‹‹የግሎባላይዤሽን ታቦት ነቀላ፣ ለኦሮሙማ ጣዖት ተከላ!!!›› ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

et5 በኢትዮጵያ የብልጽግና ፓርቲና የብልፅግና ወንጌል !!!

በሃገረ-ኢትዮጵያ ‹‹የግሎባላይዤሽን ታቦት ነቀላ፣ ለኦሮሙማ ጣዖት ተከላ!!!›› ቀን ከሌት የሚደክሙት የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲና የብልፅግና ወንጌል ሰባኪው  ዶክተር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ ሰማይ በታች፣ ፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለምና የእርሶም የኦሮሙማ ዘመን አተላ ታሪክ ያልፋል፣ ዘመኑ  የዓለም አቀፍ ትስስር (ግሎባላይዤሽን) ዘመን መሆኑን መዘንጋትዎ ግን ሃገራችንን የአንድ ብሄር የሙከራ የጥላቻ፣ የጦርነት፣ የዘረኝነትና የተረኛነት ዘመን በመደመር ስም የብልፅግና ወንጌል በመስበክዎ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለማጥፋት ታሪክ ይቅር በማይልዎት የፖለቲካ ሴራ ተተብትበው ይገኛሉ፡፡  በእርሶ የእውቀትና እድሜ ግንዛቤ  ኦሮሙማ የዓለማችን ጥንታዊ ዴሞክራሲዊ ስርዓት አድርገው መቁጠርዎ ለሴቶች ምንም መብት ያማይሰጥ ኦሮሙማ ባህል፣ ከራሱ ዘር ውጪ ያሉትን ባርያ አድርጎ ለመግዛት የሚሻ ኃላቀር ባህልና እሳቤ ያለው አመለካከት ሃገራችን አትሠለጥንም፡፡

በአገራችን የፊደል ሠራዊት ያለው የግዕዝ ቌንቌና ፁሁፍ በብዙ የዓለማችን ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርቱ በሩስያ፣ በእንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ ወዘተ እንደሚሠጥ እየታወቀ የግዕዝ ቌንቌና ፁሁፍን በፊደል አልባው ቁቤ ለመተካት የሚደረግ ከመሃይምነት በቀር የሚጨምሩት ምንም የለም፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር ገዝታናለች የሚሉት ሻብያው ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የወያኔው መለስ ዜናዊ፣ የኦህዴድ ሌንጮ ለታ፣ ኦብነግ፣ ሲአን የመሳሰሉት የጦር አበራዞች ታሪክን በማዛነፍ የዳግማዊ ሚኒሊክና የቀኃሥ ዓለም አቀፋዊ ታሪካዊ ገድል ማጨለም አልተቻላቸውም፡፡ ‹‹የግሎባላይዤሽን ታቦት ነቀላ፣ ለኦሮሙማ ጣዖት ተከላ!!!›› ሲማስኑ ማየት ገና ፀጉራቸው ያልሸበተ፣ እግራቸው ያልሸበተና ልባቸው ያልሸበተ  አማካሪዎች፣ ልጅ እግር ባለጊዜዎች ከጊዜ ጋር ተጣልተው፣ የጊዜ ጎርፍ ይወስዳቸዋል እንላለን፡፡ የኢትጵያን ጥንታዊ ታሪክና የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሥራ፣ የዳግማዊ ሚኒሊክ የጥቁር ህዝቦች ገድል የሆነውን የዓድዋ ድል ታሪክ፣ የቀኃሥ የስልጣኔ ገድል ለማንቆሸሽና ለመበረዝ በኦሮሙማ አዲስ የውሸት ታሪክ ለመተካት የሚደረግ የፖለቲካ ሴራ ሁሉ የከሸፈ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እምነትን በዋቄፈታ፣ መስቀልን በኢሬቻ፣ የኦሮሙማ ማንነት ለማስከበር የሌላውን ማንነት ለማጥፋትና ኦሮሙማን ለመጫን የሚደረግ የባህልና የእምነት ወረራ ያልበሰሉ ፖለቲከኞች ከንቱ ሥራ ነው እንላለን፡፡  የሃገሪቱ ወርቃማ ታሪኮች በአሜሪካ፣ በአውሮፓ ህብረት፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በእስያ፣ በካሪቢያንና አፍሪካ አህጉሮች ሁሉ በየ ቤተመጽሃፍት ቤቶችና ሙዝየሞች የሚገኝ የዓለማችን ህዝቦች ኃብትን ማንም ማጥፋት አይቻለውም፡፡  ህወሓት/ኢህአዴግ ከአዲስ አበባ ነቅሎ መቐለ የመሸገው  በኤች አር 128 በስብአዊ መብቶች ጥሰት በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ታድነው እንዳይያዙ በአሜሪካ መንግስት ሲአይኤ፣ በአውሮፓ ህብረት አገሮች ዲፕሎማቶች ማስጠንቀቂያ ደርሶት፣ ከሥልጣን ገለል እንዲሉ ታዘው መሆኑን እርሶም ያውቃሉ፡፡ ይሄ እጣ ዛሬ ደግሞ ለኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በአማራ ህዝብ ላይ በሚያደርጉት የዘርና ኃይማኖት ጭፍጨፋ (ጆኖሳይድ) የዓለም ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በመንግሥትዎ ላይ  በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በዓለም አቀፍ ስብኣዊ ድርጅቶች፣ በጆኖሳይድ መጠየቅዎ አይቀርም እንላለን፡፡

የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች፣ ልጆቾም ያልቃሉ እም ትሞታለች፡፡

ዓለም አቀፍ ትስስር (ግሎባላይዤሽን) መመዘኛ ሚዛን የተመሠረተው በልዕለ ኃያል ግለሰቦችና በብሔራዊ መንግሥታቶች መኃል ባለ ሚዛናዊ ግንኙነቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በዓለም አቀፋዊው ትስስር ሥርዓት ውስጥ ዓለማችን በነፃ የመረጃ አገልግሎት መረብ ከታች ወደ ላይ፣ ከላይ ወደታች፣ እንደ ሸረሪት ድር የመረጃ መረቦች የተዘረጉበት ዓለም ለመሆን በቅታለች፡፡ በዚህም ምክንያት ልዕላ ኃያል ግለሰቦች ወይም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች (Super-empowered individuals) በዓለም አቀፋዊው ንግድና በብሄራዊ መንግሥታቶች ላይ የሚያሳድርቱን ጫናና ተፅዕኖ ከመቼውም ጊዜ በላይ የግለሰቦች ሚና በዓለማችን ላይ በከፍተኛ ደረጃ የሚገመት ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እውቅና ያገኙበት በትረ ስልጣን የጨበጡበት ወርቃማ ዘመን አንደኛው ኃይል በመሆን በታሪክ ይታወቃል፡፡ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ዘራቸውን እንዲያበዛልን በሥራቸው እንወቃቸው፣ ሃገራችን ብዙ ተፅዕኖ ፈጣሪ ልጆች ለዓለም ህብረተሰብ ታበረክታለች ለአብነት ያህል፡-

ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ፡- የጥናተ ዕፅና ሥነ ባህሪ ተመራማሪ ናቸው፤ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊ ሲሆን በ2009 እኤአ ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ በሳይንሳዊ በዕፅዋት ማዳቀል ምርምር ግኝት፣ የማሽላ ምርት እንዲጨምር በማድረግ የዓለም ምግብ ሽልማት ተሸላሚ ሆኖል፡፡ የሙያ ባልደረባዎቻቸው ስለ ፕሮፊሰር ገቢሳ እጀታ ጥናትና ምርምር ከድረገፁ መረጃ በመውሰድ ለህዝብ ማካፈል ተመራማሪ ኢትዮጵያዊያን እንዲበዙ ትምህርት ይሆናልና እንድትሳተፉ ይሁን፡፡

Gebisa Ejeta is an Ethiopian American plant breeder, geneticist and Professor at Purdue University. In 2009, he won the World Food Prize for his major contributions in the production of sorghum.

