‹‹የአውሮፓ ፓርላማ የሳውዲ አረቢያ መንግስትን ስብዓዊ መብቶች ጥሰትን አወገዙ!!! ፈቅደው የሞቱትን ዳግም መግደል አይቻልም!!!›› – ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

et52‹‹ በሳውዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ የሚፈፀም ኢሰብአዊ ግፍ ይቁም!!!››

ከውኃ አጥማቂው ወደ እሳት አጥማቂው ዘመን!!!

‹‹ ፈቅደው የሞቱትን ዳግም መግደል አይቻልም!!!››1

‹‹የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ከአፍሪካና እስያ ክፍለአህጉር በመጡ ስድስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሽህ የስደተኛ የጉልበት ሠራተኞች  በቤት ውስጥ ሠራተኛነትና በህንፃና በመንገድ  አድካሚ ሥራ ተሠማርተው ይገኛሉ፡፡  የሰደተኞቹ ቁጥር  የገልፍ ሃገሮችን ህዝብ   ሃያ በመቶ ይሸፍናል፡፡ ጋዜጠኞች በምርመራ እንዳረጋገጡት የስደተኞቹ ህይወት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በምግብ እጥረት ችግር፣ አየር በማይገባበት ክፍሎች ውስጥ በመኖር፣  ሽንት ቤቶቹ ሞልተው በሚገነፍሉበት ሥፍራና  የሞቱ ሰዎች ሬሳ በተኙበት ቦታ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ አንድ ወጣት ራሱን ከግድግዳ ላይ ሰቅሎ  ይስተዋላል፡፡ ሌሎች ሰዎች ለሰንዴ ቴሌግራፍ ጋዜጠኞች ራሱን ነው የገደለው ይባላል ያሉበት ሁኔታ ለውጥ እስከሌለው ድረስ ያው ነው፡፡››  Saudi Arabia has long been reliant on migrant labour from Africa and Asia. In June 2019, an estimated 6.6m foreign workers made up about 20 per cent of the Gulf nation’s population, most occupying low paid and often physically arduous jobs. The migrants work mainly in construction and domestic roles that Saudi nationals prefer not to do themselves. Investigations by the Telegraph in August revealed hundreds of men, scrawny from lack of nutrition, being kept in small, airless rooms where toilets overflowed and dead bodies lay. The body of a young man who killed himself hung from one wall. Other men told Sunday Telegraph that they were considering suicide if their conditions remain unchanged.2

የአውሮፓ ፓርላማ የሳውዲ አረቢያ መንግስትን በስብዓዊ መብቶች ጥሰትን አወገዙ!!!

