“ተጨፈኑ እናሞኛችሁ ” የብልጠት የፖለቲካ ጨዋታ እንዲቆም ማድረግ አገርን ከጥፋት ፤ ህዝብን ከሞት እና ስደት መታደግ ነዉ – ማላጅ

Abiy Ahmed parliamentበኢትዮጵያ  የመንግስት ስርዓት ፀረ ኅዝብ እና አንድነት ኃይሎችን በተለያዩ የሃይል እና ጉልበት ግብዓቶች በማገዝ የብዙሃን ዜጋ ደህንነት ፣ በአገር ሰርቶ ሀብት እና ንብረት የማፍራት ብሎም በአገሪቷ በየትኛዉም ክፍል የመኖር ሠባዊ እና ህጋዊ የዜግነት መብት በማሳጣት እንደሁለተኛ ዜጋ በባይተዋርነት እንዲኖር ሲደረግ የረጅም ዓመታት የአገራችን ህዝቦች  ያሳለፉት የቀይ/ነጭ  ታሪክ  እና  በክፋት እና ጥፋት ይዘቱ የዘመናችን  ወደር የለሽ የማይፋቅ ታሪካዊ ክስተት እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በተለይም በኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያ አንድነት ላይ ጠንከር ያለ እይታ እና ይሁንታ ባላቸዉ የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ ከየትኛዉም የአገሪቷ ክፍል ከሚገኘዉ ማህበረሰብ የትዉልድ ሀረግ ይመዘዝ ከዚህ በተቃራኒ የማርያም ጠላት እየተባሉ እኛን ያየህ ተቀጣ እንዲሉ ተወልደዉ ዕትብታቸዉ በተቀበረበት ፣ ባደጉበት ፣ ወልደዉ ስመዉ በኖሩበት በየአካባቢዉ ዉግዘት፣ ዉርደት፣ ስደት፣ሞት እና እንግልት እንዲያስተናግዱ በክፉዎች ተፈርዶባቸዉ የአመታት ዕልቂት አሁንም ድረስ እንዲቀጥል የመሆን ሚስጥር  በተደጋጋሚ ይስተዋላል  ፡፡

በኢትዮጵያ በሚደረገዉ ህብረ ብሄራዊ አንድነት እና የአገር ግንባታ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን ወደ ጎን ትቶ ታሪካዊ እና ብሄራዊ የሩቅ እና የቅርብ ጠላት ማደላደል የዉስጥ ቀጋ የዉጭ አልጋ ከመሆን ዉጭ ለአገር እና ለወገን ዕድገት እና ብልፅግና ማደናቀፍ እንጅ መደገፍ ሊሆን አይችልም  ፡፡

ለሁሉም የሚበጀዉ የጋራ ችግርን በገራ መንቀስ እና መዉቀስ ብሎም በጋራ አንድነት እና ጥረት መፍታት እንጅ ችግርን ማድበስበስ የገራ መድሃኒት እና ፈዉስ አያስገኝም ፡፡

ብዙ ጊዜ በአጥፊ እና በደል አድራሽ ወገን  ሚዛን እንዲያጋድል ሲደረግ ተበዳይ እና ንፁሃን አይን እያየ ጆሮ እየሰማ ሞት እና ዉርደት  አሜን ብሎ እንዲቀበል የማድረግ ሸንጋይ የፖለቲካ  አካሄድ  ልማድ በአገራችን ስር ከሰደደ ቆይቷል ፡፡ ይህም ከጅምር የታየ የብልጠት እና ህዝባዊ ክህደት አደረጃጀት ማሳያ ከሚሆን ጥቂቱን ማየት እንደሚከተሉት ማየት በቂ ነዉ ባይባልም በማሳያነት የሚጠቀስ ማስረጃ የማይሻ የአደባባይ ሚስጥር ነዉ ፡-