https://en.wikipedia.org/wiki/Gebisa_Ejeta

ዶክተር ቴዎድሮስ አድሓኖም ገብረኢየሱስ:- የስነ-ህይወትና ማህበራዊ ጤና ተመራማሪ  ሲሆኑ፣ በ2017እኤአ  የዓለም ጤና ድርጅት ዴሬክተር ጀነራል በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ቴዎድሮስ አድሓኖም በአለማችን መቶ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች አንዱ ሆነው በታይም መፅሔት ተመራጭ ሆነዋል፡፡  የሙያ ባልደረባዎቻቸው ስለ ዶክተር ቴዎድሮስ ጥናትና ምርምር ከድረገፁ መረጃ በመውሰድ ለህዝብ ማካፈል ወጣት ኢትዮጵያዊያን እንዲበዙ ትምህርት ይሆናልና እንድትሳተፉ ይሁን፡፡ Tedros Adhanom Ghebreyesus is an Ethiopian biologist, public health researcher and official who has served since 2017 as Director-General of the World Health Organization. Tedros is the first non-physician and first African in the role; he was endorsed by the African Union. Wikipedia/ https://en.wikipedia.org/wiki/Tedros_Adhanom

ለምን ሲሳይ፡- ደራሲ፣ ገጣሚና ብሮድካስተር ሲሆን ኢትዮጵያዊ እንግሊዛዊ ነው፡፡ ለምን ሲሳይ ከ2015 እኤአ ጀምሮ የማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ቻንስለርና የፋውንድሊንግ ሙዝየም የቦርድ አባል ነው፡፡ ደራሲ ለምን ሲሳይ ብዙ መፅሃፎች ፅፎል፣ የግጥም መድብሎች፣ የድራማ ጹሑፎች አበርክቶል፡፡ በ2019እኤአ ፔን ፔይንተር ፕራይዝ ተሸላሚ ሆኖል፡፡  የሙያ ባልደረባዎቹ ስለ ደራሲው ሥራዎች ከድረገፁ መረጃ በመውሰድ ለህዝብ ማካፈል ወጣት ኢትዮጵያዊያን እንዲበዙ ትምህርት ይሆናልና እንላለን፡፡ Lemn Sissay MBE[1] (born 21 May 1967)[2] is an English author and broadcaster. Sissay was the official poet of the 2012 London Olympics, has been chancellor of the University of Manchester since 2015, and joined the Foundling Museum‘s board of trustees two years later, having previously been appointed one of the museum’s fellows. He was awarded the 2019 PEN Pinter Prize. He has written a number of books and plays./https://en.wikipedia.org/wiki/Lemn_Sissay

ጁሊ ምህረቱ፡- በረቂቅ ገጸ-ምድር ስዕል ከሃያ እስከ ሠላሳ ሜትር ርዝመት ያላቸው ስእሎች በቀለም ብሩሾቾ ከሰማይ ማማ ላይ ወጥታ የገጠርና የከተማ ገፀ-ምድር በመሳል ወደር ያልተገኘላት በዓለማችን በስዕሎቾ ከፍተኛ ተከፋይ አንስት በመሆን ተመዝግባለች፡፡ ጁሊ በአለማችን መቶ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች አንዱ ሆና በታይምስ መፅሔት ተመራጭ ሆናለች፡፡ ጁሊ ምህረቱ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊ ናት፤ የሙያ ባልደረባዎቾ ስለ ሰዓሊዎ ሥራዎች ከድረገፁ መረጃ በመውሰድ ሥራዎቾን ለህዝብ በማካፈል ወጣት ኢትዮጵያዊያን እንዲበዙ ትምህርት ይሆናልና እንላለን፡፡ Julie Mehretu (born in 1970) is an American contemporary visual artist, known for her multi-layered paintings of abstracted landscapes on a large scale. Her paintings, drawings, and prints depict the cumulative effects of urban sociopolitical changes. Mehretu is included in Time magazine ‘s 100 Most Influential People of 2020./https://en.wikipedia.org/wiki/Julie_Mehretu

