ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር፤ ክቡራን የምክር ቤቱ አባላት – ከኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ

3433ቀን: 09.10.2020 (እንደ አውሮፓ አቆጣጠር )

ከኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ

ፍራንክፉርት ጀርመን

ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠ/ሚ ክቡር ዶክተር አብይ አሕመድ፤

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር፤ ክቡራን የምክር ቤቱ አባላት

ጉዳዩ፥ በሥራ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥትና የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን ይመለከታል፤

እኛ የሀገራችን የኢትዮጵያ ጉዳይ ግድ የሚለን፣ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ነዋሪ የሆንን ኢትዮጵያውያን ‘በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን ማሕበር’’ በሚል ሕጋዊ እውቅና ባለው ጥላ ስር ተሰባስበናል። አባሎቻችን በየምንኖርባቸው ሀገራት በተለያዩ ዘርፎች ለኢትዮጵያ ልዩ ልዩ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ። የሀገራችንን ጉዳይ በንቃት እየተከታተልን የምንኖርባቸው ሀገራት የውጪ ግንኙነት ተጠሪዎች ሙሉ መረጃው እንዲኖራቸው በማድረግም ላይ እንገኛለን። እንደ ማሕበር ሥራ ከጀመርንበት ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ ጠንካራ የዲፕሎማሲና የመረጃ ልውውጦች በተሳካ ሁኔታ አከናውነናል። የአባይ የመጀመርያው ዙር ሙሌት በአውሮፓ መገናኛ ብዙሃን ግብጾች በፈለጉት መጠን እንዳይራገብ፣ የተዘገበውም እኛን በመደገፍ መሆኑ አንዱ ማስረጃ ነው።

እንደሚታወቀው ለዘንድሮ መስከረም ወር ታቅዶ የነበረው 6 ተኛው የሕዝብ ተወካዮችና የጠቅላይ ሚንስትር ምርጫ በልዩ ልዩ አስቸጋሪ ምክንያቶች ቀደም ብሎ በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሊካሄድ አልቻለም። አንድ አንድ አካላት በታቀደው ቀንና ሰዓት ምርጫ ስላልተደረገ አሁን ያለው መንግሥትም ሆነ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከመስከረም 30 ቀን በኋላ ሕጋዊ አይደሉም ሲሉ ይደመጣሉ። ለዚህም ሀገሪቱ ላለችበት የሰላም መደፍረስና ፍጅት በዋናነት ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው ጸረ ኢትዮጵያ/ጸረ አንድነት ኃይሎች የሸረቡትና ወደማያባራ የባሰ ፍጅት የሚመራ ‘ሕገ መንግሥት የሚሉትን ሰነድ በመጥቀስ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ዛሬ ማክሰኞ 18/2012 በዋለው ችሎት 7 ዓመት ተፈረደበት

በመግቢያችን ላይ እንደገለጽነው፣ እኛ በአውሮፓ አህጉር የምንኖር ኢትዮጵያውያን ከምንኖርባቸው ሀገራት ከቀሰምናቸው መጠነ ሰፊ የትምሕርት፣ ሥራና የሕይወት ተመክሮ በመነሳት አሁን የኢትዮጵያ መንግሥት የሚተዳደርበትን ሕገ መንግሥት ስንመረምር የሚከተሉትን ጉልህ ግድፈቶች አግኝተናል።

 • በዓለም ላይ ካሉ 195 ሀገራት ሁሉ በተለየ ሁኔታ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የግለ ሰብን መብት በሚደፈጥጥ መልኩ የሚጀምረው ትርጉም አልባ በሆነ ‘’እኛ ብሔር ብሔረ ሰብ’’ በሚል የወል መጠርያ መሆኑ፥

 

 • በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ሆነ ሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ለምሳሌ እንደ Human Rights Watch ን በመሳሰሉት ይኽንን ሕገ መንግሥት ‘’ ግልጽነት የጎደለው‘’(Vague) ተብሎ መጠቀሱ፥

 

 • አዲሲቷ ኢትዮጵያ’’ን እንፈጥራለን በሚል ፈሊጥ ታሪካዊቷንና የአፍሪቃ የነፃነት ተምሳሌት፣ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነችው ኢትዮጵያ ሀገራችንን ለማፈራረስ የተሸረበ ሴራ መሆኑን እንረዳለን። ይልቁንም አሁን ያለው ሕገ መንግሥት ጸረ_ኢትዮጵያ የሆኑ ግለሰቦች ተቧድነው የወሻሸሉት እንጂ እኛ የምናውቃትን ከሦስት ሽህ ዓመታት በላይ የተመዘገበ ታሪክ ያላት ኢትዮጵያን የሚወክል ስላልሆነ ሰነዱ በአብዛኛው መለወጥ እንደሚገባው ተማምነንበታል።