 • ኢህዴግ የቀደመዉን ስርዓት መከላከያ በዉጭ ጠላት ተፅዕኖ ትጥቅ እንዲፈታ እንዲሆን በማድረግ ብሄራዊ ጦር በብሄር ጦር ተካ፣
 • ወደ አገር ቤት በለስ ቀንቶት ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ሳይቀር በተለይም ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያን( ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ እና ሸዋን በሰላም እና ፀጥታ ማስከበር ነፍስ ወከፍ ጠበንጃ አይደለም የሽንኩርት መክተፊያ ካራ/ቢላ  እንዲፈታ ፤እንዲቀማ አደርጓል፣
 • የሌላቸዉ ሳይቀር በስመ ሠላም እንዲሞቱ፣ አካለ ጎደሎ እንዲሆኑ በማድረግ እና ራሳቸዉን እንዳይከላሉ በማድረግ በህዝብ እና አገር ላይ የደረሰዉ ግፍ እና መከራ ከመቁጠር ይልቅ ፤ከድሃዉ አርሶ አደር በተገፈፈ/ በተቀማ መሳሪያ ሀብት ንብረት ያካበቱትን እና በህዝብ መሳሪያ ለወንጀል ስራ የሚገለገሉትን መቁጠር ይቀላል፣
 • በሌሎች የአገሪቷ ክፍልም በየአካባቢዉ መስተዳደር የስርዓቱ አገልጋይ እና ታማኝ በሚሰጠቻዉ ተልዕኮ ምክነያት ከጥቃት ለመከላከል እና ህዝብ ለማስገበር በታጠቁት መሳሪያ ለሁለት አሰርት ዓማታት ምን እንደተሰራ እና እየተሰራ እንዳለ ግልፅ ነዉ፡፡
 • ሌላዉ በክልል አደረጃጀት በየትኛዉም የአገሪቷ ክፍል በሌለ እና ምክነያቱ እንኳን በዉል ይህ ነዉ በማይባልበት በክልል ሶስት (በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ) በቋንቋ ላይ የተመሰረተ የዞን መስተዳደር( አዋዊ፣ ኦሮሞ ) ሲኖር ይህ ድሮም የነበሩ እና ያሉ ህዝቦች ሆነዉ እያለ ስያሜዉ ግን እንዴት እና ለምን የሚል በተለይ ከሁለት ዓመታት አስቀድሞ አልነበረም ፡፡

እነዚህን ከላይ የተቀስኳቸዉን ጥቂት እና ቀላል  ሁነቶች ማለትም ፡

ኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ እንዲራቆት (ርቃን እንዲሆን) እና ሁሉን አሜን ባይ የማድረግ  የሴራ ምኞት

በአስተዳደር ስያሜ ወጥ እና ቀጣይነት ያለዉ ስያሜ እና ሁሉን አቀፍ አሰራር ያለመከተል ዛሬ ላይ አገሪቷ ላለችበት ወቅታዊ ችግር ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረጋቸዉን እንገነዘባለን ለዚህም መነሻ  እንደሚከተለዉ ለማቅረብ ነዉ ፡፡

ይኸዉም ሰሞኑን በሰፊዉ ሲጉን የምንሰማዉ  በህገ መንግስት ዙሪያ ስለተደረገ ዉይይት እና ዉጤት እንዲሁም ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በመተከል ዞን ለዘመናት አስከ ቅርብ ቀናት በዜጎች ላይ ለይቶ ጥቃት የማድረስ ወንጀል መቆም ስላለበት አስተላለፉት ስለተባለዉ መመሪያ ነዉ ፡፡

ሁላችንም ቢሆን በራሳችን እና በአገራችን ጉዳይ አስተያየትም ሆነ መከላከል ለማድረግ የግድ ከዚያ ወይም ከዚህኛዉ መሆን የለብንም ለዚህም ለእኛ ማንም ከእኛ በላይ ሊናገር ሊመስክር አይችልም እና  ሁለቱን መሰረታዊ ሠሞነኛ አብይ ነጥቦች እንዲህ ልበል ፡፡

ህገ መንግስት ፡ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በህገ መንግስት ኅፀፅ ላይ በተደረገ ዉይይት  ማብራሪያ ሲሰጡ ህገ መንግስቱ  መሰረታዊ ችግር የለበትም የአፈፀፃም ችግር  እንጅ ይሉናል ፡፡ አስከትለዉ ደግሞ ጥቂት የህገ መንግስቱ ክፍሎች ማስተካከያ የሚሹ  ሊኖሩ ይችላሉ ይሉናል፡፡

እርሳቸዉ የአፈፃፀም ችግር ለሚሉት  እኮ ስራ ላይ በገቢር እና በምግባረ ገብነት ካልዋለ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን አላይ ነዉ የሚል እንዴት ከታዳሚዉ ይጥፋ ፡፡ ደግሞ ተግባር ላይ ካልዋለ እርሳቸዉ ለረጅም ዓመታት የህግ አዉጭ እና አስፈጻሚ አልነበሩም (የህዝብ እንደራሴ) እንዴት ለህዝብ እና አገር ጥቅም አዋሉት/ እንዴት ሰሩበት ፡፡

አወያይ እና የህግ ባለሙያ መድረክ መሪ ህገ መንግስቱ ከጅምር ህዝባዊ መሰረት እና ቅቡልነት እንዳልበረዉ እንዲያዉም አግላይ እና ፈንጋይ ነበር እያሉን ፕ/ ር  ዝም በሉ እኔ ልናገር አዉቃለሁ ሲሉ እርሳቸዉን ተናገር በከንፈሬ ፤ ተቀመጥ በወንበሬ ያላቸዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ብሶት ከማድመጥ እና ከማስተጋባት እኔ አዉቃለሁ ማለታቸዉ ያልነበረዉን ነበር ፤የነበረዉን እንዳልነበር ላለመሆኑ አላስረዱንም ፡፡ ለማንኛዉም ህዝብ እንዳይታዘብ ለአገር እና ወገን እዉነቱ የሚነገርበት የንስሃ ጊዜ ላይ መሆናችንን ሁላችንም ልብ እንበል፡፡