አቤል መኮንን ተስፋዬ፡-በሙያው  ዘ- ዊኬንድ በመባል የሚጣወቀው ድምፀ መረዋው  አቤል ተስፋዬ ኢትዮጵያዊ ካናዲን ነው፡፡ አቤል ዘርፈ ብዙ ሙያተኛ ሲሆን  ዘፋኝ፣ የሙዚቃ ደራሲ፣ አክተር/ተዋናይ፣ ሪከርድ ፐፕሮዲውስርነት ነው፡፡ በዩቲውብ ‹‹ዘ- ዊኬንድ›› በሚል መጠሪያ በሚልካቸው ዘፈኖቹ በዓለም ለመታወቅ የቻለ ታዕምረኛ የሙዚቃ ሰው ነው፡፡ አቤል በብላክ ፖፕ ሙዚቃ አዲስ ግኝቱ በአለማችን መቶ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች አንዱ ሆና በታይምስ መፅሔት ተመራጭ ሆኖል፡፡ አቤል ተስፋዬ ለግዕዝ ቌንቌ ትምህርት እንዲስፋፋ ለቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ የሃምሳ ሽህ ዶላር፣ ለጥንታዊ የኢትዮጵ ታሪክ ጥናት እርዳታ አድርጎል እንዲም በህፃንነቱ ጊዜት ለጸለየበት ለቶሮንቶ ቅድስት ማርያም ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃምሳ ሽህ ዶላር እርዳታ አድርጎል፡፡ አቤል ለኮቪድ 19 በጎአድራጎት እጁን በመዘርጋት ለሙዝክ ኬር አምስት መቶ ሽህ ዶላር እንዲሁም ስካርቦሮ ሄልዝ ኔትወርክ አምስት መቶ ሽህ ዶላር በድምሩ አንድ ሚሊዮን ዶላር ለግሶል፡፡ አቤል ለአሜሪካ ጥቁሮች አሰቃቂ ፖሊስ ግድያ በመቃወም ‹‹ለብላክ ላይፍስ ማተር›› ድርጅት መጀመሪያ ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ ዶላር፣ ለሁለተኛ ጊዜ ለጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ጊዜም አምስት መቶ ሽህ ዶላር ለግሶል፡፡ የሙያ ባልደረባዎቹ ስለ ሙዚቀኛው ሥራዎች ከድረገፁ መረጃ በመውሰድ ሥራዎቹን ለህዝብ በማካፈል ወጣት ኢትዮጵያዊያን እንዲበዙ ትምህርት ይሆናልና እንላለን፡፡ Abel Makkonen Tesfaye (born February 16, 1990), known professionally as the Weeknd, is a Canadian singer, songwriter, actor, and record producer. He began his recording career in 2010, anonymously uploading several songs to YouTube…After being presented with a Bikila Award for Professional Excellence in 2014, Tesfaye donated $50,000 to the University of Toronto to help them start a course on Ge’ez, the classic language of Ethiopia. He stated that he “was proud to support his hometown by sharing the brilliant, ancient history of Ethiopia.”[204] In August 2016 he continued donations to the University in the creation of a new Ethiopic Studies program.[205] In May 2016 Tesfaye donated $50,000 to the St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Toronto, Canada, the church he once attended as a child…. Tesfaye donated $500,000 each to MusiCares and $500,000 to his hometown front-line hospital workers of the Scarborough Health Network in Ontario, Canada for a total of $1 million to COVID-19 relief.….In the context of media outlets reporting cases of police brutality, in 2016, he expressed disdain, tweeting “blue lives murder”.[212][213][205] In August 2016, Tesfaye donated $250,000 to Black Lives Matter.[214][205] In May 2020, in response to the killing of George Floyd, the ongoing protests in reaction, and racial violence in the United States, Tesfaye donated $500,000 to Black Lives Matter, Colin Kaepernick‘s Know Your Rights Camp, and the National Bail Out; he also posted on his official Instagram account to spread awareness./ https://en.wikipedia.org/wiki/The_Weeknd

