‹የኢትዮጵያ መንግሥትዕዳ ከጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሔራዊ ምርት (ጂዲፒ) ጋር ሲነፃፀር 57% ነው› – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

et34 ‹የኢትዮጵያ መንግሥትዕዳ ከጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሔራዊ ምርት (ጂዲፒ) ጋር ሲነፃፀር 57% ነው›   ሚሊዮን ዘአማኑኤልቅቤ ያልዋጡ የፖለቲካ ሰባኪዎች ዘመን አከተመ፣ቅቤ የዋጡ የኢኮኖሚ ሠባኪዎች ይመጣሉ!!! 

ከውኃ አጥማቂው ወደ እሳት አጥማቂው ዘመን  !!!

‹የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከጠቅላላ አመታዊ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ጋር ሲነፃፀር 57 በመቶ ነው›

ህወሓት/ኢህአዴግ ለሃያ ሰባት አመታት የሾፈረው የፖለቲካ ባቡር ሞተሩ አረጀና ፉርጎዎቹ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደቡብ አመጹበት ሃራ ገበያ ላይ ባቡሩ ወደ መቐለ ሳያመራ ወያኔ ተጠራርጎ ከመቐለ ገባ፡፡ አጎጌውን ባቡር የሚዘውሩት ያረጀውን ኢህአዴግ በመተው አዲስ ያቆቆሙት የብልጽግና ፓርቲ ካድሬዎች ከወገባቸው በታች ኢህአዴግ፣ ከወገባቸው በላይ ብልፅግና አሜቼ የተመረቱ የተገጠሙ ሆነና ጭንቅላታቸው እግሮቻቸውን ማዘዝ የተሳነው ዘመን መጣ፡፡ የብልጽግና ፓርቲ ፉርጎዎቹ የባቡሩን ሞተር አድሰው መሾፈር ከጀመሩ ከመጋቢት 2010ዓ/ም ጀምረው የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ማለትም የኢትዮጵያ ጠቅላላ አመታዊ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) 2.2 (ከሁለት ነጥብ ሁለት ትሪሊዮን) ብር ወደ 3.4 (ሦስት ነጥብ አራት ትሪሊዮን) ብር አሳድገናል ይላሉ፡፡ እንዲሁም  የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከጠቅላላ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ጋር ሲነፃፀር ከ31% (ሠላሳ አንድ) በመቶ ወደ 25% ሃያ አምስት በመቶ እንዲቀንስ አድርገናል ይለናል ዶክተር ዐብይ አህመድ በዚህ የቪዲዮ መልእክቱ አድምጡት፡፡ (https://www.youtube.com/watch?v=4DClE6-GRQs/Ethiopia: ሰበር – ከብልጽግና የሾለከው የዶ/ር ዐቢይ ቪድዮ-በሚዲያ ባልተለቀቀው ምስጢራዊ ስብሰባ ምን ተናገሩ? Dr Abiy Ahmed’s Speech/ 132,539 views/•Oct 8, 2020)

ዶክተር ዐብይ አህመድ በኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ ምስጢራዊ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ በሚል በቪድዮ የቀረበ መረጃ   በ የውሽትና በሃሰት ማስረጃዎች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እንዳደገ ገልፀዋል፡፡ ሆኖም የዓለም ኢኮኖሚ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዘመን በወደቀበት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አደገ ለማለት የሚያስችል አንዳችም አሳማኝ ምክንያት የለም፡፡  ዶክተሩ ዐብይ አህመድና የብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች ይሄን የዓለም ባንክ (The World Bank) መረጃ ከምንጩ  አጣርተው ሂስ እንዲውጡ ማድረግ አለባቸው እንላለን፡፡

  • በ2012 ዓ/ም የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከጠቅላላ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ጋር ሲነፃፀር 57 (ሃምሳ ሰባት) በመቶ ደርሶል፡፡
  • በ2012 ዓ/ም የኢትዮጵያ ጠቅላላ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ጋር ሲነፃፀር 57 (ሃምሳ ሰባት) በመቶ ደርሶል፡፡

 

{1} የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከጠቅላላ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ጋር ሲነፃፀር /Ethiopia Government Debt to GDP1991-2019 Data | 2020-2022 Forecast | Historic

የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከአመታዊ አጠቅላላ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) ጋር በማነፃፀር በየዓመቱ አጠቃላይ ዕዳችንን ከአመታዊ  አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ጋር የምናወዳድርበት የምጣኔ ኃብት ትምህርት ነው፡፡  በኢኮኖሚስቶች ምክረ ሃሳብ መሠረት፣ የአንድ አገር ዕዳ ዝቅተኛ ከሆነ ሃገሪቱ አምርታ በውጭ ንግድ ከምትሸጠው ምርት፣ ሸቀጣሸቀጥና አገልግሎት ከምታገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ እዳዋን ለመክፈል ያስችላታል፡፡ በአንፃሩ የሃገሪቱ ዕዳ ከፍተኛ ከሆነ ምርቶን ሸጣ የምታገኘው ገቢ እዳዋን ለመክፈል አያስችላትም፡፡ ስለዚህ ዕዳ ከጂዲፒ ንፅፅር ከመቶ ከሃምሳ በታች ሲሆን የተሸለ ሲሆን ከሃምሳ በላይ ከሆነ ግን ዕዳ ለመክፈል አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

“In economics, the debt-to-GDP ratio is the ratio between a country’s government debt and its gross domestic product. A low debt-to-GDP ratio indicates an economy that produces and sells goods and services sufficient to pay back debts without incurring further debt.” Wikipedia

The debt-to-GDP ratio is the metric comparing a country’s public debt to its gross domestic product (GDP). By comparing what a country owes with what it produces, the debt-to-GDP ratio reliably indicates that particular country’s ability to pay back its debts.

የህወሓት/ኢሀአዴግና ኦዴፓ ብልፅግና  የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከአጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) ጋር በማነፃፀር ከ1991 እስከ 2020እኤአ ዕዳ ከጂዲፒ ንፅፅር እንቃኛለን፡፡ በዚሁ መሠረት በ2010እኤአ 26.8%፣ በ2012እኤአ 27.4%፣ በ2014እኤአ 31.8%፣ በ2016እኤአ 34.9%፣ 2018 እኤአ 60%፣ በ2019እኤአ 57% በመቶ መሆኑን ከሠንጠረዡ ላይ መረዳት ይቻላል፡፡  ዶክተር ዐብይ አህመድ የሃገሪቱን የእዳ ጫና ከአጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) ከ31% በመቶ ወደ 25% በመቶ እንዲቀንስ አድርገናል ብለው ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡  ከታች የምጣዩት የሠንጠረዥ ማስረጃ ምንጩ ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ዶት ኮም/ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተገኘ እንደሆነ ያሳያል፡፡

Ethiopia recorded a government debt equivalent to 57 percent of the country’s Gross Domestic Product in 2019.

Ethiopia Government Debt to GDP1991-2019 Data | 2020-2022 Forecast | Historic (https://tradingeconomics.com/ethiopia/government-debt-to-gdp/)

342 ‹የኢትዮጵያ መንግሥትዕዳ ከጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሔራዊ ምርት (ጂዲፒ) ጋር ሲነፃፀር 57% ነው›   ሚሊዮን ዘአማኑኤል

{2}  የኢትዮጵያ አጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) Ethiopia: Gross Domestic Product, billions of U.S. dollars:

የኢትዮጵያ አጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) ከ1981 እስከ 2019እኤአ በቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተሰልቶ እንቃኛለን፡፡ በ2081እኤአ 7.32 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2091 እኤአ 13.46ቢሊዮን ዶላር፣ 2001እኤአ 8.23 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2011እኢአ 31.95 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2019 እኤአ 96.11 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የዓለም ባንክ የሠላሳ ሰባት አመታት መረጃ ከሠንጠረዡ መረዳት ይቻላል፡፡ በዓለም ባንክ ዘገባ መሠረት 174 (የመቶ ሰባ አራት) አገራት አማካይ ጂዲፒ (አጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት) 489.66 (አራት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ) ቢሊዮን ዶላር መሆኑን  አስገንዝበዋል፡፡

Ethiopia: Gross Domestic Product, billions of U.S. dollars:

For that indicator, we provide data for Ethiopia from 1981 to 2019. The average value for Ethiopia during that period was 23.99 billion U.S. dollars with a minimum of 6.93 billion U.S. dollars in 1994 and a maximum of 96.11 billion U.S. dollars in 2019. The latest value from 2019 is 96.11 billion U.S. dollars. For comparison, the world average in 2019 based on 176 countries is 489.66 billion U.S. dollars. See the global rankings for that indicator or use the country comparator to compare trends over time.

