ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት 1.9 በመቶ መሆኑን ገለጸ፣ የአብይ 6.1 በመቶ ውሸት ነው!!! (ሚሊዮን ዘአማኑኤል)

በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤፍ ኤም) የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በወፍ በረራ At a Glance

file76zkhq83hjr1fme347jo 336433025 1568323598 ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት 1.9 በመቶ መሆኑን ገለጸ፣ የአብይ 6.1 በመቶ ውሸት ነው!!!  (ሚሊዮን ዘአማኑኤል)

 • 2020እኤአ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት(አይኤምኤፍ) የኢትዮጵያ አመታዊ ጥቅል ምርት(ጂዲፒ) እድገት 1.9 በመቶ/ 2020 Projected Real GDP (% Change) : 9
 • 2020እኤአ የሸማቾች የሸቀጥ ዋጋ መናር በመቶ 20.2 በመቶ/ 2020 Projected Consumer Prices (% Change): 2
 • የህዝብ ብዛት 98.131 ሚሊዮን/ Country Population: 131 million
 • አይ ኤፍ ኤም አባል የሆንበት ዲሰምበር 27 ቀን 1945/ Date of Membership: December 27, 1945
 • አንቀፅ አራት/ የሃገር ሪፖርት ጀንዋሪ 28 ቀን 2020/ Article IV/Country ReportJanuary 28, 2020
 • Outstanding Purchases and Loans (SDR): 56 million (September 30, 2020)
 • Special Drawing Rights (SDR): 78 million
 • Quota (SDR): 7 million
 • Number of Arrangements since membership: 7

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ተካሂዷል። በዚሁ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል:: (2)

ምጣኔ ሃብት:- ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ የ6.1 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገቡን ይፋ አድርገዋል። ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይኤም ኤፍ) የኢትዮጵያ አመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) እድገት 1.9 በመቶ እንደሆነና ለሚቀጥለውም አመት ምንም እድገት እንደሌለ ገልፆል፡፡

{1} አመታዊ ጥቅል ምርት (Gross Domestic Product)፡- የኢትዮጵያ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት በቢሊዮን ዶላር GDP  በ2015 (64.6)፣ 2016 (74.3)፣ 2017 (81.8)፣2018 (84.3)፣ 2019 (96) ቢሊዮን ዶላር

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2012 የበጀት ዓመት 3.37 (3.4) ትሪሊየን ብር ጠቅላላ አገራዊ ምርት መመዝገብ መቻሉንም ተናግረዋል። ”ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ አጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) 2.2 (ከሁለት ነጥብ ሁለት) ትሪሊዮን ብር ወደ 3.4 (ሦስት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ማደጉን ኢኮኖሚው መመንደጉንና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ  ድባቅ መተን ለዓለም ዓቀፍ ንግድ የምናስተምረው ትምህርት እንዳለ  ያበስሩን ይሆናል፡፡   የዓለም አቀፍ ንግድ እንቅስቃሴ ግብይይት የሚደረገው በዶላር፣ ፓውንድ፣ ዩሮ፣ በመሆኑ ዓለም ባንክና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) መረጃ በዶላር የሆነው ለዚህ ነው፡፡  በዚህም ስሌት በ2011ዓ/ም 2.2 (ከሁለት ነጥብ ሁለት) ትሪሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወደ ዶላር ስንቀይረው 75.9 ቢሊዮን ዶላር  (አንድ ዶላር በ29) ብር ይሆናል፡፡ በ2012ዓ/ም  3.4 (ሦስት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ወደ ዶላር ስንቀይረው 94.4 ቢሊዮን ዶላር  (አንድ ዶላር በ36 ብር) ሲመነዘር ይሆናል፡፡ በጥቁር ገበያ የብር ምንዛሪ ተመን ከ46 ብር እስከ 50ብር መድረሱን በጥናታችን አረጋግጠናል፡፡ ዶክተር ዐብይ አህመድ  በኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ ቆራጥ አመራር የሃገራችንን ጂዲፒ ትሪሊየን ውስጥ ከተናል ለማለት አስቦ ከሆነ የብር የመግዛት አቅም መሽመድመድና ብር የወረቀት ያህል መርከሱን ያሳየናል እንጂ የኢኮኖሚ እድገት በኮቪድ 19 ዘመን የሚታሰብ አይደለም እንላለን፡፡”

{2} የኢትዮጵያ  የነፍስ ወከፍ ገቢ በመቶ ዶላር/ GDP per capita/ በ2015 (483)፣ 2016 (514)፣ 2017 (548)፣2018 (571)፣ 2019 (602)ዶላር መሆኑ ተገልፆል፡፡ የኢትዮጵያ 2019እኤአ በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የነፍስ ወከፍ ገቢ 602 (ስድስት መቶ ሁለት)  ዶላር (22 ሽህ ሁለት መቶ ብር ) በዓመት! ይህም መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ኢትዮጵያን ማሰለፏን እንደሚያረጋግጥ በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዘመነ አገዛዝ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ አንድ ሽህ ዶላር ወይም (37 ሽህ ብር ) በዓመት ገቢ ያገኛል ያሉት ውሸት ነው፡፡ አጠቃላይ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት፣ለጠቅላላ የህዝብ ቁጥር አካፍለን የእያንዳንዱን ሰው የነፍስ ወከፍ ገቢ እናገኛለን፡፡

