የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም የልቅሶ እና ዋይታ ከማስከተሉ በቀር ሌላ ለአገር አንድነት ሆነ ለህዝብ ደህንነት ያስገኘዉ ፋይዳ የለም

“ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ” አስተዳደር ምስረታ

በኢትዮጵያ ያልተማከለ የመንግስት አስተዳደር(ፌደራሊዝም) በንድፈ ሃሳብ ተቀምጦ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ አስካሁን የልቅሶ እናዋይታ መዘዝ ከማስከተሉ በቀር ሌላ ለአገር አንድነት ሆነ ለህዝብ ደህንነት ያስገኘዉ ፋይዳ አለመኖሩን ላለፉት ሀያ አመታት በተጨባጭ ታይቷል፡፡

ይህ ብቻ አይደለም ከስያሜ አስከ አደረጃጀት በአገር እና ህዝብ የወደፊት ዕጣ ፋንታ ምን ዕንደምታ ሊያስከትል እንደሚችል እንኳን ልብ ያለ ወይም ግድ የሰጠዉ ማንም አልነበረም ፡፡

ሆኖም ገና ከጥዋቱ የሚወጣ እንጀራ ከምጣዱ ነዉ እና ይህ ጅምር ከአገራችን እና ህዝባችን አልፎ ለምስራቅ አፍሪካ ሆነ ለመላ አፍሪካ አንድነት (Pana Africanism) የሚዋጥ እንዳልነበር የሚያዉቅ ያዉቀዋል፡፡

1280px Ethiopia 1991 1995.svg  የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም የልቅሶ እና ዋይታ ከማስከተሉ በቀር ሌላ ለአገር አንድነት ሆነ ለህዝብ ደህንነት ያስገኘዉ ፋይዳ የለምበዚህ ረገድ ከግዛት አስተዳደር ወሰን፣ አደረጃጀት እና ከህዝብ አኗኗር እንዲሁም ከህገ መንግስት ረቂቅ ፣ይዘት፣አተገባበር እና አዝማሚያ አኳያ  የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን እዉነተኛ የህዝብ አለኝታነታቸዉን ምንም ኣይነት አፍቅሮ ንዋይ፣ምቾት እና የህልዉና ስጋት ሳይበግራቸዉ በብርቱ  ተጋድሎ ያደረጉት እነ ፕሮፌሰር አስራት እና ዶ/ር መኮንን ቢሻዉን ፣አሰፋ ማሩ እና የመሳሰሉትን ትዉልድ የማይረሳቸዉ የታሪክ እና የተዉልድ አንጸባራቂ ፈርጦች መሆናቸዉን ሳንዘነጋ ነዉ፡፡

የሆነዉ ሆኖ “የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ”መስራች አካባቢዎች ማለትም ከፋ ፣ ሸካ፣ ሸኮ፣ ቤንች ሸኮ ( ቤንች ማጅ ) ምዕራብ ኦሞ፣ዳዉሮ እና ኮንታ  በአንድ አስተዳደር እና ስያሜ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ  ሆነዉ እንዲቆቋሙ መሆን የሚበረታተዉ ኢትዮጵያዊነት የሚያስከትል ቅፅል ስያሜ መያዛቸዉ ነዉ፡፡

ከዚህ ሌሎች እና ነባር ክልል ግን በቋንቋ(ብሄረሰብ) ለሚጠሩት አይነተኛ ምሳሌ ነዉ፡፡

ከላይ የተገለጹት በአብዛኛዉ በቀድሞዉ ከፋ እና ኢሉ አባቡር ክፍለ ሀገራት የነበሩ ሲሆን በመልካ ምድር አቀማመጥ እና ኩታ ገጠምነት ፣በስነልቦና፣ በቋቋ፣ በባህል መሰል መቀራረብ አንድ መሆናቸዉ ለብሄራዊ አንድነት መጠናከርም በብዙ እይታ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ፡፡

እኛም ይህ “የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ” በየመንደሩ ለግል እና ቡድን ከንቱ ፍላጎት እና ምኞት ለመንገስ ለሚሹት አይነተኛ መሳያ እንደመሆኑ እነርሱም ሆነ ማዕከላዊ መንግስት ከዚህ ሊወስዱት የሚገባ ተሞክሮ ይኖራል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ማላጅ ፡ ያሚ

ምንጊዜም እናት አገር ትኑር !!!!

2 Comments

  1. ሰማይ ወረደ መሬት ከጠቀስከው የተሻለ አደረጃጀት የለም የዚህ ክፉ ፕሮግራም ዋናው ጠንሳሽ አረጋዊ በርሄ ድርጅቱ ያለው ትግሬ ውስጥ ነው እሱ ቤትና ቀለብ ተሰፍሮለት የሚኖረው በሌላው የኢትዮጵያ ክልል ነው። ነገሩ ሁሉ ቀልድ ሁኗል እኮ ጎበዝ። ትንሽ እፍረት የለውም የሚታገልለት ነገድ ትግሬ ውስጥ ሁኖ አዲስ አበባ ቁጭ ሲል? ወይስ በሞጋሳ ኢትዮጵያዊ ሁናል?ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ሲጠየፈው ይገርማል። የስራውን ሰጥቶታል ኢትዮጵያን ወግቶ ኢትዮጵያ ትቀልበዋለች።

  2. EPRDFites are from refugee camps in Sudan who loves bed feeling inferiority complex until now, Abiy Ahmed included in these mentality also SI CE he was raised by Meles & Co.
    . The only way these people who got inferiority complex feel equal is if they attack and get away with it. But that feels mg don’t last long so they got to keep attacking again and again. The only way for the EPRDFites federalists to feel good about themselves is if they succeed in doing what they know is inflicting harms on others so in their eyes federalism their only source of feeling equality.

    If they get attacked and suffer harm they claim they got harmed more severely than they deserved because their harm are as just goofing around horse playing not serious , they just do it in search of feeling good feeling equality trying to seek attention , trying to seek sense of belongingness to an equality.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.