አዲዬስ ኢኮኖሚክስ! በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የነፍስ ወከፍ ገቢ አንድ ሽህ ዶላር (37 ሽህ ብር ) በዓመት! ሚሊዮን ዘአማኑኤል

eeአዲዬስ ኢኮኖሚክስ!

የዶክተር አብይ አህመድ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ  ኢትዮጵያን ሊበታትናት የደረሰውን ጥልቅ የብሔር ስንጥቆች ክፍፍል ብሎም የኃይማኖትና ዘር ጭፍጨፋ (ጆኖሳይድ) ስጋት ውስጥ ጥሎታል፡፡  በዛም  የመንግሥታዊ ሽብርተኛነት ሊለውጠው ያልቻለው በደመነፍስ ስሜት የኃይል እርምጃ መውስድና መጨቆን ህዝቡን አስመረረ፡፡ በዚህ አመት ብቻ 147 አሰቃቂ ግጭቶች ምክንያት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል፣ እንደ የታጣቂዎች የግጭት ቦታ የሁኔታ መረጃ ፕሮጀክት (ማፑን አጉልታችሁ ተመልከቱ) (Armed Conflict Location & Event Data project (see map) በጁላይ ወር በአዲስ አበባ አካባቢና በኦሮሚያ ውስጥ አመፅና ነውጥ ተነስቶ ነበር፡፡ በመላ ሃገሪቱ በተደጋጋሚ በሚከሰቱት ግጭቶችና የዘር ፍጅት ከክልሌ ውጣ፣ ህዝብ በነፃነት ተንቀሳቅሶ መስራት አልቻለም፡፡ ሃገሪቱ በጦር አበጋዞች የክልል መንግሥቶች  የድንበር ግጭት የተነሳ ወደማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነት ለመሸጋገር ክልሎች ካራ እየሳሉ ይገኛሉ፡፡ የትግራይ ክልል 250000(ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ) ልዩ ሓይል፣ የአማራ ክልል 300000 (ሦስት መቶ ሽህ) ልዩ ኃይል፣ የኦሮሚያ ክልል 400000 (አራት መቶ ሽህ) ልዩ ኃይል፣ የሱማሌ ክልል 40000 (አርባ ሽህ በአብዲ ኢሌ ሄጎ ኃይል)፣ የጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሃረሪ፣ አፋር፣ ደቡብ (ሲዳማ ክልል አንድ ሽህ ልዩ ኃይል)፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት 250000(ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ) ይገመታል፡፡ ሁሉም ክልሎች የራሳቸው ሚሊሽያና ፖሊስ ኃይል በተጨማሪ አላቸው፡፡  ይህ የዕለት ተዕለት ሥራችን ሆኖ ምርት የማያመርት እልፍ ልዩ ኃይል ጥገኛ ተዋሲያንና ሰባት ሚሊዮን የኢህአዴግና ብልፅግና ፓርቲ ጥገኛ ተዋሲያን መጅገር ካድሬዎች ባሉበት አገር የኢኮኖሚ እድገት አይታሰብም፡፡ የህክምና ዶክተሮች መቅጠር ያልቻለ መንግሥት ብልፅግና አያመጣም፡፡ የህግ የበላይነት የማያስከብር መንግስት ብልጽግና አያመጣም፡፡ በሃገሪቱ የኮሮና ቨይረስ ወረርሽኝ፣ ጎርፍ፣ አንበጣ ወረርሽኝ፣ የዘርና ኃይማኖት ፍጅት እንዲሁም የድንበር ግጭት እያለ የኢኮኖሚ እድገት ውሸት ነው አሊያም አዲዬስ ኢኮኖሚክስ!!!፡፡

የሃገሪቱን ምጣኔ ኃብት ሁኔታ በቀላሉ ለመረዳት፡-

Ethiopia: Gross Domestic Product, billions of U.S. dollars, GDP per capita & Debt to GDP

(measure: billion U.S. dollars; Source: The World Bank)

አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት፣የነፍስ ወከፍ ገቢና  የመንግሥት ዕዳ ከጠቅላላ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት

ዓመት Year2010201120122013201420152016201720182019
 አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት GDP29.9331.9543.3147.6555.6164.5974.381.7784.2796.11
የነፍስ ወከፍ ገቢ

GDP per capita

341.6369.2389.9419.2449.4482.6514.1548.4570.7602.2
ዕዳ ከጠቅላላ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት Debt to GDP26.825.627.428.631.832.134.935.66057

 

