የአውሮፓ ኅብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ሰበብ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብጽ መካከል ውጥረት ሊባባስ እንደማይገባ አሳሰቡ

safe image 1ኃላፊው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከሰጡት አወዛጋቢ አስተያየት በኋላ እንዳሉት “በታላቁ የኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ላይ ስምምነት የሚደረሰው በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል ነው።”
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሶስቱ አገሮች ሥምምነት አቅርበው እንደነበር በትናንትናው ዕለት ተናግረው ነበር። “ሥምምነት አቅርቤላቸው ነበር። እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ ሥምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም። ያ ትልቅ ስህተት ነው” ብለው ነበር።
45
“አሁን ጊዜው የተግባር እንጂ ውጥረት የሚባባስበት አይደለም” ያሉት የአውሮፓ ኅብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ግን ሶስቱ አገሮች በጀመሩት ድርድር ገፍተው ከሥምምነት የመድረስ ዕድል እንዳላቸው ዛሬ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
“የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ-መንበር የሆነችው ደቡብ አፍሪካ ሁሉንም ወገኖች መፍትሔ እንዲያበጁ ለማደራደር የጀመረችው ጥረት የአውሮፓ ኅብረት ሙሉ ድጋፍ አለው” ያሉት ቦሬል ድርድሩ ቀጥሎ ስኬታማ ፍጻሜ ላይ ይደርሳል የሚል ዕምነት በአውሮፓ ኅብረት ዘንድ እንዳለ ጠቁመዋል።-
DW
Trump i

2 Comments

  1. የኢትዮጵያ አምላክ ፍርዱን ያሳየን በገዛ ወሀችን ውሀ አትጠጡ በጨለማ ኑሩ የሚል የጥጋብ ንግግር ይሄ ሰውዬ ለምርጫም አይደርስም።

  2. አነሰም በዛም ለማኝነት ተዋህዶን ስንራብ ከሚያበሉን ስንጠማ ከሚያጠጡን መንግስታት ጋር እታካራ ማብዛት ተገቢ አይደለም።
    ዝምታ ወርቅ ነው!!
    ሞያ በልብ ነው!!!
    በለፈለፉ…….ይጠፉ!!!

    We Ethiopians at all levels need to practice living upto the famous saying ” If you got nothing nice to say to others then choose not to say anything”.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.