የመተከል አስተዳደር ህዝብ ወይም ኗሪ ለዓመታት ከፀረ ህዝብ እና አገር ጥቃት እራሱን ለመከላከል መደራጀት እንዳለበት ም/ል ጠ/ሚ/ ደመቀ የስራ ትዕዛዝ ለሚመለከተወዉ የመንግስት አካል መስጠታቸዉ አገር እና ህዝብ ከጥቃት እና ዉድቀት ለመከላከል ወሳኝ እና ወቅታዊ አማራጭ መሆኑን ብዙ ኢትዮጵያዉያንን የሚያስደስት ሲሆን ከዚህ በተቃራኒ ህዝብ እጅ ተወርች ታስሮ እንደፈለጉ ንብረቱን የሚዘርፉት፣  የሚነዱት፣ የሚያስሩት፣ የሚያፍኑት እና የሚገድሉት  ትልቅ ድንጋጤ የፈጠረባቸዉ መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃሳብ በጣም የዘገየ እና በመንግስትም ዳተኝነት ይስተዋላል ካልተባለ በቀር  የማዕከላዊ እና የአካባቢ መንግስት የህዝብ፣ ዜጎችን እና የአገር ደህነትን እና አንድነትን በተደጋጋሚ አደጋ ላይ በሚጥል ማዕበል ዉስጥ ሆኖ ምንም ማድረግ ካልቻለ ይህ ከስዉር ተልዕኮ ወይም አቅም ማጣት ሌላ ትርጉም ሊሠጠዉ አይገባም ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ የመንግስት አካሄድ ሚዛን የጠበቀ እና ፍትሃዊ የሆነ የኃይል ዝግጅት እና አሰላለፍ፣ የፖለቲካ ስልጣን ተሳትፎ፣የመኖሪያ አካባቢ የልማት እና አገልግሎት አጠቃቀም ፣ብሄራዊ ዕኩልነት በሠዉነት፣በዜግነት እና በስራ ብቃት……..የመሳሰሉት ቀድሞ ቢሆን ኖሮ ይህ ለዓመታት የደረሰ የህዝብ ዕልቂት እና የብሄራዊ አንድነት እና ደህንነት ስጋት እዚህ ባልደረሰ ነበር ፡፡

ምክትል ጠ/ሚኒስቴር  ህዝቡ እራሱን፣ አካባቢዉን እና አገሩን ከሩቅ እና ከቅርብ ወዳጅ መሰል ጠላት ለመከላከል ዘብ ይቁም ማለታቸዉ ለእኔ ቢመሽም  አገርን ከጥፋት ፤ህዝብን ከሞት ለመታደግ ብቸኛ እና ወቅታዊ አማራጭ በመሆኑ አበጁ የሚያስብል በመሆኑ ሁሉም አገሩን ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚጠብቀዉ እና የሚያደንቀዉ ሀሳብ እና ተግባር ነዉ ፡፡

ለአገር አንድነት ፣ለዜጎች ክብር እና ደህንነት ዋስትና ለማረጋገጥ ሲባል ለዓመታት የመጣንበት እና አሁን የደረስንበት የግፍ እና የሞት ገድል ጎዳና ተጨፈኑ እናሞኛችሁ   ሙት ገዳይ  በሆድ የተፀነሰ እና የተጠነሰሰ  የበታችነት ስሜት የወለደዉ የጥላቻ እና ብቀላ ጉዞ  መግታት ራስን ከብሄራዊ ደህንነት እና አገር አንድነት ጋር የመከላከል አካል ሆኖ የሚቆጠር ቅዱስ እና ተራማጅ ተግባረ -ሃሳብ መሆን አለበት  ፡፡  

ማላጅ

እናት አገር ምንጊዜም ትኑር

2 Comments

 1. ከመቼውም በላይ ርብርብ በሁሉም መስክ ተገቢ ነው።
  ከተሜ ለገበሬ መድረስ ግዴታው ነው።
  iopia.om/en

 2. We middle aged and older Ethiopians must close our eyes and get fooled inorder to prevent a civil war. Otherwise if we the middle aged and older Ethiopians keep our eyes open and resist being fooled the young and the youth will surely engage an endless civil war, that is why it is so important for all the middle aged and older aged Ethiopians to lead by example , we need to show the youth how to get fooled by keeping our eyes closed . If we do not do it then the youth will for sure start an all out civil war with no quick end since there will be no winner.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.