የሳውዲ አረቢያ መንግስት በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ የአፍሪካ ስደተኞችን በባሪያ ፈንጋይ በመሰለ በኮቪድ ቨይረስ ወረርሽኝ እስርቤት በማጎራቸው፣ የአውሮፓ ፓርላማ የሳውዲ አረቢያ መንግስትን በስብዓዊ መብቶች ጥሰት በጥብቅ አውግዘዋል የቴሌግራፍ ምርመራ ቡድን አስከፊውን የእስር ሁኔታ አጋልጠዋል”፡፡ የሳውዲ አረቢ ንጉሳዊ ሥርዓት  እንዳይጋለጥ ያደረገው በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወንዶች፣ ሴቶችና ህፃናት በእስር ቤት በግዳጅ ታጉረው የሚኖሩበት እዛው የሚበሉበት፣ የሚጠጡበት፣ የሚተኙበትና የሚፀዳዱበት ሁኔታ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን የሚያስፋፋ  መሆኑን ያጋለጡት ተደብቆ በገባ ሞባይል ተቀርፆ በተላከ መልዕክት ነበር፡፡ እስረኛ ስደተኞቹ በድርቀት በሽታ፣ በፀሐይ የበርሃ ንዳድ፣ በርሃብ አለንጋ እንደተጠቁ ታውቆል፡፡ ሌሎች ስደተኞች ላይ የደረሰ ድብደባና አሰቃቂ ግርፋት ጠባሳ በፎቶግራፎች ተነስቶ በመላክ ተጋልጦል፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ተስፋ በመቁረጥ በድርቀት በሽታ፣ በበርሃ ንዳድ፣ ርሃብ ቸነፈር የተነሳ ራሳቸውን እንደሚገሉ በተላኩት ፎቶግራፎቹ መረጃ ላይ ተስተውሎል፡፡ የገልፉ ንጉሥዊ ቤተሰብ በዓለም አቀፍ የአውሮፓ መንግሥታትና ህብረተስብ ሲወገዙ ቆይቶም  የአውሮፓ ፓርላማ የሳውዲ አረቢያ መንግስትን አልጋ ወራሽ ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን በስብዓዊ መብቶች ጥሰትን አወግዞ መግለጫ አውጥቶል፡፡›› አምኒስቲ ኢንተርናሽናል ባጋለጠው መረጃ መሠረት ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች ኢስብዓዊ ግርፋት በኤሌትሪክ ከፍተኛ ንዝረት በአከላታቸው ላይ በመጥበስ ስደተኛ እስረኞችን አሰቃይተዋል፣ እርጉዝ ሴቶች መታሰራቸውና በዚህም የተነሳ አምስት ህፃናት መሞትና የተወለደ ህፃን እንደሞተ አጋልጠዋል፡፡ ‹‹The vote to censure the kingdom comes a month after an investigation by this newspaper found thousands of men, women and children locked up to stop the spread of coronavirus were being forced to sleep and eat in their own faeces. Harrowing footage captured on smuggled phones by the migrants in August shows hundreds of emaciated Ethiopian men at various stages of dehydration, heatstroke, and starvation. Other photos show migrants with scars and wounds from beatings and torture and disfiguring skin infections. Some images, too graphic to publish, show the bodies of migrants who appear to have died from dehydration, disease or suicide. The condemnation is a major blow to the Gulf kingdom’s international standing.  The resolution was passed by members of the European Parliament (MEPs) in Brussels on Thursday afternoon, after a fiery debate where criticism rained down on the Gulf kingdom from across the European political spectrum.›› ….. Last week, a report by the rights group Amnesty International said that inmates were subjected to electric shock torture and that pregnant women were also being detained in woeful conditions. The rights group said they had heard about the deaths of at least five children and newborns.>> 3 የኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ መሪ ዶክተር ዐብይ አህመድ ሰለቸው መሰል፣  ስለ ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ምንም ያለው ነገር የለም፡፡ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ 400,000 (አራት መቶ ሽህ) ስደተኞች ከሳውዲ ረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ሃገራቸው ተመልሰው ነበር ከነዚህ ውስጥ 320000 (ሦስት መቶ ሃያ ሽህ) 80 በመቶ ወደ ሳውዲ አረቢያ ዳግም  ተሰደዎል፡፡ ለምን? ለምን?

ኢትዮጵያ በዘር የተደራጁ የጦር አበጋዞች መንግሥታት የተፈለፈሉባት አገር ናት፣ በየክልሉ የዘር መታወቂያ የሚሠጡ የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች በየዘርህ ያደራጁሃል፣ በየክልሉ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ፈጥረው ህዝቡን በዘር ከፋፍለው በሠላም እንዳይኖር  ካደረጉት ሦስት አስርቶች ተቆጥሮል፡፡ ለዚህ ነው ወጣቶች አገራቸውን ጥለው የሚሠደዱት፣ በርሃ አቆርጠው፣ ውቅያኖስ ሰንጥቀው  ነፋሳቸውን ሸጠው ቀን ከሌት ይጎዛሉ፣ ወጣቶቹ  የሞት ፍርኃትን ድል ነስተው ‹‹ ፈቅደው የሞቱትን ዳግም መግደል አይቻልም!!!››

ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከሃምሳ ሦስት እስር ቤቶች በላይ አሉ፣ ኢትዮጵያዊያን በሁሉም እስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ በዛም ውስጥ ይኖራሉ፡፡አቶ ያሲን ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ኮርፖሬሽን እንዳሉት ለምሳሌ አል ሱማይሲ እስር ቤት ከጅዳ ስልሳ ኪሎሜትር ይርቃል በዛ 16000 (አስራ ስድስት ሽህ) ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ይገኛሉ፡፡ ቴሌግራፊ ጋዜጠኞች ከስደተኞቹ ጋር በስውር በተገኛኙት መሠረት አል ሱማይሲ እና ጃዛን የወደብ ከተማ የመን ድንበር አካባቢ የሚገኝ እስርቤት ሲሆን ምንያህል እስረኞች እንዳሉ ግን ለማወቅ አልተቻለም፡፡  በሳውዲ አረቢ ያሉትን እስር ቤቶች እንደምታስመረምር ለተባበሩት መንግስታት አስታውቃለች፡፡   “Jeddah has over 53 prisons. Ethiopians are held in every one of them,” Mr Yassin told the Ethiopian Broadcasting Corporation. “If you take the one at Al Shumaisi…located around 60km from Jeddah, there are about 16,000 Ethiopians kept in the prison and the holding cells.”  … Last month, the Telegraph was able to communicate with migrants at the centres at both Al Shumasi and Jazan, a port city on the border in Yemen. It is unclear how many people are being held at the detention centre at Jazan…. United Nations, Saudi Arabia said it would investigate all of its detention centres.4

‹‹የነገ ሞች ዛሬ አስክሬን ይሸኛል!!!››

መንግሥት መር ሽብርተኛነት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው እንዲሁም ከቦታ ቦታ በሃገሪቱ ውስጥ ተዘዋውሮ መሥራት መብቶች አሉት የሚለውን የተቀደሰ ሃሳብ ኦህዴድ ብልጽግና ፓርቲ በተግባር ማሳያት አልቻለም፡፡ በሃገሪቱ ዜጎችን እንደ ልጅና ሌላውን የእንጀራ ልጅ በማድረግ አድሎ የሚፈፅሙ መሪዎች በታሪክ ተጠያቂ ናቸው፡፡ በህወሓትኢህአዴግ ዘመንና ቀጥሎም በኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት የሚመራ መንግሥት መር ሽብርተኛነት ላለፉት ሠላሳ አመታት ሃገሪቱ አስተናግዳለች፣ በመንግሥታዊ መዋቅሮቹ በመጠቀም፣ በመከላከያ ሠራዊቱ፣ ፖሊስ ኃይሉ፣ በጸጥታና ደህንነት ድርጅቱ በጋራ የተቀነባበረ የሽብርተኛነት ድርጊት  የተፈፀመ የዘርና የኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) ሽሽት ወጣቶች አገራቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደዱ፡፡ ህወሓትና ብልፅግና የመሰሉ ወንጀለኛ ሽብርተኞ ቡድኖች በወንጀል ድርጊት ኃብትና ንብረት የሚዘርፉ ቡድኖች፣ በዕፅ ንግድ፣ በመሳሪያ ሽያጭ፣ በሰዎች ዝውውር፣ በወሲብ ንግድ፣ በህጻናት ሽያጭና ህፃናትን በወታደርነት በመመልመል ፣ በገንዘብ ዝውውር በህገ ወጥ መንገድ የተሰማሩ ወንጀለኛ ሽብርተኛ ብድኖች  በሚስጢርና በይፋ ተደራጅተው ይገኛሉ፡፡

