በሕገ መንግስቱ ላይ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ጊዜ መገደብ አለበት” ተባለ

223 161230 121615405 375578057190197 7239331214557221094 o 700x400 በሕገ መንግስቱ ላይ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ጊዜ መገደብ አለበት” ተባለአሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግስት አንቀጽ 70 ንዑስ አንቀጽ አራት የፕሬዚዳንት የሥራ ዘመን ስድስት ዓመት እንደሆነና አንድ ሰው ከሁለት ጊዜ በላይ ለፕሬዚዳንትነት ሊመረጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 72 በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ዘመን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን ነው የሚል ሲሆን የመመረጥ ገደብን አልጣለም። አሁን ላይ ሕገ መንግስትን በተመለከቱ ውይይቶችና መድረኮች ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመመረጥ ገደብ ሊቀመጥለት እንደሚገባ እየተገለጸ ነው፡፡

ለአብነትም ዛሬ ጥቅምት 05 ቀን 2013 ዓ.ም. በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አዘጋጅነት ፣ በተካሄደ ውይይት ላይ ጉዳዩ ተነስቶ ነበር፡፡ በዚሁ ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራሮች በተገኙበት “ሕግ መንግስት እና ሕገ መንግስታዊነት በኢትዮጵያ” የሚል ጽሑፍ ቀርቧል፡፡ አቅራቢው አቶ ሱልጣን ቃሲም የኢትዮጵያ ሕገመንግስት በ1987 ዓ.ም ሲረቅና ሲጸድቅ ከሂደቱ ጀምሮ ሁሉን አቀፍ እንዳልነበረ ገልጸዋል፡፡

223 161402 ekxfnqtxyamgvfp በሕገ መንግስቱ ላይ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ጊዜ መገደብ አለበት” ተባለ

አሁን የፈረሰውና የቀድሞው ገዥ ፓርቲ ኢሕአዴግ ፣ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ በሕገ መንግስቱ ማርቀቅና ማጽደቅ ሂደት ላይ በርካቶች ተሳትፈዋል የሚል ሃሳብ ሲያቀርብ ቢቆይም ይህ ግን በብዙዎች ይተቻል፡፡

ጥናት አቅራቢውም ሕገ መንግስቱ በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ተቀባይነት እንደሌለውና አልተወከልንም የሚሉ ሃሎች እንዳሉ ይገልጻሉ፡፡ በተለይም ሰፋ ያለ የሕዝብ ድጋፍ የነበራቸው የፖለቲካ ድርጅቶችም በዚህ የሕገ መንግስት ሂደት ላይ ተሳታፊ እንዳልነበሩ ገልጸዋል፡፡

ሕገ መንግስቱ የኢትዮጵያን ርዕሰ ብሔር የስልጣን ጊዜ እንደገደበው ሁሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም የመመረጥ ሁኔታ ገደብ በግልጽ ማስቀመጥ ነበረበትም ነው ያሉት፡፡

ገዢው ፓርቲ የመንግስትን ሚና ተክቶ እየሰራ እንደሆነ ያነሱት አቶ ሱልጣን ይህ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ እየታየ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ ይሁን እንጂ መንግስት እና ፓርቲ መለያየት አለባቸው ይላሉ፡፡

223 161436 ekxe90exyaalvcj በሕገ መንግስቱ ላይ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ጊዜ መገደብ አለበት” ተባለ

ከዚህ ባለፈም በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 62 ንዑስ አንቀጽ 1 የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ መንግስቱን የመተርጎም ሥልጣን እንደሚኖረው ይገልጻል፡፡ ጥናት አቅራቢው ግን የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፖለቲካ ተቋም እንደሆነና ሕገ መንግስቱን ለመተርጎም ሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ሊቋቋም እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

የሕገ መንግስቶች አለመረጋጋት በሀገሪቱ እንዳለ ገልጸው አፍርሶ የመገንባት ባህልን ማስቀረት አስፈላጊ እንደሆነ አንስተዋል አቶ ሱልጣን ቃሲም፡፡

የጥናታዊ ጹሑፉ አወያይ እና የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር እንዲሁም የፖሊሲ ጥናት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ሕገ መንግስቱ ትልቁ ችግር አለመተግበሩ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ የሕገ መንግስቱን የሚስተካከሉ መጠነኛ ነገሮችን በማስተካከል በትክክል ስራ ላይ ማዋል ቢቻል ብዙ ለውጥ እንደሚመጣ አንስተዋል፡፡

223 161556 ekxe8aixyaamd7u በሕገ መንግስቱ ላይ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ጊዜ መገደብ አለበት” ተባለ

ከዚህ በፊት የአማራ ክልል ምክር ቤት አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገ-መንግስቱ እንዲሻሻል የጠየቀ ሲሆን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የተለያዩ አካላትም ሕገ መንግስቱ እንዲሻሻል መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ ምሁራንና ፖለቲከኞች በአንድ ወገን ሕገ መንግስቱ ይሻሻል በሌላ ወገን ደግሞ መሻሻል የለበትም በሚል ክርክሮች እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

አል-ዐይን

2 Comments

 1. የሰፋሪ ጣቢያ ነፍጠኛ በመተከል ተነሳ
  ምክትል ደመቀ ጠቅላይ አንበሳው ስላገሳ

  አዲስ አበቤ ተወረወረ ዘብጥያ
  ደግሞ ሊሰበር በአዳነች ሚሊሽያ

  ሽመልስማ ዝልዘላውን አጧጡፎት
  ነፍጠኛ መሰባበሩን ለአዳነች ትቶት

  እዲስ አበቤ ዳግም አልሰበርም ባለ
  ትምክህትኛ አሸባሪ ተባለ

  የመተከል ፋኖ ሲያቅራራ እንስቶ ነፍጥ
  አዲስ አበቤም ተከተል ውጩን ትተህ ውስጥ ውስጡን አጣፍጥ

  እየሞትን ማን ሊሰማት
  እርባ ሚሊየን ዘርፋ ያነሳት

  አዲስ አበቤ ተባዛ ንፋ እምቢልታ
  እንደ መተከል አስበርግግ በእሩምታ

  እናስመስክር ከቆሼ እስከ ቦሌ ብቸኝነታችንን
  በህብረት ወልውለን የሺ ግምት ባሩድ ምንሽራችንን

 2. Also should be restricted such as the amounts of times the PM goes without:
  1)giving a press conference and appointing a press secretariat for the PM’s office
  2)apointing ministers for his ministries
  3)holding a national election
  4)holding public rallies
  5)taking appropriate actions to certain states who become DeFacto States
  6)adhereing to international agreements such as the Algiers agreement.
  7) Holding statehood referendums for those who asked for it.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.