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6 ዓመት የስራ ዘመን 1 ልዩ ስብሰባ ተካሂዷል። በዚሁ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። 1

ምጣኔ ሃብት:- ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ የ6.1 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገቡን ይፋ አድርገዋል። የኢንደስትሪ ዘረፉ ደግሞ ከፍተኛውን እድገት ካስመዘገቡ ዘርፎች መካከል ቀዳሚው ነው።

{1} አመታዊ ጥቅል ምርት (Gross Domestic Product)፡- ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2012 የበጀት ዓመት 3.37 (3.4) ትሪሊየን ብር ጠቅላላ አገራዊ ምርት መመዝገብ መቻሉንም ተናግረዋል።

<<ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ አጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) 2.2 (ከሁለት ነጥብ ሁለት) ትሪሊዮን ብር ወደ 3.4 (ሦስት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ማደጉን ኢኮኖሚው መመንደጉንና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ  ድባቅ መተን ለዓለም ዓቀፍ ንግድ የምናስተምረው ትምህርት እንዳለ  ያበስሩን ይሆናል፡፡   የዓለም አቀፍ ንግድ እንቅስቃሴ ግብይይት የሚደረገው በዶላር፣ ፓውንድ፣ ዩሮ፣ በመሆኑ ዓለም ባንክና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) መረጃ በዶላር የሆነው ለዚህ ነው፡፡  በዚህም ስሌት በ2011ዓ/ም 2.2 (ከሁለት ነጥብ ሁለት) ትሪሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወደ ዶላር ስንቀይረው 75.9 ቢሊዮን ዶላር  (አንድ ዶላር በ29) ብር ይሆናል፡፡ በ2012ዓ/ም  3.4 (ሦስት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ወደ ዶላር ስንቀይረው 94.4 ቢሊዮን ዶላር  (አንድ ዶላር በ36 ብር) ሲመነዘር ይሆናል፡፡ በጥቁር ገበያ የብር ምንዛሪ ተመን ከ46 ብር እስከ 50ብር መድረሱን በጥናታችን አረጋግጠናል፡፡ ዶክተር ዐብይ አህመድ  በኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ ቆራጥ አመራር የሃገራችንን ጂዲፒ ትሪሊየን ውስጥ ከተናል ለማለት አስቦ ከሆነ የብር የመግዛት አቅም መሽመድመድና ብር የወረቀት ያህል መርከሱን ያሳየናል እንጂ የኢኮኖሚ እድገት በኮቪድ 19 ዘመን የሚታሰብ አይደለም እንላለን፡፡ >>

{2} የነፍስ ወከፍ ገቢ (GDP per capita) የነፍስ ወከፍ ገቢም 1ሺህ ዶላር መድረሱን ተናግረው፤ ይህም መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ኢትዮጵያን ማሰለፏን እንደሚያረጋግጥ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይፋ አድርገዋል።

አጠቃላይ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት፣ለጠቅላላ የህዝብ ቁጥር አካፍለን የእያንዳንዱን ሰው የነፍስ ወከፍ ገቢ እናገኛለን፡፡

በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዘመነ አገዛዝ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ አንድ ሽህ ዶላር ወይም (37 ሽህ ብር ) በዓመት ገቢ ያገኛል ብለዋል፡፡

 • 1000 ሽህ ዶላር በአመት በ12 ወራት ሲካፈል3 ዶላር ይሆናል ለ 30 ቀን ሲካፈል ደግሞ 2.8 ዶላር በቀን በ8 ሰዓት ሲካፈል 0.35 ሳንቲም በሰዓት በምንም ተዓምር ወደ መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው አገራቶች ተርታ አያስገባም፡፡ የመካከለኛ ገቢ አገሮች የነፍስ ወከፍ ገቢ 10000 (አስር ሽህ ) ዶላር መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡

 

 • አንድ ዶላር በ 37 ብር (https://combanketh.et/exchange-rate-detail/) ሲመነዘር 1000 ሽህ ዶላር ይሆናል 37000 ብር በአመት በ12 ወራት ሲካፈል 3083 ብር ይሆናል ለ30 ቀን ሲካፈል ደግሞ 102 ብር በቀን በ8 ሰዓት ሲካፈል 12ብር 85 ሳንቲም በሰዓት በምንም ተዓምር ወደ መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው አገራቶች ተርታ አያስገባም፡፡ የመካከለኛ ገቢ አገሮች የነፍስ ወከፍ ገቢ 10000 ዶላር መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡)   በእኛ ስንመነዝረው ደግሞ 370000 (ሦስት መቶ ሰባ ሽህ) ብር በዓመት ይሆናል፡፡

 

Ethiopia GDP per capita1981-2019 Data | 2020-2022 Forecast | Historical | Chart

The Gross Domestic Product per capita in Ethiopia was last recorded at 602.20 US dollars in 2019. The GDP per Capita in Ethiopia is equivalent to 5 percent of the world’s average.