 

ስለዚህ እነዚህንና ሌሎች መሰረታዊ ግድፈቶችን በማግኘታችን፣

የተከበራችሁ የምክር ቤት አባላት፣ የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ፤ ይህን የታሪክ አጋጣሚ ተጠቅማችሁ የተበላሸውን ለማሻሻል የተጣመመውን ለማቃናት ትጠቀሙበታላችሁ ብለን አሁን መንግሥት የሚጠቀምበትን ሕገ መንግሥት በከፊልም ቢሆን ሊተካ ይችላል ብለን፣ ከላይ የተዘረዘሩትን ግድፈቶች የሚቀርፍ የ‘’ሕገ ኢትዮጵያ’’ን ረቂቅ አሰናድተን ከዚህ ደብዳቤ ጋር ልከናል።

ከላይ ከተዘረዘሩት እንከኖች በተጨማሪ አሁን በሥራ ላይ ያለው ሰነድ(‘’ሕገ መንግሥት’’) የኢትዮጵያን ሕዝብ የዜግነት መብት የገፈፈ፣ ሰዎችን በሀገራቸው ባይተዋር ያደረገ ከመሆኑም በላይ መሰረታዊ የሆኑ የዲሞክራሲን የመምረጥና የመመረጥ መብት ያላገናዘበ እንደሆነ ግልጽ ነው። ስለሆነም 21 ኛውን ክፍለ ዘመን የሚመጥን ሕገ መንግሥት ለሀገራችን ለኢትዮጵያ

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ከሳተላይት በሚታይ ምስል የመቀሌ ብርሃማነትና የጎንደር ጨለማነት አስገራሚ ነው” የአለም ባንክ

ከማዘጋጀት ጀምሮ በሚከተሉት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የተሻሻለ ሕገ መንግሥት የሚቀጥለው 6 ተኛ ሀገራዊ ምርጫ ከመደረጉ በፊት ለሕዝብ ውይይት አቅርቦ እንዲያስጸድቅ፣ አሁን የሥራ ጊዜውን ያራዘመው መንግሥትና የተወካዮች ምክር ቤት ሃላፊነቱን እንዲወስድ በድጋሚ እናሳስባለን።

እኛም በቅርቡ በምንልከው ረቂቅ ሰነድ ውስጥ ሁሉም የተዘረዘረ ቢሆንም በሚከተሉት ዐበይት ነጥቦች ላይ አጽንዖት እንዲደረግባቸው በድጋሚ እንጠቅሳቸዋለን።

 • ሕገ መንግሥቱ በጎሣ ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝምን ሙሉ በሙሉ እንዲቀይር

 

 • ክልል የሚሉት ሕዝብን ከሕዝብ ነጣጥሎ የሚያራርቅ ማነቆ ለአስተዳደር በሚመች መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን በተመረኮዘ ክፍለ ሀገራት እንዲተካ፤

 

 • በየክልሉ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጅ ያልሆኑትን የዜግነትና ሰብአዊ መብትን የሚያስጠብቅ እንዲሆን፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የትም ይኑር የት ወይም የትኛውም ቋንቋ ተናጋሪ ቢሆን በመረጠው የኢትዮጵያ ክፍላተ ሀገራት የመኖር፣ የመምረጥም ሆነ የመምረጥ መብቱ ሙሉ በሙሉ እንዲከበር፤

 

 • በውጪ ሀገራት ነዋሪ የሆኑ/ የተወለዱ ኢትዮጵያውያን ካለ ምንም ገደብ የዜግነት መብታቸውን / ኢትዮጵያዊነታቸውን እንዲያስጠበቅ፥ የሌላም ሀገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያዊነታቸው እንዲከበር (dual Nationality) እንዲፈቀድ፣

 

 • የውሸት ትርክትን ተመርኩዞ የተዘራው ሕዝብን ከሕዝብ የሚያፋጅ የፈጠራ ታሪክ በሕግ ታግዶ በእውነት ላይ በተመሠረተ እንዲተካ፤ የትምሕርት ካሪኩለም/አሰጣጥ እንዲስተካከል፥

 

 • የሀገሪቱ / የመንግሥቱ ስርአተ መርህ በፕሬዝዳንት ሆኖ ሕዝብ በቀጥታ መሪውን እንዲመርጥ።

 

ቢደረግ ሀገራችን ከተደቀነባት የመፈራረሰ አደጋ ትድናለች ብለን በፅኑ እናምናለን።

ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!