 

Ethiopia: Gross Domestic Product, billions of U.S. dollars

(measure: billion U.S. dollars; Source: The World Bank)

Year198119821983198419851986198719881989199019911992
GDP7.327.718.578.19.489,8510.5310.9111.4812.1813.4610.49

 

Year199419951996199719981999200020012002200320042005
GDP6.937.668.558.597.827.78.248.237.858.6210.1312.4

 

Year2007200820092010201120122013201420152016201720182019
GDP19.7127.0732.44429.9331.9543.3147.6555.6164.5974.381.7784.2796.11

https://www.theglobaleconomy.com/Ethiopia/GDP_current_USD/Ethiopia: GDP, current U.S. dollars (measure: billion U.S. dollars; Source: The World Bank)

Definition: GDP at purchaser’s prices is the sum of gross value added by all resident producers in the economy plus any product taxes and minus any subsidies not included in the value of the products. It is calculated without making deductions for depreciation of fabricated assets or for depletion and degradation of natural resources. Data are in current U.S. dollars. Dollar figures for GDP are converted from domestic currencies using single year official exchange rates. For a few countries where the official exchange rate does not reflect the rate effectively applied to actual foreign exchange transactions, an alternative conversion factor is used.

 

ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ አጠቅላላ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) 2.2 (ከሁለት ነጥብ ሁለት) ትሪሊዮን ብር ወደ 3.4 (ሦስት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ማደጉን ኢኮኖሚው መመንደጉንና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ  ድባቅ መተን ለዓለም ዓቀፍ ንግድ የምናስተምረው ትምህርት እንዳለ  ያበስሩን ይሆናል፡፡   የዓለም አቀፍ ንግድ እንቅስቃሴ ግብይይት የሚደረገው በዶላር፣ ፓውንድ፣ ዩሮ፣ በመሆኑ ዓለም ባንክና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) መረጃ በዶላር የሆነው ለዚህ ነው፡፡  በዚህም ስሌት በ2011ዓ/ም 2.2 (ከሁለት ነጥብ ሁለት) ትሪሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወደ ዶላር ስንቀይረው 75.9 ቢሊዮን ዶላር  (አንድ ዶላር በ29 ብር )ይሆናል፡፡ በ2012ዓ/ም  3.4 (ሦስት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ወደ ዶላር ስንቀይረው 94.4 ቢሊዮን ዶላር  (አንድ ዶላር በ36 ብር) ሲመነዘር ይሆናል፡፡ በጥቁር ገበያ የብር ምንዛሪ ተመን ከ46 ብር እስከ 50ብር መድረሱን በጥናታችን አረጋግጠናል፡፡ ዶክተር ዐብይ አህመድ  በኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ ቆራጥ አመራር የሃገራችንን ጂዲፒ ትሪሊየን ውስጥ ከተናል ለማለት አስቦ ከሆነ የብር የመግዛት አቅም መሽመድመድና ብር የወረቀት ያህል መርከሱን ያሳየናል እንጂ የኢኮኖሚ እድገት በኮቪድ 19 ዘመን የሚታሰብ አይደለም እንላለን፡፡ ዐብይ አህመድ ለመዋሸት ለምን ፈለገ፣

ፈጣን ነው ባቡሩ…. ዐብይ ዛሬ የተናገረውን ነገ አይደግመውም፡፡ አጠገብህ ያሉት ሰዎች ሰው ከሆኑ ቢመክሩህ!!!

{3} ‹‹አዲሱ የኢትዮጵያ 267 ቢሊዮን ብር (አንድ ዶላር በ36 ብር) ሲሰላ የአሜሪካ 7.3 ቢሊዮን ዶላር ነው!!! ››

{4} የአሜሪካ አንድ ቢሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ 36 ቢሊዮን ብር  በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባንኮች አጠቃላይ ካፒታላቸው በ 8 በመቶ አድጎ 85.7 ቢሊዮን ብር ወይም 3.1 ቢሊዮን ዶላር መሆኑ ታውቆል በ2018እኤአ

 The total capital of bank in Ethiopia has increased by around 8% to 85.7 billion birr (around $3.1 billion at the prevailing exchange rate)

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.