1

Ethiopia GDP per capita

The GDP per capita is obtained by dividing the country’s gross domestic product, adjusted by inflation, by the total population.

 

የእዳ መጠን;-<<ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በአገሪቱ የሚገኙ ግዙፍ ኩባንያዎች ከ600 ቢሊዮን ብር በላይ እዳ ተከማችቶባቸው እንደነበረ ተናግተዋል። እነዚህ ኩባንያዎች ከአገሪቱ በጀት በላይ እዳ ውስጥ ተዘፍቀው እንደነበረ ተናግረው እነዚህን ኩባንያዎች መልሰው እንዲዋቀሩ በመደረጉ ተጋርጦባቸው ከነበረው አደጋ መንግሥት እንደታደጋቸው ተናግረዋል።መልሶ የዋቃሩ ስራ ባይሰራ ኖሮ “ስለመብረት እና ስኳር ማውራት አንችልም ነበር” ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ።>>

 

{3} የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከጠቅላላ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ጋር ሲነፃፀር /Ethiopia Government Debt to GDP1991-2019 Data | 2020-2022 Forecast | Historic

የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከአመታዊ አጠቅላላ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) ጋር በማነፃፀር በየዓመቱ አጠቃላይ ዕዳችንን ከአመታዊ  አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ጋር የምናወዳድርበት የምጣኔ ኃብት ትምህርት ነው፡፡  በኢኮኖሚስቶች ምክረ ሃሳብ መሠረት፣ የአንድ አገር ዕዳ ዝቅተኛ ከሆነ ሃገሪቱ አምርታ በውጭ ንግድ ከምትሸጠው ምርት፣ ሸቀጣሸቀጥና አገልግሎት ከምታገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ እዳዋን ለመክፈል ያስችላታል፡፡ በአንፃሩ የሃገሪቱ ዕዳ ከፍተኛ ከሆነ ምርቶን ሸጣ የምታገኘው ገቢ እዳዋን ለመክፈል አያስችላትም፡፡ ስለዚህ ዕዳ ከጂዲፒ ንፅፅር ከመቶ ከሃምሳ በታች ሲሆን የተሸለ ሲሆን ከሃምሳ በላይ ከሆነ ግን ዕዳ ለመክፈል አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

“In economics, the debt-to-GDP ratio is the ratio between a country’s government debt and its gross domestic product. A low debt-to-GDP ratio indicates an economy that produces and sells goods and services sufficient to pay back debts without incurring further debt.” Wikipedia

The debt-to-GDP ratio is the metric comparing a country’s public debt to its gross domestic product (GDP). By comparing what a country owes with what it produces, the debt-to-GDP ratio reliably indicates that particular country’s ability to pay back its debts.

የህወሓት/ኢሀአዴግና ኦዴፓ ብልፅግና  የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከአጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) ጋር በማነፃፀር ከ1991 እስከ 2020እኤአ ዕዳ ከጂዲፒ ንፅፅር እንቃኛለን፡፡ በዚሁ መሠረት በ2010እኤአ 26.8%፣ በ2012እኤአ 27.4%፣ በ2014እኤአ 31.8%፣ በ2016እኤአ 34.9%፣ 2018 እኤአ 60%፣ በ2019እኤአ 57% በመቶ መሆኑን ከሠንጠረዡ ላይ መረዳት ይቻላል፡፡  ዶክተር ዐብይ አህመድ የሃገሪቱን የእዳ ጫና ከአጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) ከ31% በመቶ ወደ 25% በመቶ እንዲቀንስ አድርገናል ብለው ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡  ከታች የምጣዩት የሠንጠረዥ ማስረጃ ምንጩ ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ዶት ኮም/ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተገኘ እንደሆነ ያሳያል፡፡

Ethiopia recorded a government debt equivalent to 57 percent of the country’s Gross Domestic Product in 2019.

