ይድረስ ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አማካሪዎችና በአጠገባቸው ላላችሁ ሙህራኖች በሙሉ – ከታምራት ይገዙ

abiy ይድረስ ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አማካሪዎችና በአጠገባቸው ላላችሁ ሙህራኖች በሙሉ   ከታምራት ይገዙመንደርደሪያ

እስራኤል ሁሉ ያነግሡት ዘንድ ወደ ሴኬም መጥተው ነበርና ሮባዓም ወደ ሴኬም ሄደ። እንዲህም ሆነ የናባጥ ልጅ ኢዮራዓም ይህን በሰማ ጊዜ እርሱም ከንጉሡ ከሰሎሞን ፊት ኮብልሎ በግብጽ ተቀምጦ ነበርና በግብጽም ሳለ ልከው ጠርተውት ነበርና ኢዮርባዓምና የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ መጥተው ለሮባዓም አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር አሁንም አንተ ጽኑውን የአባትህን አገዛዝ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቃልልልን እኛም እንገዛልሃለን ብለው ተናገሩት። እርሱም ሂዱ በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመለሱ አላቸው። ሕዝቡም ሄደ

yy ይድረስ ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አማካሪዎችና በአጠገባቸው ላላችሁ ሙህራኖች በሙሉ   ከታምራት ይገዙንጉሡም ሮባዓም ለዚህ ሕዝብ እመለስለት ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ። እነርሱም ለዚህ ሕዝብ አሁን ባሪያ ብትሆን ብትገዛላቸው መልስህም በገርነት ብትነግራቸው በዘመኑ ሁሉ ባሪያዎች ይሆኑልሃል ብለው ተናገሩት።

እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ምክር ትቶ ክረርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ። እርሱም አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቃልልልን ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? አላቸው።

ከእርሱም ጋር ያደጉት ብላቴኖች አባትህ ቀንበር አክብዶብናል አንተ ግን አቅልልልን ለሚሉህ ሕዝብ ታናሺቱ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች። አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሗል እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለው አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሗል እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችሗለሁ በላቸው ብለው ተናገሩት።

ንጉሱም በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመለሱ ብሎ እንደ ተናገረ ኢዮርባአምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮባአም መጡ። ንጉሱም ሽማግሌዎች የመከሩትን ትቶ ለሕዝቡ ጽኑ ምላሽ መለሰላቸው። እንደ ብላቲኖችም ምክር አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሗል እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለው አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሗል እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችሗለሁ ብሎ ተናገራቸው። (መጽሐፈ ነገስት ቀዳማዊ 12:1-15)

እናንት በጠ/ሚ አብይ ፊት እና ሗላ ግራና ቀኝ የምትቀመጡ የጠ/ሚ አብይ አማካሪዎች እራሳችሁን የምታዩት ንጉስ ሰሎሞን በህይወት ሳለ በፊቱ እንደሚቆሙት ሽማግሌዎች ነው? ወይስ ከንጉስ ሮባዓም ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ነው እናንተነታችሁን የምታገኙት? እባካቹን መልሱልኝ። ይህንን ጥያቄ የመጠይቃችሁ በሀገራችን የእለት ተለት ጉዞ ላይ ሆድ እንደባሰው አንድ ኢትዮጵያዊ ሆኜ ነው የምጠይቃችሁ። እንደ እውነቱ ከሆነ ስም መጥራቱ ይቅርና  ጠ/ሚ አብይን ከአጠገቡ ሆናችሁ ለምታማክሩት ሁሉ ያሌኝ ሌላው ጥያቄ ለጠ/ሚ አብይ የምታቀርቡት ዘገባና ምከረ ሀሳብ እርሳቸው መስማት የሚፈልጉትን ባቻ ነው ወይስ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለውንና የሚያሰማውን ብሶቱንና ጭንቀቱን ነው? እስቲ ለሂሊናችሁ ብላችሁ ለራሳችሁ መልሱልኝ።