የኢትዮጵያውያን ማሕበር በአውሮፓ፣ ፍራንክፈርት/ጀርመን

 

መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ.ም.

ግልባጭ፥ ለክብርት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

ለክቡር የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ

ለኢትዮጵያውያን የመገናኛ ብዙሀን በሙሉ

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሕወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት ተዘርፎ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ የገባውን የኢትዮጵያ habt ለማስመለስ ጥረቱ ከጫፍ ደረሰ

Europe

3 Comments

 1. ውድ የኢማአ አባሎች፡
  ማመልከቻችሁ ደርሶን አይተነዋል፡፡ ጥያቄአችሁ በመቅረቡ ችግር የለውም። ኦፊሺያል መልስ ለመስጠት ግን ያስችግራል፡፡ ጥያቄያዎቻችሁ በህግ አውጪው እንጂ በሥራ አስፈጻሚው የሚከናወኑ ስላልሆኑ ከጠ/ሚሩ መልስ አትጠብቁ፡፡ ስለማህበሩም በጥቂቱም ቢሆን መረጃ ቢኖረንም እናንተ በትከክል እነማን እንደሆናችሁ ግን ልናውቅ አንችልም፡፡ ቁጥራችሁስ ስንት ነው ብለን ለመገመት ክበደን? የብሄር ስብጥራችሁስ? ይቅርታ ይህን ጥያቄ ባንጠይቃችሁ እኛም ደስ ይለን ነበር፤ ግን ለጊዜውም ቢሆን አስፈላጊ ነው፡፡ ፡
  አንዳንዶቹ ጥያቄዎች የታሰቡ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ገን በማመልከቻ የሚስተናጋዱ ስላልሆኑ፡ ለጊዜው ሃሳባችሁን ማስፈጽሙ ይከብዳል፡፡ እንዲያውም በአሁኑ ውቅት አይቻልም፡፡ የራሱ ሂደትም አለው፡፡ እናንተ እስከዚያ ከቻላችሁ በማቴሪያል ደልቀቅ ያለውን የአውሮፓ ኑሮ ትታችሁ፤ ወደ ሃገር ቤት ተመልሳችሁ፤ ራሳችሁን በፓርቲ አደራጅታችሁ (ወይም አላማችንን ያራምድልናል የምትሉትን ተቀላቅላችሁ)፤ በምርጫ ተወዳድራችሁ፤ ህዝብ መርጧችሁ ፤ መንግስት መስርታችሁ ፤ ፈላጎታችሁን ማስፈጸም ትችላላችሁ፡፡ ከበሮ በሰው እጅ …እንዳይሆን ነገሩ አስቡበት፡፡
  እግረመንገድ ቢፈቀድልን፡፡ እንደው ለመሆኑ እናንተስ “በቀን አንድ ዶላር”ን ተግባራዊ አድርጋችኋል? ህገር ቤት ገንዘብ ስትልኩስ? ብላክ ማርኬት አትጠቀሙም? የማህበራችሁ አባላት ቢያንስ በብላክ ማርኬት እንዳይሳተፉ ታስተምራላችሁ? ለማንኛውም ጥያቄ ብቻ ሳይሆን እገዛችሁም አይለየን፡፡
  ከሠላምታ ጋር
  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት
  ግልባጭ፡ ለፈዴሬሽን ምክር ቤት
  እንዲያውቁት፡ ለሁሉም ህጋዊ ፓርቲዎች ጽ/ቤቶች (ለአባላት ምልመላ ሊጠቅማቸው ይችላል፡፡)

