀጥላል፡፡

6 Comments

 1. አየህ ዶ/ር፤ ግድያውን የሚፈጽሙት ቡድኖች የፈለጉትም አማራ ሁሉ ልክ እንዳንተ እንዲያስብ ነው፡፡ ከዚያም አቢይን ከዚህም ከዚያም ማዋከብ፤ የሚገርመው አንተ ዶ/ር ብትሆንም የችግሩ መጠን የአማራ አርሶ የገባውን ያህል እንኳ አልገባህም፤፤

 2. Kedir:

  Assume the pregnant woman killed in a savage way in Shashemene was your wife? Assume the babies massacred in Metekel were yours. Assume the people burried in a mass grave Guraferda are your family members. What would you have felt? Do you think these people hunted in all corners of the country feel that there is a country called Ethiopia or a government? I just leave the answer to you.
  Did non-Amhara Ethiopians, political parties or even the prime minister condemn these massacres? The answer, with very few exceptions, is a BIG NO.

  Where would these situations lead to? We will see.

  • መሰረት
   የግድ ይኔ ዘመድ መሆን የለባችውም፡፡ እንክዋን በገዛ ወገየለባኔ ይቅርና በማንም ላይስ ቢሆን እንዲህ አይነት ዘግናኝ ድርጊት ሲፈጸም ማየት እንደሀገርም እኮ እንደወደቅን ንው የሚገባኝ፤ ግን ለምን እንዲህ ሆነ? ለምን አላማ ተፈልጎ ነው? ብሎ መተንተንም ይጠይቃል፡ “አላወገዙም” ማለት እኮ “ደግፈዋል” ማለት አይደለም፤ ህገር በስሜት አይመራም፤ አንተ እኮ ችግርህ የሚመስለኝ “ሁሉን ነገር የሚሰራው መንግስት ነው ብለህ ስለምታስብ” ነው፡፡ እኔ የማስበው “ገዳይም እኛ ሟችም እኛ” ብዬ ነው፡ እንጂ “ገዳይ ሁሉም፤ ሟች አማራ” ብዬ አይደለም፡፡
   ዋናው ሥራ “ገዳይ” ዉስጥ ያሉትን “እኛዎች” ነጥሎ ማውጣትና ለፍርድ ማቅረብ ነው፡ እየተደረገም ንው፡

  • ትክክል!
   ታዲያ እኔ ምን አስተዋጾ አድርጌአለሁ? ምንስ ይጥበቅብኛል? ብሎ እያንዳንዱ ሰው ራሱን መፈተሽ አለበት፡

 3. የፌደራል መከላከያ በክልሎች ልዩ ሀይል በተለይ በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ተዋርዶ በሚያሳዝን ሁኔታ ስለተመታ ነው ጠቅላዩ ይህንን የተናገሩት በፓርላማ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.