በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የውጪ ጥቃት መሆኑ ይታወቅ – ያሬድ ኃይለማርያም +

ይቺ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የውጪ ጥቃት ሲሰነዘር ወይም የተሰነዘረ ሲመስለን ከጫፍ ጫፍ፣ ከልጅ አዋቂ ሳንል የምናሳያትን ቁጣ እና በአንድ ድምጽ የመገንፈል ስሜታችንን አፈናን፣ ጭቆናን፣ ግፍን፣ ሙስናን፣ ዘረኝነት እና ጎጠኝነትን፣ የውስጥ ፖለቲካ ንቁሪያችንን፣ በሕዝብና በአገር ሃብት ላይ የሚደርሱ ውድመቶችን እና ዝርፊያዎችን፤ እንዲሁም የፍትሕ መጓደለን እና መድልዖን ለመዋጋት አውለናት ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያን ገና በጠዋቱ ፍትሕ የሰፈነባት፣ ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የተገነባባት፣ ድህነትን አሸንፋ ለሌሎችም የምትተርፍ የበለጸገች አገር እናደርጋት ነበር። ውስጡ የተናጋ እና ሰላም ያጣ አገር ሁሌም ለውጪ ደፋሪዎች የተጋለጠ ነው።

ውስጣችንን እናጽዳ፣ ከሸርና የመጠላለፍ ፖለቲካ እንውጣ፣ ጎጠኝነትን እንጠየፍ፣ ኢትዮጵያዊያን በሰውነታቸው ተከብረው እና ተከባብረው የሚኖሩባት አገር እንፍጠር፣ የግፍ ጽዋው ይንጠፍ፣ ለእውነት እና ለፍትሕ አብረን እንቁም። ኢትዮጵያዊያን ለውጭ ጠላት ብቻ ሳይሆን ለዘመናት በተጣቡን ግፍ፣ መድሎ፣ ሙስና፣ አፈና፣ ድህነት እና ሌሎች ክፉ እሳቤዎቻችንም ላይ አብረን በጋራ እንነሳ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.