የህክምና ዶክተሮች ሥራ አጥነት፡- በሃገሪቱ ስር የሰደደው የሥራ አጥነት ችግር የተመዘገቡ ሠላሳ ሚሊዮን ወጣቶች በአገራቸው ውስጥ የሥራ ዕድል ተፈጥሮ መሥራት ባለመቻላቸው ስደትን መርጠዋል፡፡ በኢትዮጵያ 65 በመቶ ከሚሆነው የህዝብ ቁጥር ወጣቶች ናቸው፡፡ በዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት ዘመን ደግሞ በህክምና ትምህርት ተምረው በዶክተርነት የተመረቁ ከአስር ሽህ የሚበልጡ ሃኪሞች በተለይ በአማራ ክልልና በአዲስ አበባ አስተዳደር እንዲሁም በሌሎች የዘር ክልሎች የተያዘ ባጀት ስለሌለ ተቀጥረው መሥራት አልቻሉም ሥራ ፈት ሆነው ከቆዩ አመታት አስቆጥረዋል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግና ኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ ባሉት ሰባት ሚሊዮን ፖለቲከኛ ካድሬዎች የሃገሪቱን መደበኛ በጀት ለፖለቲከኞች ከማዋል ሌላ ከፍተኛ የሃኪም እጥረት ባለበት ሃገር ዶክተሮችን አለመቅጠር የባሰ ድንቁርና የለም እንላለን፡፡ በተመራቂዎቹ ዶክተሮች ላይ የደረሰ ኢኮኖሚና የስነልቦና ቀውስ አስከትሎል፣ ለመኖር ሥራ ለመቀየር ተገደዋል፣ አንድ ዶክተር ለብዙ መቶ ሽህ ሰዎች በሚያክምበት ሃገር ሃኪሞች ሥራ ካጡ የ2013ዓ/ም የኢትዮጵያ መንግሥት 476 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ 133 ቢሊዩን ብር ለመደበኛ በጀት፣ 176 ቢሊዮን ለክልሎች ድጎማ፣ 160 ቢሊዮን ለካፒታል በጀት ፣ 6 ቢሊዮን ለዘላቅ ልማት እያሉ እንደ በሬ ቅርጫ ሲመድቡ ዐብይ አህመድ እንዳሉት ‹‹የዜጎች ህይወት ላይ የማመጣው ውጤት የማረሰርሰው ጉሮሮ የማስተምረው ጭንቅላት፣ ሥራ  የምሠጠው እጅ ቁጥር ብዛት የእኔን መሆን ውጤት ይለካል፡፡›› በአሉበት አፍዎ፣ ቃልዎን በልተው፣  ሰባት አመታት በህክምና ሣይንስ የተማሩ ዶክተሮችን አለመቅጠር የኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ ‹‹በቁሙ የሞተ፣ ካለ አይቆጠርም!!!›› ተብሎ ሊዘመርለት ይገባል ህወሓት/ኢህአዴግና ኦህዴድ ብልፅግና  ዜጎች የገደለ፣ ትውልድ የገደለ ሥርዓት ይሄን ችግር ካልቀረፈ ሊወገድ ይገባል እንላለን፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች  በአገራቸው መታረድ መሮቸው፣ የሥራ እድል አጥተው፣  ወገንና ዘመድ አጥተው ነው፣  በርሃ አቆርጠው፣ ውቅያኖስ ሠጥመው፣  ሞትን ተጋፍጠው ‹‹ፈቅደው የሞቱትን ዳግም መግደል አይቻልም!!!›› የምንለው ለዚህ ነው፡፡

 

የህክምና ዶክተሮች መቅጠር ያልቻለ መንግሥት ብልጽግና አያመጣም!!!
በሳውዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ የሚፈፀም ኢሰብአዊ ግፍ ይቆማል!!!
የአውሮፓ ፓርላማ ለኢትዮጵያ ስደተኞች ላደረገው ድጋፍ እናመሰግናለን!!!
የሻብያ የኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት  በኤርትራዊያን ሰደተኞች ህይወት ቀልዶል፡፡

 

ምንጭ፡-

1- የጹሑፉ ርዕስ ‹‹ፈቅደው የሞቱትን ዳግም መግደል አይቻልም!!! )ተዋህዶ ባልተቆረጠ ጥቃት ዐባይነህ ካሴ ርዕስ የተወሰደ

2- Ethiopian migrants detained in Saudi Arabia return home/Women and children land in capital after pressure on government to act/ByShola Lawal LAGOS, NIGERIA11 September 2020 •

3- EU Parliament condemns human rights abuses in Saudi migrant camps after Telegraph investigation/ByZecharias Zelalem and Will Brown, AFRICA CORRESPONDENT, NAIROBI8 October 2020 • /igrants trapped in Saudi Arabian detention centres CREDIT: The Telegraph

4-https://www.telegraph.co.uk/global-health/science-and-disease/16000-migrants-held-saudi-centres-ethiopian-official-reveals/

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.