ዓለም አቀፍ ትስስር (ግሎባላይዤሽን) አንዱ ገፅታውና ከህግጋቶቹ መኃከል ብሄራዊ ክልላዊ ድንበሮችና ኬላዎችን ማስከፈትና ማጥፋት ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ትስስር አንዱ ገፅታው የዓለም የኢኮኖሚ መሠረት በነፃ የገበያ የካፒታሊዝም ሥርዓት በመዘርጋት ነፃ ንግድና ውድድር በዓለም አቀፋዊ ንግድ ሁሉም እንዲሳተፉ ሃገሮችን የሚጋብዝ መርህ ላይ የተመሠረተ መሆኑ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ግሎባላይዤሽን የእራሱ የሆነ የኢኮኖሚ መመሪያዎች አሉት፡፡ ከህግጋቶቹም መኃከል ብሄራዊ ክልላዊ ድንበሮችና ኬላዎችን ማስከፈት፣ በመንግስት ቁጥጥር ሥር ያሉ ፋብሪካዎች፣ እርሻዎች፣ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ ፋይናንሻል የባንክና ኢንሹራንስ ድርጅቶች ወደ ግሉ ዘርፍ ክፍለ ኢኮኖሚ እንዲዘዋወሩ በማድረግ ለነፃ ንግድና ውድድር ውስጥ እንዲገቡ ብሎም ለውጭ ኢንቨስትመንት አገሮች በራቸውን እንዲከፍቱ የራሱ የሆነ ‹‹አሥርቱ ትዕዛዞች››አሉት፡፡ በዛም ያመኑና የተጠመቁ አገራቶች በዓለም አቀፍ የንግድ ድርጅት ውስጥ የመሳተፍ ብሎም በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እና በዓለም ባንክ እውቅናና ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ይሰብካል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ በመቶ ከተማ፣ ሰማንያ በመቶ ገጠር ንዋሪዎች ባሎት ሃገር የኦሮሙማ የንግድ ባህል መንገድ መዝጋት፣ የኢንቨስተሮች ንብረት ማቃጠል፣ ከክልሌ ውጡ፣ ድንበርና ክልል በየቦታው ማካለል ያልሰለጠነ ለዓለም አቀፍ ንግድ ቀርቶ ለብሄራዊ ንግድ የማይመጥን ፀረ-ንግድና ልውውጥ መርህ ተከታይ በመሆኑ በኦሮሙማ ባህል የኢኮኖሚ እድገት አይታሰብም፡፡ ኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ በመቶ የከተማ ንዋሪ፣ ሰማንያ በመቶ የገጠር ንዋሪ ህዝብ በሚኖርባት ሃገር የአዲስ አበባ ከተማ እድገት ያቀጨጨና ገበሬው በከተማ እድገት ተጠቃሚ እንዳይሆን ኦህዴድ/ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ አንድ ወጥ የከተማና ገጠር የእድገት ፖሊሲ የሌለው ፓርቲ ነው፡፡ ገጠሮች ሁላ ከተማ ይሆናሉ፡፡ ዓለም አቀፍ ትስስር የራሱ የሆነ የህዝብ አስፋፈር (Demographic Pattern) ዘይቤዎች ሲኖሩት ይህም የህዝብ ፍልሰት ከገጠሩ የግብርና የኢኮኖሚ ዘረፍ አላቆ ወደ ከተሜነት በመቀየር ወደ ኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ ገበሬውን ወደ ላብአደርነት በመለወጥ ላይ ያተኮረ የኢኮኖሚ ሥርኣት ነው፡፡ በዚህም መንገድ የገጠሩ ህዝብ ወደ ከተማ በመፍለስ አዲስ የስራ ዕድል በመፍጠር የኑሮ ደረጃቸውን ከፍ በማድረግ ልዩ ልዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች  ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤት፣ ቤተመፅሃፍት ቤት፣ መብራት፣ ውኃ፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ አገልግሎቶች እንዲያገኙ ገጠሬው ወደ ከተሜነት በመቀየር ወደ ዓለም አቀፋዊው የህዝቦች ትስስር፣ የንግድ ልውውጦች፣ የባህልና የፋሽን መከላለሶች ፣ የባህላዊ ልብስ፣ የባህል የምግብ ዓይነቶች ልውውጥና የተለያዩ የመዝናኛ አገልግሎቶች መስፋፋት የሁሉንም አገሮች ምልዕተ ህዝብን የሳይንስና ቴክኖሎጅ ጥቅም ተቆዳሽ እንዲሆኑ በር መክፈት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃምሳ በመቶ ከተማና ሃምሳ በመቶ ገጠር ንዋሪዎች እንዲሆኑ ለማድረግ በትንሹ ከሠላሳ እስከ ሃምሳ ዓመታት ይጠይቃል፡፡ በኦሮሙማ ባህል የአዲስ አበባን፣ ድሬዳዋን፣ የቤኒሻንጉልን ወዘተ ከተሞችና ገጠሮች ስነ-ህዝብ በኦሮሞ ህዝብ በመሙላት የሌሎችን ዘሮች በተለይ አማራውን፣ ጉራጌውን፣ ጋሞውን፣ ወዘተ በግፍ በማስወጣት የዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) በማድረግ የዶክተር አብይ አህመድ ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ተጠያቂ ናቸው፡፡