  • ውድ ከደር ሰተቴ፣ በቅድሚያ ጊዜዎን ወስደው ከላይ የተጠቀሰውን ደብዳቤ ለማንበብ እና ሃሳቦትን ስላጋሩን እናመሰግናለን። በነገራችን ላይ ከላይ የተፃፈእ “ደብዳቤ” እንጂ “ማመልከቻ” አይደለም፣ መቼም የፓርላማ አባል ሆነው በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት ያውቃሉ ብለን እንገምታለን። ሃሳብዎትን ጠቅለል ባለ መልኩ ስንመለከተው የሚከተሉትን ነጥቦች እናገኛለን፣ ምላሻችንም እንደሚከተለው ይቀርባል፣ ፩) የዚህ ደብዳቤ ዓላማ ፣መልእክትን ይዘቱ አሁን በስልጣን ላይ ያሉትን ጠሚ አብይ ለማስታወስ፣ ለማሳሰብና ብሎም ለማይቀረው ህዝባዊ የህግና የስርዓት ለውጥ እንዲዘጋጁ ለማድረግ እንጂ እንዲህ እንደዋዛ ምላሽ ጠብቀብም አይደለም።
   ፪) እርሶ እንዳሉት ግልፅ (official) ምላሽ ልናገኝ አንችልም ይሆናል፣ ባናገኝም ደሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን እስካወቀ ድረስና ትንሽም ቢሆን በአቅማችን ኢትዮጵያን ከተቀረቀረችበት የጎጥ የክክልልና የቋንቋ ፖለቲካ እንድትወጣ ለማድረግ መጣራችንን እስካሳወቅን ድረስ ምንም አይደል፣ አንድ ቀን እውን ይሆን ይሆናል።

   ፫( በርግጥ ይሄን ደብዳቤ የተፃፈበትን አድራሻ ካዩት የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ ይላል ፣ የድህረ ገፃችንን ቢጎበኙ እኛ ማን እንደሆንን የማህበራችንንም ዓላማ በግልፅ ይፕተፃፈውን ማንበብ ይችላሉ። አንዱ ስጋት ግን የፖለቱካ ድርጅቶች ወይም ስልጣን ናፋቂዌች መስለነዎት ከሆነ ተሳስተዋል፣ አይደለንም። እኛ ከተለያየ የህይወት፣ የትምህርትና የሙያ ልምድ የተሰባሰብን ኢትዮጵያዊያን ነን፣ ከስምና ከሙያችንን ውጪ እዚህ በሰለጠነው ዓለም ተቀምጠን ራሳችንን የምንቄጣጠርም አይድለንም። ግን ይ ማለት ጎሳ የለንም ቋንቋ የለንም ሃይማኖት የለንም የትውልድ ቤታ የለንም ማለት አይደለም። ግን እኛም ሆንን ባገር ቤት ያሉ ኢትዮጵያውያን በሰውነታቸው፣ በስምና በሙያቸው እንጂ በጎሳ ስምና አጥንት ተቆጣጥረው መገናኘት መሰባሰባቸውን ስለምናወግዝ ነው። ሁላችንም የሰው ልጅ ሆነን ነው ወደዚህ ምድር የመጣነው፣ ማናችንም አባትና እናታችን አልመርፕጥንም፣ ማናችንም ከዚህ ብሄር ወይ ከዚያ ብሄር እንቅልፍ ብለን አልመረጥንም። በጋራ ለምንኖርበት ህልገር ግን የጋራ የሆነ ህግና ስርዓት ብቻ ነው የሚያስፈልገን። ቋንቋ ሃይናኖትና ባህል ግን እንደየ አኗኗራችን ፍላጎትና ምርጫችን የፈለግነው መምርፕጥም መናገርም መልበስም መዝፈንም እብችላለን፣ መንግስት እዚህ ተወልዳችኃልና የዚህ ብሄር ናችሁ ብሎ ማንነት ሊጭንብን አንፈልግም። የሰው ልጅ ነፃ ፍጡር ነውና የትም ይወለድ የትም ከማንም ይወለድ ከማንም በየትኛውም ቤታብየመንቀሳቀ፣ ቋንቋ የመማር፣ ባህል የመቅሰም መብቱ የተጠበቀ ነው። የህውሃት ወያኔ ህገ መንግስት ይህን የሰው ልጅ መብት ይፃረራል። የሰው ልጆችን እንደ ከብት እብድ እንስሳ ባንድ ክልል ባንድ አካባቢ ባንድ ቋንቋ ባንድ ባህል ግድቦ የኢትዮጵያዊነታችንን መገለጫ የሆነውን ዥንጉርጉርነታችንን እያሳጣን ነው። ይህን ህገ ኢትዮጵያን ያዘጋጀነውም የኢትዮጵያ ህዝብ የሰው ልጅ መብቱን እንዲያውቅ፣ እንዲረዳ፣ እንዲይልስብ እና ከህውሃት ወይን የጎሳ የክልል የቋንቋ ፖለቲካ ተላቆ በሰውነቱ ደረጃ ከፍ ብሎ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር የመንቀሳቀስ የምስራት፣ የመነገድ ሃብት የማፍራት መብቱ የተጠበቀ እንዲሆን ብቻ ነው። ያ ብቻ አይደለም ከኢትዮጵያም ውጪ በየትኛውም የዓለም ክፍል ሳይሸማቀቅ በኩራት እንዲንቀሳቀስ እንዲማር እንዲነግድ ነው ያለ ምንም የዘር የጎሳ ፖለቲካ (ክፍፍል)።

