ትራምፕ ግብፅ የኢትዮጵያን ግድብ ‘ልትፈነዳ’ ትችላለች

Damስለ ዐባይ ወንዝ ግድብ ጉዳይ ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አደገኛ ቅጥፈት የኢትዮጵያ መንግሥት ተገቢውን መልስ እንደሚሰጥና ለውድ ሐገራችን የሚበጅ እርምጃ እንደሚወስድ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚም፤ ከዚህ በታች በተመለከቱት ነጥቦች ላይ ትኩረት በመስጠት ለዘለቄታው የሚጠቅም ሥልት እንዲተገበር በትሕትና አሳስባለሁ፤
1ኛ/ በዐባይ ወንዝ አማካኝነት ወደ ሱዳንና ግብጽ ለሚፈሰው ውሀና ለም አፈር ለኢትዮጵያ ተገቢው ክፍያ እንዲከናወን፤ ይህም የሚታሰበው፤ ለሶቶ ከደቡብ አፍሪካ በየዓመቱ ለምታበረክተው ውሀ $50 ሚሊዮን ያህል ክፍያ የምታገኝ መሆኑን በመልካም ምሳሌነት በማሰብ ነው፤

2ኛ/ ግብጽ በራሷ የውሀ ህብት፤ (ሀ) የመሬት ውስጥ (ground water)፤ (ለ) ከቀይ ባሕርና ከሜዲቴሬኒያን የምታገኘውን ጨዋማ ውህ (desalination)፤ እንዲሁም (ሐ) የቆሸሸውን ውሃ በማጥራት (recycling); እንድትጠቀም ማድረግ፤
3ኛ/ ኢትዮጵያ ባላት መጠነ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት ሁሉ፤ በውሀ ምንጮች (በዐባይ ወንዝ) በሌሎቹም ጭምር እንድትጠቀም፤ የተሟላና ሥልታዊ የሆነ ብሔራዊ የልማት እቅድ ማዘጋጀት፤ መተግበርዓትና ሐገራችንን ከአሰቃቂ ድህነት ማላቀቅ፤ በUNDP Human Development Index ኢትዮጵያ 173ኛ ከመሆን ዝቅተኛ ደረጃ እንድትላቀቅ ማድረግ)፤
4ኛ/ ተከስቶ ከሚገኘው የዘረኛ ሥርዓትና ያልተቋረጠ ግጭት፤ መፈናቀልና ውድመት ለመላቀቅ፤ መሠረታዊው ምክንያት ጎሰኛነትን የሚያጎለብተው አደገኛ ሕገ መንግሥት ስለ ሆነ፤ በሌላ፤ በኢትዮጵያዊነት ላይ ያተኮረ፤ አንድነት፤ ሰላም፤ ጸጥታ፤ ልማት፤ እውነተኛ ዲሞክራሲና የሕግ በላይነት በሚያሰፍን እንዲሁም በሕዝብ ተሳትፎ በሚጸድቅ እንዲተካና የአስተማማኝ ምርጫ ቅድመ፟ ዝግጅት እንዲሆን ማድረግ፡፡
ቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳን፤ ያበርታን፡፡
ኪዳነ አለማየሁ

 

2 Comments

  1. The revolutionary democrats who conceived and implemented the Grand Ethiopian Renaissance Dam
    are now sidelined and blamed for everything that went wrong in Ethiopia. The present Oromo dominated government will not be able to complete the project.

  2. We will make the late world class leader , Meles Zenawi’s vision a reality. Ethiopia is set to become one of the developed middle income countries within less than five years time from now.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.