 • 602 (ስድስት መቶ) ዶላር በአመት በ12 ወራት ሲካፈል 50 ዶላር ይሆናል ለ 30 ቀን ሲካፈል ደግሞ7 ዶላር በቀን በ8 ሰዓት ሲካፈል 0.21 ሳንቲም በሰዓት በምንም ተዓምር ወደ መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው አገራቶች ተርታ አያስገባም፡፡ የመካከለኛ ገቢ አገሮች የነፍስ ወከፍ ገቢ 10000 (አስር ሽህ ) ዶላር ነው፡፡
 • አንድ ዶላር በ 37 ብር (https://combanketh.et/exchange-rate-detail/) ሲመነዘር 600 ሽህ ዶላር ይሆናል 22200 ብር በአመት በ12 ወራት ሲካፈል 1850 ብር ይሆናል ለ30 ቀን ሲካፈል ደግሞ7 ብር በቀን በ8 ሰዓት ሲካፈል 7ብር 70 ሳንቲም በሰዓት በምንም ተዓምር ወደ መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው አገራቶች ተርታ አያስገባም፡፡ የመካከለኛ ገቢ አገሮች የነፍስ ወከፍ ገቢ 10000 ዶላር መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡)   በእኛ ስንመነዝረው ደግሞ 370000 (ሦስት መቶ ሰባ ሽህ) ብር በዓመት ይሆናል፡፡
 • በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤፍ ኤም) የነፍስ ወከፍ ገቢ 850 (ስምንት መቶ ሃምሳ) ዶላር መሆኑን ገልፆል፡፡

{3} የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከጠቅላላ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ጋር ሲነፃፀር /Ethiopia Government Debt to GDP1991-2019 Data | 2020-2022 Forecast | Historic / Ethiopia recorded a government debt equivalent to 57 percent of the country’s Gross Domestic Product in 2019.

የኢትዮጵያ  ዕዳ ከጠቅላላ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት በመቶኛ/  Debt to GDP/ በ2015 (32)፣ 2016 (35)፣ 2017 (36)፣2018 (60)፣ 2019 (57) በመቶ መሆኑ በመረጃ ተረጋግጦል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከአመታዊ አጠቅላላ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) ጋር በማነፃፀር በየዓመቱ አጠቃላይ ዕዳችንን ከአመታዊ  አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ጋር የምናወዳድርበት የምጣኔ ኃብት ትምህርት ነው፡፡  በኢኮኖሚስቶች ምክረ ሃሳብ መሠረት፣ የአንድ አገር ዕዳ ዝቅተኛ ከሆነ ሃገሪቱ አምርታ በውጭ ንግድ ከምትሸጠው ምርት፣ ሸቀጣሸቀጥና አገልግሎት ከምታገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ እዳዋን ለመክፈል ያስችላታል፡፡ በአንፃሩ የሃገሪቱ ዕዳ ከፍተኛ ከሆነ ምርቶን ሸጣ የምታገኘው ገቢ እዳዋን ለመክፈል አያስችላትም፡፡ ስለዚህ ዕዳ ከጂዲፒ ንፅፅር ከመቶ ከሃምሳ በታች ሲሆን የተሸለ ሲሆን ከሃምሳ በላይ ከሆነ ግን ዕዳ ለመክፈል አስቸጋሪ ይሆናል፡፡   የህወሓት/ኢሀአዴግና ኦዴፓ ብልፅግና  የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከአጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) ጋር በማነፃፀር ከ1991 እስከ 2020እኤአ ዕዳ ከጂዲፒ ንፅፅር እንቃኛለን፡፡ በዚሁ መሠረት በ2010እኤአ 26.8%፣ በ2012እኤአ 27.4%፣ በ2014እኤአ 31.8%፣ በ2016እኤአ 34.9%፣ 2018 እኤአ 60%፣ በ2019እኤአ 57% በመቶ መሆኑን ከሠንጠረዡ ላይ መረዳት ይቻላል፡፡  ዶክተር ዐብይ አህመድ የሃገሪቱን የእዳ ጫና ከአጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) ከ31% በመቶ ወደ 25% በመቶ እንዲቀንስ አድርገናል ብለው ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡  ከታች የምጣዩት የሠንጠረዥ ማስረጃ ምንጩ ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ዶት ኮም/ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተገኘ እንደሆነ ያሳያል፡፡

የጉራፈርዳ አማራዎች ላይ የተፈጸመ የዘርና የኃይማኖት ጭፍጨፋ (ጆኖሳይድ) ተጠያቂዎች ለፍርድ ይቅረቡ!!! ሽፈራው ሽጉጤና ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ሹማምንት ለፍርድ ይቅረቡ!!! ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ መንግሥታዊው ሽብር ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ስለሆነ ወንጀለኞቹ የማይያዙት ከፍተኛ መረጃ ስላላቸው ነው!!!

ምንጭ፡-

{1}   https://www.imf.org/en/Countries/ETH https://www.imf.org/external/datamapper/NGDP_RPCH@WEO/OEMDC/ADVEC/WEOWORLD/ETH

{2}  https://www.bbc.com/amharic/54597783/ዐብይ አሕመድ፡ ጠ/ሚር ዐብይ ከሕውሓት ጋር የተከሰተው አለመግባባት “በሕግ እና ሕግ ብቻ የሚመለስ ይሆናል” አሉ 19 ጥቅምት 2020, 13:30 EAT

{3} Ethiopia Government Debt to GDP/1991-2019 Data | 2020-2022 Forecast | Historic (https://tradingeconomics.com/ethiopia/government-debt-to-gdp/)

3 Comments

 1. Ethiopia needs to rise the price of coffee exported to cope up with the ever growing need for foreign currency.

 2. የባንኮች የሚሰበስቡት ተመላሽ የብድር መጠን እየቀነሰ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ::

 3. የኤክስፖርት ምርቶች ተመን የሚወጣው በአምራቹ አገር በዘፈቀድ ሳይሆን የዓለም የንግድ መስፈርትን ተከትሎ በመሆኑ በቡና ላይ እንዳሻን ዋጋ መጨመር አይቻልም ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.