ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሰረ

temeየፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ እና የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ምስጋን ዝናቤ ከቢሮአቸው በፖሊስ ተወስደው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መታሰራቸውን የተመስገን ደሳለኝ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጧል።
ታሪኩ ደሳለኝ ለአሜርካ ድምፅ እንደገለፀው፤ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የፖሊስ ደንብ ልብስየለበሱ እና ሲቪሎች ወደ መጽሔቱ ቢሮ ከደረሱ በኋላ ዋና አዘጋጁን አቶ ምስጋን ዝናቤንከያዙ በኋላ ወደ ተመስገን ደሳለኝ ስልክ እንዲደወል አድርገዋል።
ተመስገንን እንደሚፈልጉት እና ወደ ቢሮ እንዲመጣ ከነገሩት በኋላ፤ ቢሮ ሲደርስሁለቱንም ይዘዋቸው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደወሰዷቸው ተናግሯል።
ማምሻውን አዲስ አበባ ፖሊስ ሄደው መታሰራቸውን ከሩቁ እንዳረጋገጠም ተናግሯል።በጉዳዩ ላይ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።በነገው ዕለት ዘርዝር ያለ መረጃ ይዘን እንመለሳለን። (#VOAAMHARIC)
———-
ተመስገንን በአፋጣኝ ፍቱት!
የወ/ሮ አዳነችን ስም በሃሰት አጥፍተሃል በሚል ተመስጌን ደሳለኝ ከአንድ ሌላ የሥራ ባልደረባው ጋር ዛሬ ከቢሮው በፖሊሶች ተከቦ መወሰዱን እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መታሰሩን ቤተሰቦቹ አረጋግጠዋል። በመጀመሪያ በስም ማጥፋት ወንጀል የተጠረጠረን ጋዜጠኛ ማሰር አግባብ ነው ወይ። ስሜ ጠፋ የሚለው አካል አቤቱታውን አቅርቦ ክስ እንዲመሰረትበት እና ፍርድ ቤት ቀርቦ ምላሽ እንዲሰጥ ይደረጋል እንጂ የሚታሰረው በምን አግባብ ነው? ፖሊስ ጋዜጠኛውን የሚያስረው ምን ሊያጣራ እና ምን ሊመረምር ነው? በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰበሰብ ተጨማሪ ማስረጃ እስከሌለ ድረስ እና እትመቱን እንደ ማስረጃ በመውሰድ ስም መጥፋቱን ለፍርድ ቤት ማሳየት እየተቻለ የእስሩ አላማ ምን ለማግኘት ነው?
ይህ አይነቱ በጋዜጠኞች እና በመብት ተሟጋቾች ላይ የሚደረግ እሥር የታየውን ሃሳብን የመግለጽ እና የሚዲያ ነጻነት ጭላንጭል ዳግም ሊያዳፍነው ይችላል።
በቅርቡ አንድ የመከላከያ ሹም የሰራዊቱን ሹማምንት በስም ጠርቶ መተቸት እንደማይቻል በመንግስት ሚዲያ ሲገልጹ ሰምቼ ጉዳዩ አሳስቦኝ ነበር። እነዚህ አካሄዶች የሚዲያን ነጻነት እና ሃሳብን የመግለጽ መብትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው። መንግስት በአፋጣኝ በእንደዚህ ያሉ እሳቤዎች ላይ እርማት ሊያደርግ ይገባል። ተመስጌን ደሳለኝ እና ባልደረባውንም በአፋጣኝ ሊፈታቸው ይገባል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.