እናንት በተለያየ የእውቀት ደረጃ፤ በተለያየ እድሜ፤ በተለያየ የእድሜ ተመክሮ የሚትገኙ አማካሪዎች አገራችን (አገራችሁ) ከድጡ ወደ ማጡ ስትገባ አይታያችሁም ማለት ነውን? ለምሳሌ ጥቅምት 12 ቀን 2012ዓ.ም. አቶ ጃዋር መሀመድ በፀጥታ ሀይሎች ተከብብሁ በሚል ስበብ በተፈጠረ ሁከት ከ86 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ጠ/ሚ አብይ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ቤተሰቦችና ለመላ ኢትዮጵያዊ የማጽናኛ መለክት እንዲያደርጉ ምክረ ሃሳባችሁን ለግሳችሁ ይሆን ወይስ ማን ምን ያመጣል ብላችሁ አለፋችሁ? በድጋሚ ከስምንት ወራት በኃላም ደግሞ ሰኔ 23 እና 24 2012ዓ.ም. የሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከ200 በላይ ዜጎች ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ የአደባባይ ሚስጥር ነበር በዚህ ግዜ ምን ዓይነት መክረ ሀሳብ ለጠ/ሚ አብይ አቀረባችሁ? በዓመቱ የመጨረሻ ወር  ጳጉሜ 1 እና ሁለት ቀን 2012ዓ.ም. በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ160 በላይ የአማራ እና የአገው ተወላጆች  አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ እንደተገደሉም ተዘግቦ አይተናል ሰምተናል  ከጥቂት ቀናት በኃላም በዚህው ክልል በቤኒሻንጉል ጉምዝ በተመሳሳይ ሁኔታ መስከረም 14 ቀን 2013ዓ.ም. ከሃያ የሚበልጡ  አማራዎች በሌሊት ጥቃት እንደደረሰባቸው ሰምተናል ይህ ሁሉ ጥቃት ሲደርስ እናንት የጠ/ሚ አብይ አማካሪዎች እርሳቸው ጠ/ሚ አብይ በአካል በቦታው ሂደው ተጠቂዎችን ሊጎበኙ፣ ሊያፅናኑ እና እርዳታ እንዲደርጉላቸው ምክረ ሃሳብ አቅርባችሁ ይሆን? ለመላው የኢትዮጵያም ህዝብ  የተሰማቸውን ሀዘን መግለፅ፣ ማፅናኛ መልዕክት እንዲያስተላልፉ የየራሳችሁን የሂሊና ግዳጅ ተወታችዋልን? እኔ በበኩሌ ምንም ዓይነት የማስተዛዘኛ፣ የማፅናኛ ንግግር ከጠ/ሚ አብይ አንደበት አልሰማሁም። ይህ ለተጠቂዎቹም ሆነ ለመላው ኢትዮጵያዊ ህዝብ ምን አይነት መልዕክት ሊሰጥ እንደሚችል እናንተ አማካሪዎች ልብ ብላችሁት ይሆንን

በዚህ ሳምንት የኤርትራው ፕ/ት ኢሳያስ አፈወሪቂ ለሦስት ቀናት የስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ በመጡበት ግዜ ከጠ/ሚ አበይ ጋር ጅማ ላይ በመገኘት ቡና ሲለቅሙና በሌላው በኩል ደሞ የአባይን ግድብ ሲጎበኙ ነበር በሌላ አቅጣጫ ደሞ የአገራችን ገበሬ በበሬ አርሶ የደረሰለት እሸት በአንበጣ መንጋ ሲከስም ተመልክቻለው። ነገ ተነገ ወዲያ ይህ ደሃ ገበሬና ልጆቹ የሚበሉት የሚቀምሱት አጥተው ወደ ከተማ ይሰደዳሉ አሊያም አገር ጥለው ይጠፋሉ። እናንት የጠ/ሚ አማካሪዎችና በአጠገባችሁ ያላችሁ ሙህራኖች እሲቲ ከሒሊናችሁ መልሱልኝ ቡና መልቀም ይቀድማል ወይስ ከተለያዩ የዓለም መንግስታት የአንበጣ መከላከያ እርዳታ ጠይቆ እነዚህ ደሀ ገበሬዎችንና ቤተሰቦቻችውን መታደግ ይቀድማል?  አጼ ሐይለስላሴ የወሎ ረሀብ ከአለም መንግስታት ደብቀው ልደታቸውን ለማክበር ደፋ ቀና ይሉ ነበር ይባላል በጠ/ሚ አብይ ደሞ የአገራችን ገበሬ በአንበጣ መንጋ በሚታመስበት ወቅት እርሳቸው ደሞ ለቡና ለቀማ ጅማ ይሄዳሉ ታሪክ እራሷን ልትደግም ይሆ?   