ዓለም አቀፍ ትስስር ሌላው ገፅታው የእራሱ የሆነ ጨፍላቂ ባህል (Dominant Culture) ያለው ሲሆን የኣለም ህዝቦች ባህላዊ ልውውጥና ዝምድና ቀስ በቀስ ወደ አንድ ወጥ ባህልና ቌንቌ ሊሸጋገር ይችላል፡፡ ለዚህ ነው ግሎባላይዣሽን የራሱ በሆነው ባህል በጡሩውና በመጥፎው ገፅታዎቹ አሜሪካናይዤሽን (Americanization) ባህል በዓለማችን ህዝቦች ላይ መጫኑ አይቀሬ ነው፡፡ የአሜሪካኖቹ ባህል (“from Big Macs to imacs to mickey mouse”) መሸጋገሩና ዓለም አቀፋዊ ባህል መሆኑ የማይሻር ትንቢት ነው የሚሉን፡፡ የአሜሪካኖቹ ባህል ማስፋፍያ ማዕከል ዋናው የፊልም ኢንዱስትሪው ሆሊውድ የታሪክ፣ የጦርነት፣ የፍቅር፣ የቅብጠተ ወሲብ፣ የሳይንስ ፊክሽን የፈጠራ የትወና ክህሎት የሰው ልጆችን የህሊናና ምናብ የተቆጣጠረ ብዙ ቢሊዮን ዶላር በአመት የሚዝቁበት ኃብት ለመሆን ችሎል፡፡ የምዕራባዊያን ስልጣኔ የባህል ወረራ የዘመናችን የማይዋጥና የማይተፋ የጉሮሮ ላይ አጥንት በመሆን ወይ መቀላቀል አሊም መደፍጠጥ የጌቶቻችን የጊዜው ትዕዛዝ ነው፡፡ እንዲሁም የምዕራባዊያን ስልጣኔ በባህል የፋሽን ኢንዱስትሪ ዓለም አቀፋዊውን ወጣት ያማለለ፣ እራሱን ሳይሆን በእነሱ የተሰረቀ፣ በፋሽን ቅጅ የማለለና ማንነቱን በሪሞት ኮንትሮል የሚቆጣጠሩት በዓለም አቀፍ የመረጃ መረብ በመዳፉ ባለች የእጅ ስልክ የሞባይል ህሊናውን የተሰረቀና የተጠመቀ ደቀመዝሙር ከመሆን ሌላ የእራሱ የፈጠራ ስራ እንዳይኖረው የተደረገበት ዘመን ነው፡፡ የምዕራባዊያን ስልጣኔ የትምህርት አሰጣጥ የደሃ ሃገራት ምሁራንና ሳይንቲስቶችን ከሃገራቸው አስኮብልሎ የእነሱን አገር ሲታደጉና ሲያለሙ እድሜቸውን የጨረሱ የደኃ አገራቶች ምሁራን ለአገራቸው ብሎም ለአህጉራቸው በማሰራት ምሁራንን የመሳብ አርቆ አሳቢነት እንጂ አንተ ኦሮሞ ነህ፣ አማራ ነህ፣ ትግሬ ነህ መባባል ኃላቀር ሰው ሰው ያልሸተተ አስተሳሰብ ነው እንላለን፡፡ ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያንን እናብዛ ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ፣ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሓኖም፣ለምን ሲሳይ፣ጁሊ ምህረቱና አቤል ተስፋዬ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

 

1 Comment

  1. The Ethiopian Farmers Professional Association calls upon the Ethiopian government and the Tigray government to allow the formation of an Ethiopian technocrat transitional government by immediately releasing all political prisoners who are charged with only political related charges in Ethiopia.

    The Ethiopian Farmers Professional Association calls upon the international community to advise the current Ethiopian government and the current Tigray’s government on how to ensure peace and security amidst the pandemic by peacefully, without resistance allowing the technocrat transitional government urgently take over all the government within Ethiopia including within Tigray , currently the government is under the chokehold of the former EPRDF or currently known is two names Prosperity Party and Tigray People’s Liberation Front.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.