ኢሳት ! ኢሳት! ኢሳት! – ፊልጶስ

ESAT Supportየፈለግናውን ልንል እንችላለን፣ ኢሳት ብዙ ተራራዎችን የወጣ፣ ብዙ ቁልቁልነቶችን የተንደረደረ፣ ብዙ ወንዞችንና ሸንተረሮችን ያቋረጠ፣ በዚያ ጭንቅ ወቅት እስትንፋስ የሆነልን ሚዲያ ነው።

ለኢትዩጵያዊያን  አንድ ሃቅ አለ፣

ኢሳት ለኢትዩጵያ አንድነት በፅናት በመቆም ፣ ሌት ተቀን ኢትዩየያዊያነትን በማስተማር፣ የጎሳን ፓለቱካ የታጋለና አሁን ላለንበት ለውጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዝ ሚዲያ ነበር ፣ ነው። ይህን እውነታ ብንክድ ትርፋ ትዝብት ነው፣ ኢትዩጵያዊነት ይታዘበናል።

 

ግን በእኔ እይታ አሁን ለደረስንበት በይፋ ከሚነገረው  ችግር በተጨማሪ ፣ ኢሳቶች ሊናገሩት የፈሩት ሃቅ ወይም የማይናገሩት እውነታ፡

የመላው የኢትዩጵያ ህዝብ መስዋእት የከፈለለትን ሚዲያ አዲስ አበባ ላይ አርብኞች ግንባር፣ “……ኢሳት የኔ ነበር፣ አሁን ወደ ህዝብ ማስተላለፍ እፈልጋለው።………..”

ያለው መልእክትና የተዛባ እውነታ ፣ ግዜያዊ የፓለቲካ ትርፍ ነው።

“ርግጥ ነው በበላይነት ሲመሩትና ሲያስተባብሩት ነበር። ግን የውጭ አገር የአንድነት ሃይሉ ተሳክቶለት በወኔና በለጋስነት ተባብሮ የሰራው ስራ ቢኖርና ውጤት ያስመዘግበበት ዋናው ኢሳት ነው። ይህን ሚዲያ ነበር የግል ንብረታቼው እንደነበር የነገሩን። ያኔ የብዙዎቻችን ቅስም ተሰበረ። ይህን በማለታቼው ምን ሊያተርፋ ይሆን? ብለን ግራ ገባን፡፡ በወቅቱ  ከወያኔ ዘመን በበለጠ የጎሳ ፓለቲካ የጦዘበት በመሆኑ  ኢሳት አስፈላጊነቱ ግልፅ  ነበርና::

 

በ’ርግጥ ለእኔ ቢጤው   ኢትዩጵያዊነቴን እስክታደገልኝ ድረስ ሰይጣንም  “እኔ ባለቤቱ ነኝ ::“ ቢለኝ ደንታ የለኝም። ህዝብን መዋሸት ግን ዋጋ ያስከፍላልና ይኽው እየተከፈለ ነው። ኢትዩጵያና ኢትዩጵያዊነት ከማንም የፓለቲካ ድርጅትም ይሆን ቡድን በላይ ነውና።

 

እንግዲህ ከዚህ በኋላ ነው ኢሳት በተለይ ታማኝን ያህል የሚዲያው ምሰሶ የነበረን ሰው ወደ ጎን ብሎ ቁልቁለቱን ተያይዞ ለዚህ የበቃው። አሁንም በእኔ ቢጤዌች እምነት ኢሳት በምንም ዓይነት መንገድ ቢሆን መደገፍና ወደ አየር መመለስ አለበት። ግን እራሱን እንደገና ማደራጅትና ማስተካከል ይጠበቅበታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አፈትልኮ የወጣ ልዩ የወያኔ ደህንነት ሪፖርታዥ

መነሻውን እና መድረሻውን ኢትዩጵያና ኢትዩጵያውንትን አድርጎ ፣ የጎስኝነትና የመንደር ፓለቲካን በፅናት መታገልና ማስተማር ይጠበቅበታል።

 

እኛም በያለንበት ኢትዩጵያዊያንን በመላው ዓለም ማስተባበርና መርዳት ይጠበቅብናል። በየአገሩ ኢሳት ድጋፍ እንዲዋቀር ጥሪ ይደረግ። በ”ርግጥ ትላንት የበተነውን ደጋፊ. ዛሬ መሰብሰብ ቀላል አይደለም። ይሁን እንጂ ኢሳት በኢትዩጵያና በኢትዩጵያዊነት ላይ እስከተመሰረተና ጠንክሮ እስከ ስራ ድረስ በሁለት እግሩ የማይቆምበት ምክንያት አይኖርም።

 

-1-

በተጨማሪም   በአሁኑ  ሠአት  ኢሳት ከሚወቀስበት  አንዱ መንግሥትን  በተለይም  ጠቅላይ ሚኒስተር  አብይ አህመድን  በጭፍን መደገፍና  በተቃውሚ የአንድነት ሃይሎች ላይ ሚዛናዊ የጎደለው ትችትና ዘገባ ማድረጉ ነው፡፡ ይህ እውነታ ያለው ሲሆን ” ለአገር እንደነትና ሰላም  ተብሎ ነው ” የሚለው  ለሌሎች በኢትጵያ እንድነት ላይ ፅኑ እምነት ያላቼውንና  በምክናያት መንግስትን ለሚተቹ  በቂ አይሆንም፡፡ እገርና ህዝብ ፀንቶ ሊቆምም ሆነ አንድነቱ ሊጠበቅ የሚችለው የዲሞክራሲ ተቍማትና በመገንባትና በማደራጀት እንጅ በግለሰቦች በጎ ፍቃድ ሊሆን አይችልም፡፡ የግለሰቦች አስተዋእፆ እንደተጠበቅ ሆኖ፡፡

ለኢሳት ሚዛናዊነት፣ ግልፅነት፣ እውነታ፣  የኢትዮጵያ  አንድነትና ኢትዮጵያዎነት አንድ ቁጥር መርሁ ሊሆን ይገባል፡፡ ኢሳት ከግለሰቦች ወይም ከቡደኖች እራሱን  ነፃ ማውጣትና ከህዝብ በተውጣጡ ቦርድ እየተመራ ራሱን እንደ አዲስ ማደራጀትና መደራጀት እንዳለበት ይሰማኛል፡፡

አሁንም ኢሳት ከነችግሩ ለኢትዮጵያያ ህዝብ አማራጭ የሌለው ሚዲያ መሆኑ ለሁላችንም ግልፅ ሊሆን ይገባል፡፡

ኢሳት እንደትላንቱ ሁሉ ዛሬም የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ እንዲሆን የድርሻችን እንወጣ።

 

አመሰግናለሁ!

———//——

 

 

1 Comment

  1. Its like you said esat abandoned the holy ideas that got it where it was. Unfortunately the presumed personal political gains to be had was too much for birhanu to resist. Unfortunately as we can see now those gains were hollow and does not seem they will materialize looking from outside. The hidden agreements berhanu made we do not know about and may never be known. As can be seen esat is still controlled by berhanu and his looser political gain mentality. Would esat relieve its shackle from berhanu is highly unlikely. When that day comes and it better be soon esat i believe will get its support from Ethiopians all over the world. Any presence of the old g7 is unacceptable at any leadership role including the current leader. Otherwise it will be the end of esat as we remember it.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.