የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ የአንድ ወር የንቅናቄ ዘመቻ የፊታችን ጥቅምት 9 እንደሚጀመር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ

121808822 2776850955890699 1781113639677221454 o በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም ለማስወገድ የ1ወር የንቅናቄ ዘመቻ ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ የተፋሰሱ ልማት ከፍተኛ ምክር ቤት 8ኛው ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ነው።
በንቅናቄ ዘመቻው ሁሉም ክልሎች፣ የፌዴራል ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ተሳታፊ ይሆናል ተብሏል።
አረሙን የማስወገድ ንቅናቄው ”ህዳሴ ግድብ ያለአባይ፤ አባይ ደግሞ ያለጣና ማሰብ አይቻልም” በሚል ማዕቀፍ የሚካሄድ መሆኑን ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ንቅናቄውን ለማካሄድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁም ነው የተገለፀው።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2013 (ኢዜአ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.