ሦስት የሳምንቱ ጉዳዮች! – ታዬ ደንድአ

ታዬ ደንድአ
ታዬ ደንድአ

አንድም “ተሽጧል” የተባለዉ(በህውሃት ሰወች)  የህዳሴ ግድብ በግብፆች ሊመታ እንደሚችል ትራምፕ ተናግሯል። ባንዳዎች ወዲያዉ ሌላ ለቅሶ ጀምሯል! በሀገራቸዉ ጉዳይ የጀግና ኢትዮጵያዊያን ልክ ደግሞ ይታወቃል! የሚከፈለዉ ተከፍሎ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንደተለመደዉ ይከበራል! በተያዘለት ጊዜ ህዳሴ ተጠናቆ የሀገራችንን ሁሉ-አቀፍ ብልፅግና ያበስራል። ለማሸነፍ ችግርን መጋፈጥ ግድ ይላል!

ሁለትም  ግሪሳ የትዩተር ዘመቻ ከፍቷል። ዘመቻዉ “የኢትዮጵያ ችግር የብሔር ፅንፈኝነት ሳይሆን አምባገነንነት ነዉ” ይላል። ነገር ግን ከግብፅና ከህወሀት ጋር መክረዉ ጀግናዉን አርቲስት ካስገደሉ በኋላ “ነፍጠኛ ገደለዉ” በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ የ167 ዜጎች ህይወት እንዲጠፋና በቢሊዬን የሚገመት የሀገር እና የህዝብ ሀብት  እንዲወድም ማድረጋቸዉን ዓለም ያዉቃል። የንሰሃ አባታቸዉ ህወሀት “ውሸት ቢደጋገም እዉነት ይሆናል” የሚለዉን የግራ ፖለቲካ  መርህ እየነገራቸዉ በከንቱ ያንገላታቿል!
ሦስትም ህወሀት የተለመደዉን መግለጫ አዉጥቷል። መግለጫዉ “የፌዴራል መንግስት 285 ሚሊዬን ብር የሰፍቲኔት በጀት አቋርጦብናል” ይላል። በሌላ መግለጫ “ከመስከረም 25/2013 በኋላ የፌዴራል መንግስት የለም” ማለቱን የዘነጋ ይመስላል። በነገራችን ላይ በ 10 ዓመታት ውስጥ ረሃብን ለማጥፋት በ 1983 ላይ አብዮታዊ  መግለጫ አዉጥቶ የነበረዉ “አብዮታዊዉ፣ ልማታዊዉ፣ ፌዴራላዊዉ፣ እመርታዊዉ፣ ህገ-መንግስታዊዉ እና ዴሞክራሲያዊዉ” ህወሀት ከ 30 ዓመታት በኋላ በምን አፉ ስለሰፍቲኔት ያወራል? ጭንቅላቱ የደረቀ የሌባ ስብስብ ይሉኝታን የት ያዉቃል!
ሠላም ዋሉ!!

2 Comments

 1. ዶክተሩ ለወቅቱ ባላንጣችው ኃይሌ ፊዳ ያላችው ጥላቻ እስካሁን የወጣላችው አይመስልም፡፡ የተበሳጩት ደግሞ እትዬ ታደለች በአንድ ስብሰባ ላይ “ኃይሌ ፊዳ ይቅርታ ስለጠየቀ አደነቅሁት” ስላለች ይመስለኛል፡፡ በህይወት የሌለውን ኃይሌ ፊዳን “እንዲወገዝ አደረኩ” ብለው ዶክተሩ በኩራት ሲነግሩን ትንሽ እንኳ ቅር አላላችውም፡፡ ቢጠሉት እንኳ ቢያንስ “ሙት ወቃሽ አያድርገኝና” ይባላል፡፡

  እንደው ለመሆኑ “ኢህአፓ ተሳክቶለት ስልጣን ይዞ ቢሆን ኖሮ” ብሎ የተመራመረ የለም?

 2. @ታዬ ደንድአ!
  “ባንዳዎች ወዲያዉ ሌላ ለቅሶ ጀምሯል! በሀገራቸዉ ጉዳይ የጀግና ኢትዮጵያዊያን ልክ ደግሞ ይታወቃል! የሚከፈለዉ ተከፍሎ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንደተለመደዉ ይከበራል! በተያዘለት ጊዜ ህዳሴ ተጠናቆ የሀገራችንን ሁሉ-አቀፍ ብልፅግና ያበስራል። ለማሸነፍ ችግርን መጋፈጥ ግድ ይላል!”
  መልካም ብለሀል::
  ኢትዮዽያዊነት እውነተኛና የማይድን ሱስ ነው!!
  በኢትዮዽያዊነትህ ፅና!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.