   በመጨረሻም የደብዳቤያችንን ፍሬ ሃሳብ ከታሰበው ምርጫ በፊት ህገ ኢትዮጵያን ህዝብ ይወያይበትና ያፅድቅ፣ ይህ ለሁላችን እኩል የሆነ ህግ ሳይኖር በክልል በቋንቋና በሃይማኔት በተከፋፈለ ሃገር ምርጫ ማድረግ የሃገራችንን ህዝቦች እርስ በርስ ተጫረሱ፣ ተናከሱ፣ ተገዳደሉ እንደ ማለት ነው።
   እናም የእኛ ደብዳቤ በስልጣን ወይም የፖለቲካ ሳይሆን ምክራዊ አስተያየትና እገዛ ነው፣ ሃገራችን ህግና ውል ያለው የዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ እንድትገባ። እስካሁን ያለው ህገ መንግስትም ሆነ የመተዳደሪያ ደንቤች ጠመንጃ በያዙ ባለስልጣኖች ነው የሚፃፈውና በህዝብ ላይ የሚጫነው። ነገር ግን ያ ስህተት ነው። ስልጣን የሰፊው ህዝብ ነው፣ ህግ የሚይልውፕጣው ህዝብ (የህዝብ ተወካይ ሸንጎ) እንጂ በስልጣን ላይ ያለ ባለጊዜ አይደለም። መንግስትን ፕሬዚዳንትን ጠቅላይ ሚኒስትርን አወዳድሮ (ድምፅ ሰጥቶ) የሚቀጥረው ህዝብ እንጂ ራሱን በራሱ መሾም አይችልም። ጠሚ አብይ ምንም እንኳን የህውሃትን ህገ መንግስትና ባንዲራ ተመርኩዘው ቤተ መንግስት ቢገቡ የኢትዮጽያ ህዝብ ነው የመተዳደሪያ ደንቡን የሚፅፈው (ህጉን ምን ያክምህል በስልጣን እብደንሚቆዩ ፣ስልጣናቸውን ባግባብ ሳይጠቀሙ ሲቀሩ ከስልጣንም የሚያወርዳቸው)። ይህ እንግዳ ሃሳብ ሊሆንባችሁ እንደሚችል እንገምታለን ግን ቀስ በቀስ በውይይት በማንበብና በመጠያየቅ ይህ ግልፅ ሊሆንላችሁ ይችላል። ዋናው ነገር እኛም የተረዳነውን የምናውቀውን ይጠቅማል የምለውን ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ማካፈላችን ነው። ያለውን የወረወረ ንፉግ አይባልም። እንዲያው የማኪያቶ አንድ ዶላርና ሃዋላ ከመጠበቅ ሰውንም ሃገርንም ትውልድንም ሊቀይር የሚችል እውቀትና አሰራር እናበርክት ብለን ነው። ፍፁማዊ አይደለንም ፣ የምንፅፈው የምንናገረው ግድፈት ስህተት ሊኖረው ይችል ይሆናል፣ ሰውንም ልናስቀይም ይሆናል፣ ምናልባት በሃሳባችን ያልተስማማችሁ ቅር ያላችሁም ሆነ የተደሰታችሁ ካላችሁ ባድራሻችን ፃፉልን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነን!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር። (ከማህበሩ ማህከላዊ ኮሚቴ አንዱ)

 2. አቶ ፋሲል
  የእርስዎ ማህበር የሚለውን categorically የማይቀበል ተመጣጣኝ ኃይል እንዳለ ማህበራችሁ አይገነዘብም ማለት ነው? ታዲያ እነዚህ “የማይታረቁ ህልሞች” የተባሉት የእናተ ማህበር ባለው መንገድ ይፈታል ብሎ እንደ እናንተ የተማረ እና የተመራመረ ሰው እንዴት ያምናል? ቢያንስ ትንሽ ጊዜ አያስፈልገውም? እውነት እትዮጵያን በደንብ ካወቃችሁ እስቲ እንደገና አስቡበት፡፡

  “ስልጣን የሰፊው ህዝብ ነው፣”
  ይቺን እንኳ ይተዋት፡፡ መንግስቱ ኃይለማሪያምም እንደዛ ይል ነበር፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.