2Ethiopia Government Debt to GDP1991-2019 Data | 2020-2022 Forecast | Historic (https://tradingeconomics.com/ethiopia/government-debt-to-gdp/)

 

ምንጭ፡-

{1} https://www.bbc.com/amharic/54597783/ዐብይ አሕመድ፡ /ሚር ዐብይ ከሕውሓት ጋር የተከሰተው አለመግባባትበሕግ እና ሕግ ብቻ የሚመለስ ይሆናልአሉ 19 ጥቅምት 2020, 13:30 EAT

5 Comments

 1. The reformed economic policy is defending Ethiopia’s national economic sovereignty. As a result in a short period of time the income of Ethiopians skyrocketed to this level. It might sound too good to be true but it is true, the numbers do not lie.

  Ethiopia could have arrived to this stage decades ago if only the economic policies were reformed back then , even though it took too long, now we can finally say “YES WE HAD ARRIVED!!” .

  From now on there is no going back The future keeps getting brighter and brighter each minute especially for all of those who got discipline in budgeting money .

  prosperityuk.com › Articles
  Web results
  Defending National Economic Sovereignty – Prosperity

 2. ምነው ልጄ? በአለም ያለኅው ኢኮኖሚስት አንተ ብቻ አስመሰልከው? ሁሌ የምትጽፈው ደግሞ “ነጋቲቭ ነጋቲቩን” ብቻ ነው፡ አይደብርህም? ወይ የምጽፈው ለፖለቲካ አላማ ነው በለንና እኛመ ባላነበበ እንለፈው፡፡ ያለበለዚያ ጎበዝ ከሆንክ ወይ በጆርናል አርቲክል ወይም Ethiopian Economics Association በመሳሰሉ እና ተዐማኒነት ባላቸው outlets ከእኩዮችህ (peer group) ጋር ብትነጋገር የሚሻል መሰለኝ፡፡

  • ከድር ሰተቴ በክፋት አትይብኝ እንጂ እንዲህ አይነት ነገር ላንተ አልተሰጠም ነገርን አራቅቆ ማየትና መመርመር ይጠይቃል ምን አለፋህ አንተ ዝም ብለህ ኑር ንከስ ሲሉህ ንከስ ለመኖርህ ግን የሚያሰብለህ ያስብልሀል እንደዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ።
   እንዴት መታደል ነዉ እንዳነት መኖር ቢቻል አይ ትንተና እዚህ ከምታባክነዉ መጽሀፍ ነገር ጠርዘህ ለታየ ደንዳ ለሺመልስ አብዲሳ መታሰቢያ ይሁንልኝ ብለህ ልቀቀዉ እንገዛለን ችግር የለዉም።

 3. ከድር ሰተቴ

  በዶ/ር አብይ አህመድ አመራር ዘመናትማ የኢኮኖሚስቶቻችን ዕጣ ፋንታማ ውሀ በላው። በይበልጥ ምን ለማለት እንደፈለግኩኝ ለመረደት
  ” What did Abiy Ahmed say about Economists and Eduacted ? By Bedassa Tadesse , Professor of Economics, – ” የሚለውን መጣጥፍ ብትመለከተው በይበልጥ ትረዳኛለህ።

 4. ዘ አማኑኤል ነህ ማነህ ጽሁፍህ መረጃን ያማከለ ቢሆንም እንደዚህ መላ ቅጡ በጠፋን ጊዜ የታችኛዉን ወደላይ የላይኛዉን ወደ ሰማይ እያጓንክ የተስፋ እንጀራ ብተመግበን ምን ይጎዳሀል ባለፈዉ ስለ ተወልደ አየር መንገድ የጻፍከዉን አንብቤ ሳምንት ሳለቅስ ከረምኩ አረ ወዳጄ ትንሺ ለህዝብ ማሰብ ጥሩ ነዉ። አገር የሚያጠፋ የመሬት መንቀጥቀጥም ሆነ እሳተ ጎመራ መፈንዳቱ ቢታወቅም ለህዘቡ አይነገረም ከተነገረዉ እልቂቱ የከፋ ይሆናል። እዚህ ላይ በተቃዉሞ አትይብኝ ማስረጃ አጣቅሰህ ለትምህርትና ለሀገር በማሰብ ይመስለኛል የማሰጠንቀቂያ ደወል የላክልን። ከዚህ በላይ አንዱ እንዳለዉ ለንክሻ በየክፍሉ የተመደቡ ስላሉ በእዉቀት የተጎዱ ስለሆኑ እንዲህ አይነት ጽሁፍ እየላክህ መከራቸዉን አታብላቸዉ ይሄን አንብቦ መረዳት ለነሱ የቅጣት ያህል ነዉ ንክሻዉን የማትፈራ ከሆነ ግን ሞቅ አድርገዉ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.