በማስከትል አረ ተው አረ ተው በምታምኑት አምነት በምታምኑት አምላክ ብላችሁ እናት የጠ/ሚ አማካሪዎችና በአጠገባቸው ያላችሁ ሙህራኖች አገራችንን ኢትዮጵያን በምክራችሁ ታደጓት።  ጠ/ሚ አብይ አኔ ያልኩት ባቻ ካልሆነ የሚሉ መሪ ከሆኑ እናንተ  ከሒሊናችሁ ጋር አውጥታችሁና አውርዳችሁ “ምከረው ምከርው እምቢ ካለ…..…”  የሚለውን የአባቶች አባባል አስረግጣችሁ በመንገር ከአጠገባቸው ዝሮ በማለት ከሒሊና ወቀሳና ከሒሊና ተጠያቂነት እንዲሁም ከታሪክና ከትውልድ ተጠያቂነት እራሳችሁን ማግለል ነው።

በመጨረሻም በደርግ ዘመን አንድ ሰማቸውን መጥራት የማያስፈልግ ሚንስቴር ከፕ/ት መንግስቱ ሀ/ማርያም ጋር አንድ የእርሻ ቦታ እየጎበኙ ሳለ ፕ/ት መንግስቱ በከስክስ ጫማቸው መሬቱን ቆፈር ቆፈር በማድረግ ይህ ቦታ ለእራሻ ተስማሚ አይደለም ሲሉ አብሮዎቸው ከሄዱት ሚንስትሮች ውስጥ አንዱ በእጃቸው አፈሩን አፈስ አድርገ በአፍንጫቸው እያሸተቱ ጓድ ፕ/ት መንግስቱ ትክክል ናቸው ይህ ቦታ ለእርሻ አይሆንም አሉ እየተባለ በአሁኑ ሰዓት ድረስ የወቀሳሉ የናንተስ የጠ/ሚ አብይ አማካሪዎችና በአጠገባቸው ያላችሁ ሙህራኖች አጣ ፋንታ እንዴት ነው? በሚል ብሶቴን በመጠይቅ የዛሬውን ጹሁፊን ላብቃ።

አገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን  ቸሩ ፈጣሪያችን ይታደጋቸው !!

1 Comment

  1. Abiy Ahmed wanted to visit the desert locust infested parts in person because he felt it is his duty to show up in person and discuss the desert locust infestations problem with the affected farmers. Isayas was scheduled to travel with Abiy to the locust affected areas in Ethiopia, so Isayas can have the chance to evaluate the situation and figure out what kind of strategies Isayas would have suggested to combat the locust .Unfortunately the locust infestation was too much the locusts took down two airplanes that were flying to spray pesticides on the locusts , making it risky for these two leaders safety to travel to areas where locusts managed to take down not one but two airplanes , so the scheduled visit to these areas got canceled with Isayas flying to GERD then the other areas while Abiy went to Arsi farm then they both went to Jimma area because they already had scheduled plans they just changed where they were going. Then the Prime Minister Abiy Ahmed’s office, Press Secretariat Nigussu Tilahun announced that Ethiopians should practice eating the locusts as certain cultures around the world do eat desert locusts.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.